9.5 ሚልዮን የባለ አንድ እና የባለ አምስት ብሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት ከገበያ ውጭ ሆኑ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው።

ብሮችን የሚቀብሩ እና አሽገው የሚያስቀምጡ እንዳሉ የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባንኩ የህዝብ ግንኝነት ሰራተኛ፣  በየጊዜው የብር ዋጋ የመግዛት አቅም እየተዳከመ በመሄዱ ህብረተሰቡ ተጎጅ እየሆነ መምጣቱን ይገልፃሉ፡፡

መንግስት በብር አያያዝ በኩል ምንም አይነት የግንዛቤ ስራ ባለመስራቱ በመንግስት ላይ በ2005 ዓ/.ም ብቻ 3.3 ሚልየን ብር የህትመት ወጭ ኪሰራ እንደገጠመው ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ በተጠቀሰው አመትም 9.5 ሚልየን ብር የሚወክሉ የገንዘብ ኖቶች ከአገልግሎት ውጭ ሆነው ተቃጥለዋል።