የሞይ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለ5ኛ ጊዜ ለሽልማት የሚበቃ የአፍሪካ መሪ ማጣቱን አስታወቀ

ጥቅምት (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በሱዳናዊው ቱጃር ሞ ኢብራሂም የተቋቋመው የሞ ፋውንዴሽን መልካም አስተዳደርን ያሰፈረ፣ ስልጣኑን በሰላም ለለቀቀ የአፍሪካ መሪ 5 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣል።

በዚህ አመትም ለ4ኛ ጊዜ አሸናፊ የሚሆን የአፍሪካ መሪ አልተገኘም።

እስካሁን ድረስ ሽልማቱን ያሸነፉት የኬፕ ቨርዴው ፔድሮ ቬሮና ፓይሬስ፣ የቦትስዋናው ፌስተስ ሞጋኤና የሞዛምቢኩ ጆአኪም ቺሳኖ ናቸው።