ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሌ በራያ ቆቦ ወረዳ ከ40 በላይ መንገደኞች ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ በመገልበጡ ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶችም ቆስለዋል። መኪናው ከጭንቱ ልክ በላይ ሰዎችን ጭኖ መጓዙ ታውቋል። በኢትዮጵያ የመኪና አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨ መ ረ መሄዱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል።
Read More »ዚምባቡዌ በሕገወጥ መንገድ ድንበሯን በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ ነበሩ ያለቻቸውን 38 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች፡፡
ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያው ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ሙታሬ በምትባለውና ከሞዛምቢክ ጋር ድንበርተኛ በሆነችው ከተማ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ በፖሊስ እንደተያዙ ማክሰኞ ማምሻውን ተዘግቧል፡፡ ተጠርጣሪ ስደተኞቹ በግምት ከ20 እስከ 30 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚምባቡዌ በሕገወጥ መተላለፊያ በኩል መግባታቸውን ያስታወቁት፣ በዚምባቡዌ ቤት ብሪጅ ዲስትሪክት የፖሊስ ኮማንደር ዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት ላውረንስ ...
Read More »በሁለት የቀድሞ የህወሀት ባለስልጣናት ቤቶች በርካታ የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አቃቢ ህግ ገለጸ
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ህግ አንድ ግለሰብ ከመንግስት በማስፈቀድ አንድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲይዝ ቢፈቀደልትም ፣ በተግባር ግን አብዛኛው ህዝብ በመሳሪያ አሰሳ ስም የግል መሳሪያውን መቀማቱን በተለያዩ የመገናኛ ብሀን ሲዘገብ ቆይቷል። በ1997 ምርጫ ወቅት የአንድ ብሄር አባላት በገዢው ፓርቲ ህወሀት ራስን የመጠበቂያ መሳሪያ እንዲታደላቸው መደረጉ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል። የፌደራል አቃቢ ህግ በቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ...
Read More »20 ሚሊዮን ገደማ የፈጀው ስታዲየም 3 አመት ሳይሞላው ፈረሰ
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 13ኛውን የአርብቶ አደሮች ቀን ለማክበር ደቡብ ኦሞ ዞንን ለማክበር በተገኙበት ወቅት ለእርሳቸው ክብር መገለጫ እንዲሆን እስከ 20 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የሚነገርለት ስታዲያም በጅንካ ከተማ ተስርቶላቸው ነበር። ይሁን እንጅ ስታዲየሙ ሶስተኛ አመቱን ሳይደፍን ለሁለተኛ ጊዜ ፈርሷል። በመጀመሪያ ከክቡር ትሪቡኑ በስተቀኝ በኩል ያለው ክፍል ፈርሶ ጥገና ሲደረግለት፣ አሁን ደግሞ ክቡር ትሪቡኑ ...
Read More »በቅርቡ ከቴሌ ጋር ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ውል የተፈራራመው የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ንብረት ሊወረስ ነው
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኩባንያው ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎችን ታክስ ሳይከፍል በቴሌ ስም ሲያስገባ በመገኘቱ ንብረቱ እንዲወረስ እንደሚደረግ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ቴሌ ለኩባንያው እቃዎችን እንዲያስገባ ፈቃድ አለመስጠቱን በመግለጹ ችግሩ ይፋ መውጣቱን ጋዜጣው ዘግቧል። ሁዋዌ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በአይነት ከ235 በላይ እቃዎችን አስገብቷል፤ ይኸው ኩባንያ ከሶስት ወር በፊት የማስፋፋት ስራ ለመስራት በሚል የ800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከቴሌ ...
Read More »በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤ/ክ አባቶች ባሰሙት ጠንካራ ንግግር ላይ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች አስተያየታቸውን ሰጡ
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ የሀይማኖቱ አስተማሪ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱትን ነጥቦች ዘርዝሮ አቀረበ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀይማኖት አባቶች በድፍረት መናገራቸው ከምን የመጣ ይመስለውታል ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ ምናልባትም ለውጡ ከፓትርያርኩ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ገምተዋል። እስካሁን የነበረው ልዩነት ...
Read More »የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጆች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ናቸው
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር የህወሀት ተጋይ የነበሩትና በአሁኑ ጊዜ በገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙት ታዋቂው ታጋይ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፣ ልጆቻቸው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። የማነ የተባለው ልጃቸው፣ በእስር ቤት ላይ በደረሰበት ግፍ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ሆኗል። አህፎም ደግሞ ከስራ ገበታው ላይ ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ፣ ላለፉት 7 ወራት ያለምንም ፍትህ ...
Read More »በትግራይ አንድ ቄስ ተገደሉ
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ክልተ አውላዕሎ ወረዳ ፣ አይናለም እየተባለ በሚጠራው ጣቢያ በቤተክርስትያን ግንባታ ምክንያት በህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል አምባጓሮ ተፈጥሮ አንድ ቄስ ተገድለዋል። የመቀሌው አብርሀ ደስታ እንደዘገበው ፣ ቄሱ ህዝብና ቤተክርስትያኑ ወክለው ከመንግስት አካላት ጋር ሲከራከሩ የነበሩ ሲሆን በመንግስት ካድሬዎች የተለያየ ዛቻ ሲደርሳቸው ቆይቶ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በሌሊት ተገድለው ተገኝተዋል። ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አያይዞ ...
Read More »የኢትዮጵያ የውይይት መድረክ በስዊድን የውይይት መድረክ አዘጋጀ
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታን በተመለከተ በተለይም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን የኦጋዴን ህዝብ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ያሳየውን ዶክመንትሪ ፊልም የተመለከቱ የስዊዲን የህግ ጠበቃና የአለም አቀፍ የህግ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሪስት ስቴላ ያርዴት የመንግስት ባለስልጣናትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንደተዘጋጁ በማስታወቃቸው እሳቸውንና ሌሎችን እንግዶች በመጋበዝ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በጉራፈርዳ፤በቤንሻንጉል፤በአሶሳ፤በአርባጉጉና ...
Read More »ኦብነግ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት በም/ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚመራው የልኡካን ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን የግንባሩ ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ9 የክልል መሪዎችንና ባለሀብቶችን አስከትለው በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ ቀብሪደሀር አየር ማረፊያ ባረፉበት ወቅት ነው። ባለስልጣኖቹ ጉበኝት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ ተነግሮን ስለነበር ጥቃቱን ለመፈጸም በበቂ ...
Read More »