ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳናዊው ቱጃር ሞ ኢብራሂም የተቋቋመው የሞ ፋውንዴሽን መልካም አስተዳደርን ያሰፈረ፣ ስልጣኑን በሰላም ለለቀቀ የአፍሪካ መሪ 5 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣል። በዚህ አመትም ለ4ኛ ጊዜ አሸናፊ የሚሆን የአፍሪካ መሪ አልተገኘም። እስካሁን ድረስ ሽልማቱን ያሸነፉት የኬፕ ቨርዴው ፔድሮ ቬሮና ፓይሬስ፣ የቦትስዋናው ፌስተስ ሞጋኤና የሞዛምቢኩ ጆአኪም ቺሳኖ ናቸው።
Read More »አንድ የናይጀሪያ ተጫዋች በኢትዮጵያ ደጋፊዎች መመታቱ ተዘገበ
ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በናይጀሪያ ቡድን መሸነፉ ያበሳጫቸው ደጋፊዎች የናይጀሪያን ቡድን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ ድንጋይ በመወርወር አንድ ተጫዋች አቁስለዋል። ኖሳ ኢግቦር የተባለው ተጫዋች መዳፉ አካባቢ መመታቱን የዘገበው ቢቢሲ፣ የናይጀሪያ ቡድን ባለስልጣናት ክስተቱን ለአለማቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽን ማሳወቃቸውንም ገልጿል። ድርጊቱን ተከትሎ ምናልባትም ፊፋ በኢትዮጵያ ላይ ቅጣት ሊጥል ይችላል። በሌላ ዜና ...
Read More »ከ15 ሺ በላይ የኢህአዴግ አባላት መልቀቂያ አስገቡ
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው የአባላት ግምገማ ወቅት ከ15 ሺ በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይፋ ተደርጓል። ስራቸውን ከሚለቁበት ምክንያቶች መካከል በድርጅቱ አመኔታ ማጣት ፣ ተገቢውን አገልግሎት ክፍያ አለማግኘት፣ ለድርጅቱ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍተኛ መሆን እና የድርጅቱ አባላት ሹመት በወገን መሆኑ የሚሉት ተጠቅሰዋል። ከፍተኛ የአባላት መልቀቂአ ቁጥር ከተመዘገበባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ በ9 ሺ 4 መቶ 56 ...
Read More »እ.ኤ.አ በ2020 የአፍሪካ ምርጥ በተመንግስት መሆን ራዕይ ሰነቀው የቤተመንግስት አስተዳደር ለተሰናባቹ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለሁለተኛ ጊዜ የተከራየው በወር 400 ሺ ብር ፣ በዓመት 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት ኮንትራቱ እንዲሰረዝ ተወሰነ፡፡
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አስተዳደሩ ቀደም ሲል በወር 530 ሺ ብር ገደማ ቤት በመከራየት ውል ከፈጸመ በኋላ ከሕዝብ በተከታታይ ተቃውሞ መሰማቱን ተከትሎ እንዲሰረዝ በመወሰን ለሁለተኛ ጊዜ 400 ሺ ብር የሚያወጣ ቤት በአዲስአበባ አክሱም ሆቴል አካባቢ መከራየቱ ሌላ ተቃውሞና ውግዘትን እያስከተለበት ይገኛል፡፡ አስተዳደሩ ፕሬዚደንቱ በመስከረም ወር 2006 ስልጣን እንደሚያስረክቡ አስቀድሞ እያወቀ ምንም ዓይነት ዝግጅት ሳያደርግ በመጨረሻው ሰዓት ወደቤት መከራየት ...
Read More »አፍሪካ ህብረት የዓለማቀፉን የወንጀኞች ፍርድ ቤት ወቀሰ
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ በ አፍሪካ ላይ ስጋት እያሳደረ ነው ሲሉ አንድ ከፍተኛ የህብረቱ ባለስልየጣን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘገበ። የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም ይህን ያሉት፤ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው የህብረቱ ልዩ ስብሰባ ላይ ነው። ቴዎድሮስ በስብሰባው ላይ ፦”ፍርድ ቤቱ ያነጣጠረው አፍሪካ ላይ ነው።”ማለታቸውን የገለጸው ቢቢሲ፤ በስብሰባው አፍሪካ ከዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ...
Read More »ሸህ መሀመድ ሁሴን አል ዓሙዲ ቤቶችን ተነጠቁ
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት ጋር ባላቸው ከመጠን ያለፈ ወዳጅነትና ቅርበት የሚታወቁት ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ለእግዶች ማረፊያ የተከራዩዋቸውን ቤቶች እንደተነጠቁ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ሼሁ፤ ከውጪ አገራት ለሚመጡባቸው እንግዶች በአያት ሲ.ኤም. ሲ 25 መኖሪያ ቤቶችን ለውጪ አገር ጎብኝዎች በተሰላ ሂሳብ ተከራይተው +በዶላር ምንዛሬ እየከፈሉ ሲገለገሉባቸው መቆየታቸውን የጠቀሱት እነዚሁ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች፤ መንግስት ባልተገለጸ ምክንያትና የኪራይ ውሉን በማፍረስ ...
Read More »የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጠየቀች
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት። እስከዳር” አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች። “ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ ይሄ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ ...
Read More »በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውና መኪና የሚያሸልመው የ ኢሳት ልዩ ቶምቦላ ፤ ወጣ
ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውና መኪና የሚያሸልመው የ ኢሳት ልዩ ቶምቦላ ፤ ታዛቢዎች በተገኙበትና ለሚዲያ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት አምስተርዳም በሚገኘው የ ኢሳት ስቱዲዮ በይፋ ወጥቷል። በመሆኑም መኪና የሚያሸልመው አሸናፊ ቁጥር፦ 2657 ሆኗል። የዕጣው አሸናፊ በአስር ቀናት ውስጥ አምስተርዳም፣ ወይም ዋሽንግተን ዲሲ፣ ወይም ለንደን ከሚገኙት ስቱዲዮዎች ለአንድኛቸው በስልክ ወይም በኢሜይል ...
Read More »የኢሳት ቶምቦላ ቁጥር ለማወቅ እዚሕ ይጫኑ
የኢሳት ቶምቦላ ቁጥር የተሸጠባቸው ሐገሮች ለማወቅ እዚሕ ይጫኑ
Read More »ፍጥጫ በሞላበት የብአዴን አባላት ግምገማ ከ 1 መቶ 70 በላይ ሰዎች በአንድ ጊዜ መልቀቂያ አስገቡ
መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና በስርአቱ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ኪራይ ...
Read More »