ኮሜዲያን አብረሀም አስመላሽ አረፈ

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ቁም ነገር አዘል በሆኑ ቀልዶቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን አብረሀም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ሲሰቃይ ቆይቷል።

ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አውሮፓ በመምጣት በጀርመን አገር ህክምናውን ተከታትሎአል።

አብርሀም በማእደ ኢሳት ዝግጅት ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረዱትን ወገኖች ማመስገኑና ጤናውም መሻሻልእያሳየ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል ፡፡ ከዲስከ መንሸራተት ጋር  በጀርመን ሲታከም የቆየው አብራሃም ህመሙ ጠንቶበት   እስከ ወዲያኛው አሸልቧል ፡፡

የኢሳት ቤተሰቦች በአብረሀም  አስመላሽ ሞት የተሰማቸውን  ልባዊ ሀዘን ለመግለጽ ይወዳሉ።