ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ። አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣ ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ ምንጮች:። ሌሎች ዳኞችም ከዋናው ፕሬዘዳንት ...
Read More »አገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ ከውጭ ከሚገኘው ጋር የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ወሰነ
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰሞኑን ሲያደርግ የነበረውን ምልዓተ ጉበኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላም ወደ ፊት እንዲቀጥል እና ቤተክርስቲያን አንድነት እንዲጠናከር ወስኗል። የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ቆጠራ እንዲካሄድና የቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ በደንብ ተጠንቶ እንዲቀርብም ወስኗል። ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወክለው የመጡ ሰዎች በቅርቡ ስለ አክራሪነት የሀይማኖት ...
Read More »አርሶ አደሮች በማዳበሪያ እና በምርጥ ዘር እዳ እየተዋከቡ ነው።
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ እና በአማራ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ውጤታማ ባልሆኑበትና በግዴታ እንዲገዙ በተጠየቁት የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ እዳ እየተዋከቡ ነው። እዳችንን መክፈል አልቻንም የሚሉት አርሶ አደሮች መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል። ግብርና ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የዋለውን ዳፕ የተባለውን ማዳበሪያ ውጤታማ አልሆነም በሚል እንደሚቀይር ማስታወቁ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አርሶአደሮቹ ውጤታማ አልሆነም ...
Read More »ኮሜዲያን አብረሀም አስመላሽ አረፈ
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁም ነገር አዘል በሆኑ ቀልዶቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን አብረሀም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ሲሰቃይ ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አውሮፓ በመምጣት በጀርመን አገር ህክምናውን ተከታትሎአል። አብርሀም በማእደ ኢሳት ዝግጅት ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረዱትን ወገኖች ማመስገኑና ጤናውም መሻሻልእያሳየ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል ፡፡ ከዲስከ መንሸራተት ጋር በጀርመን ሲታከም የቆየው አብራሃም ህመሙ ...
Read More »የስሚንቶ ፋብሪካዎች የገበያ ችግር እንዳጋጠማቸው ተዘገበ
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም። አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል። የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል 209 ብር እየሸጠ፣ ለደንበኞቹ ቤታቸው ...
Read More »የቆዳና ሌጦ አክስፖርት በችግር ላይ ነው
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት የተሻለ ገቢ ያስገኘ ቢሆንም ግብይቱ ኃላቀር፣ሰንሰለቱ የተንዛዛና ከፍተኛ የግብይት ወጪዎች የሚታዩበት እንዲሁም በምርት ጥራት በኣለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርትን በማቆም እሴት የተጨመረባቸውን የተለያዩ የቆዳ ውጤቶች ለውጪ ገበያ በመላክ የተሻለ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ...
Read More »ወደ አዲስ አበባ የሚጎርፉ አረጋውያን ለማኞች ቁጥር ጨምሯል
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በልመና የሚተዳደሩ አረጋውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። አረጋውያኑም ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እንደሚጎርፉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግስት የገጽታ ግንባታ በሚል አረጋውያንን ሰብስቦ ወደ ክልል ቢበትናቸውም፣ አረጋውያኑ ተመልሰው በምጣት በልመናው ቀጥለዋል። አንድ ነዋሪ እንዳሉት ቀድሞ ” አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይለመንም ነበር፣ አሁን ግን ልመናው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ሆኗል፣ ...
Read More »የስኳር ህመምተኞች መድሀኒት የለም ተባሉ
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘውዲቱ ሆስቲታል መድሀኒቱን ለመቀበል ከሳምንታት በላይ ሲጠባበቁ የነበሩ የስኳር ህመምተኞች በመጨረሻ መድሀኒት የለም መባላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠው እርዳታ መቋረጥ ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የችግሩ ምንጭ መድሀኒቱ አየር ባየር ስለሚሸጥ ነው ብለዋል። ህመምተኞች እንደሚሉት መድሀኒቱን በግላቸው ገዝተው ለመጠቀም ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። ብዙዎቹ መድሀኒቱን ለማግኘት ባለመቻላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ...
Read More »ኢትዮጵያዊቷን የማደጎ ልጅ በርሀብ የገደለችው አሜሪካዊት በ37 አመታት እስራት ተቀጣች
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።
Read More »የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል። ደብዳቤው ” ቤተከርስቲያኑ ከተመሰረተ ...
Read More »