በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤ/ክ አባቶች ባሰሙት ጠንካራ ንግግር ላይ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች አስተያየታቸውን ሰጡ

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ የሀይማኖቱ አስተማሪ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ  ጉባኤ በ፴፪ው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱትን ነጥቦች ዘርዝሮ አቀረበ ነው ብለዋል።

ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀይማኖት አባቶች በድፍረት መናገራቸው ከምን የመጣ ይመስለውታል ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ ምናልባትም ለውጡ ከፓትርያርኩ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ገምተዋል። እስካሁን የነበረው ልዩነት መሪው ላይ ያለው ልዩነት ይመስለኛል ያሉት መምህሩ፣ ራሳቸው ፓትሪያርኩ የጳጳሳቱ ደጋፊዎች ነበሩ ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

የሀይማኖት አባቶችና ቤተክርስቲያኑዋ ችግሮች እንዲፈታ እስከምን ደረጃ ልትሄድ ትችላለች ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ያስቀይሰዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በገዢው ፓርቲ በርካታ ግፎች ሲፈጸሙባቸው የቆዩት አባ  አመሐ እየሱስ ፣ የሀይማኖት አባቶቹ አስተያየት የረፈደና ከጭንቀት የመጣ ነው ብለዋል።

“አገር ፈርሶ ከጠፋ፣ ሰንደቃላማ ከተዋረደ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከስጋዊ አልፎ መንፈሳዊ ህይወቱ ከተናጋ በሁዋላ አሁን ለመናገር የደፈሩት፣ ከጭንቀታቸው ለመውጣት መስሎ ስለሚታያቸው ነው በማለት አባ አምሀ እየሱስ ተናግረዋል ። በዚሁ ዙሪያ የተቀናበረውን ዝግጅት በሚቀጥሉት ቀናት እንደምናቀርብ ለመግለጽ እንወዳለን።