በሁለት አመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ተሰደዋል

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች   ሲሆን፣ በህጋዊ መንገድ የተጓዙትን ሲጨምር አሀዙ በእጥፍ ሊጨምር ይችላል። መንግስት በቅርቡ ለስራ በሚል ወደ ውጪ በሚጓዙት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወቃል።  የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ስምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ሀይሌ እንዳሉት ፥ እገዳው ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ...

Read More »

መምህራንን ለመቆጣጠር መንግስት አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ አደረገ

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራን ለኢሳት እንደገለጹት አደረጃጀቱ ተግባራዊ በሆነባቸው በጎንደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ከሆኑ ከመምህራን አንድ፣ ከተማሪዎች አንድ ከፖሊስ አንድ እንዲሁም ከወላጆች አንድ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራንን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮች ይከታተላሉ። መመሪያው በሁሉም ትምህርት ቤቶች የወረደ ሲሆን፣ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ተግባራዊ ሆኗል። ...

Read More »

በታች አርማጭ በደዊ ቀበሌ አንድ የጸጥታ ባለሙያ አንዱን ግለሰብ ከእስር ቤት በማውጣት መግደሉ ተሰማ

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት ከስፍራው የደረሰው ዘገባ እንዳመለከተው ጋሻው የቆየ የተባለው የጸጥታ አስከባሪ የ28 አመቱን  ጎሹ እያዩ የተባለውን አርሶ አደር  ከመጠጥ ቤት ውስጥ እንዲወጣ ካደረገ በሁዋላ፣ ወደ እስር ቤት ወስዶታል። በመንግስት የተሾመው ታጣቂ ወጣት የጸጥታ ማስጠበቅ ስራ ለመስራት በሚል ለመስክ ስራ ተልኮ በነበረበት ወቅት ነው ወጣቱን ያለምክንያት ወደ እስር ቤት ካስገባው በሁዋላ፣ ከእስር ቤት አስወጥቶ ...

Read More »

የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሙስና ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደመሰረተባቸው የዘገበው ፋና ነው። የስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በክሱ ፣ ተከሳሹ ህግ እና አሰራርን ...

Read More »

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከተማሪዎች አመጽ ጀርባ ኢሳት እና ሌሎች ሀይሎች እንዳሉበት ገለጸ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተማሪዎች  የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲው ትክክለኛነቱን አረጋግጦዋል፡፡ የተማሪዎች አመጽ የተነሳው መንግስት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብ እና የአምልኮ  ስርዓት ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።  ” ተማሪዎች  እምነታችሁ ተው ፣ ማተባችሁን በጥሱ” ተብለናል ይላሉ። በ2004 እና በ2005 ዓም ተማሪዎች ህጉን እንዲተገብሩ  ሙከራ ቢደረግም  ተማሪዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህጉ  ሳይተገበር ቀይቷል ሲሉ ...

Read More »

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞቹን አባረረ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ  በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ በእለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ...

Read More »

በደብረ-ብርሀን በማጅራት ገትር በሽታ ሰዎች እየሞቱ ነው

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በበሽታው እስካሁን ከ4 በላይ ሰዎች ሞተዋል። 3 ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ተኝተዋል። በአዲስ አበባ የማጅራት ገትር በሽታ ክትባት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል። የማጅራት ገትር ሕመም በተዋህሲን አማካይነት ተከስቶ የአንጎልን ህብለሰረሰር በተለይ ከራስ ቅል በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ሕመም ነው፡፡ በባክቴሪያ አማካይነት የሚከሰተው ማጅራት ገትር በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚተላለፍ ፣ በምድር ...

Read More »

ለመለስ ፋውንዴሽን ህዝብ የሰጠው መለስ ቀዝቃዛ ነው ተባለ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም መጨረሻ በይፋ የተመሠረተው የመለስ ፋውንዴሽን ዓላማውን ለማሳካት ከሕዝብ ገንዘብ በመዋጮ መልክ ለማሰባሰብ እያደረገ ያለው ጥረት የታሰበውን ያህል ውጤት እያስገኘ አለመሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ በመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 781/2005 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተመሰረተው ይህው ፋውንዴሽን ቤተመጻህፍትና ሙዚየም ለማቋቋም በማሰብ ሕዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በየቀኑ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ...

Read More »

ከአሸጎዳ የንፋስ ሃይል ማመንጫ በስተጀርባ ሙስና መኖሩን መረጃዎች አመለከቱ ፡፡

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል በሚል በ210 ሚሊዮን ዩሮ ወይም በ5 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገነባው የአሸጎዳ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 120 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት፣ በአዳማ ከተገነባው ከሁለት እጥፍ በላይ የሚበልጥ ነው። ከ90 በመቶ በላይ በፈረንሳይ መንግስት የተሸፈነው ፐሮጀክት ሙስና እንደተፈጸመበት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የንፋስ አውታሮች ለሚቆሙባቸው ቦታዎች ...

Read More »

በደቡብ ክልል የመምህራን ተቃውሞ እየተስፋፋ ነው

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል  የመስከረም ወር ደሞዛቸው ያለፈቃዳቸው ተቀንሶ ከተሰጣቸው በሁዋላ የጀመሩት ተቃውሞ እየተስፋፋ መሆኑን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። የጨንጫ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች መምህራን የተቆረጠው ደሞዛችን ካልተመለሰ ስራ አንሰራም በሚል አድማ ከመቱ በሁዋላ፣ በዛሬው እለት ደግሞ በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ” የተቆረጠብን ደመወዝ ...

Read More »