መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉበርግ የአለማቀፍ አጥኚዎች ቡድንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው መንግስት በማስገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ መሰረቱ ችግሮች ሊኖሩበት ስለሚችል መንግስት እንደገና እንዲያስጠና መክሯል። ግድቡ በታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በደንብ መጠናት አለበት ሲሉ የባለሙያዎቹ ቡድን አስተያየቱን ሰጥቷል። የግድቡን መሰረት ለማጠንከር መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ያስፈልጋል በማለት ያመለከቱት ባለሙያዎች፣ “ድክመት ቀጠና ” ተብሎ በተለየው አካባቢ ...
Read More »ከ200 በላይ ስደተኞች አሁንም አልተገኙም
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ደሴት አካባቢ በጀልባ መስጠም ከሞቱት መካከል የ11 ሰዎች አስከሬን ቢገኙም፣ ከ200 በላይ ሰዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም። ፖፕ ፍራንሲስ በስፍራው ተገኝተው አደጋውን ከተመለከቱ በሁዋላ ሀዘናቸውን ገልጸዋል፣ ችግሩን ዝም ብለው የሚያዩትን አገራትም ወቅሰዋል። ብዙ የጣሊያን ባለስልጣናት የህጻናቱን አስከሬን እያዩ ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ሲያለቅሱ ታይቷል። እስካሁን ድረስ አስከሬናቸው የተሰበሰበውና የጠፉት ሰዎች ...
Read More »የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር የብቃት መመዘኛ ፈተና ዙሪያ መግባባት ባለመቻላቸው ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስተላለፈው ውሳኔ በተማሪዎቹና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባትን በመፍጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሰቲውም የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ እንዲወስዱ ሲጠይቃቸው ተማሪዎቹ በቂ የዝግጅት ጊዜ ...
Read More »የህንድ ኩባንያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልን ሊያስተዳድር ነው
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽንን የሥራ ሂደት ለማስተዳደር አንድ የህንድ ኩባንያ ተመረጠ፡፡ ፖወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ኦፍ ኢንድያ የተባለው ኩባንያ የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ሀይል ለማስተዳደር የሁለት ዓመት ኮንትራት ተሰጥቶታል፡፡ መንግስት ድርጅቱን ለውጭ ኩባንያ መስጠት የወሰነው በድርጅቱ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉና የተሻለ ስራን በሀገሪቱ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ ድርጅቱን ለውጭ ...
Read More »ደቡብ ክልል ለዋልታ 19 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ፈቀደ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ብሔራዊ መንግስት መስተዳደር በክልሉ ያሉ ከተሞችን አስመልክቶ ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራት ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 19 ሚሊዮን ብር ለመፍቀድ ስብሰባ መቀመጡን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ በፖለቲካ ውሳኔ ለመንግስታዊው ዋልታ የመረጃ ማዕከል ሊሰጥ የታቀደው ፕሮጀክት የደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሀንን ቅር ማሰኘቱ ታውቋል፡፡ የክልሉ መገናኛ ብዙሀን በቂ መሳሪያና የሰው ሀይል እያለው ስራውን ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ ለዋልታ እንዲሰጥ ...
Read More »በሙስና ከተጠረጠሩ ግለሰብ 7 ሚሊዮን ጥሬ ብር ተያዘ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበሪያ ሀላፊ ከነበሩት ግለሰብ ሰባት ነጥብ አራት ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብ መያዙን የፌደራል ስነ ምግባር ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጹ፡፡ ሀላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ስዩም 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል የሚል መረጃ ቀርቦባቸዋል፡፡ ከመኪናዎቹ በተገኘ የሽያጭ ...
Read More »በሜዲትራንያን ውቅያኖስ 130 አፍሪካዊ ስደተኞች ሞቱ
ከሊቢያ ወደ ጣሊያን 500 አፍሪካውያ ስደተኞችን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የእሳት አደጋ በትንሹ 130 ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸው ተሰማ፡፡ ከአቅሟ በላይ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ጣሊያን የሚሄዱ ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ በመጨናነቋ ከተሳፋሪዎች አንዱ እርዳታን ለማግኘት ሲል በለኮሰው እሳት ጀልባዋ መቀጣጠሏን አሶሼትድ ፕሬስ ከጣሊያን ዘግቧል፡፡ የእሳት ምልክትን ከሩቅ አይተው ሰዎች ለእርዳታ ይደርሱልናል በሚል የተለኮሰው እሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጀልባዋን በእሳት ...
Read More »ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ማፈንና አደባባይ መከልከል በህግም በታሪክም ያስጠይቃል ሲል አንድነትና 33 ፓርቲዎች በጋራ አስታወቁ
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲዎቹ ባወጡት መግለጫ የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን በመስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል የሚገልፅ የዕውቅና ደብባቤ ቢሰጠንም ፣ በእጅ አዙር ሠልፉን በመስቀል አደባባይ እንዳናደርግ ከመከልከሉም በላይ ከሕግ ውጨ በመከላከያ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ እንድንሰለፍ ለማስገደድ በመሞከርና ቅስቀሳ እንዳናደርግ ...
Read More »በጀልባ መስጠም ከ130 በላይ ሰዎች አለቁ
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአብዛኛው የኤርትራንና የሶማሊያን ዜጎች ከጣሊያን በመጫን ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበረችው ጀልባ ላምፔዱሳ በሚባለው የጣሊያን ደሴት አካባቢ ስትደርስ በመስጠሙዋ በውስጧ ከተሳፈሩት መካከል ከ130 በላይ የሚሆኑት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አስታውቋል። እስካሁን 150 ሰዎችን ለማትረፍ የተቻለ ሲሆን፣ የ130 ሰዎች አስከሬን ደግሞ በወደብ ሰራተኞች ተሰብስቧል። ጀልባዋ 500 የሚሆኑ ሰዎችን ይዛ ጉዞ መጀመሩዋ ...
Read More »ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አፈጻጸም ላይ ድክመት ማምጣቱን በመገምገም የማሻሻያ እርምጃ መወሰዱን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ አቶ ደመቀ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ትላንትናና ዛሬ ታትሞ በወጣው ቃለምልልሳቸው ላይ አቶ መለስ ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አንዳንድ ዘርፎችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሸ ችግር እንዳጋጠመ ...
Read More »