ወደ አዲስ አበባ የሚጎርፉ አረጋውያን ለማኞች ቁጥር ጨምሯል

ጥቅምት (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በልመና የሚተዳደሩ አረጋውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። አረጋውያኑም ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እንደሚጎርፉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግስት የገጽታ ግንባታ በሚል አረጋውያንን ሰብስቦ ወደ ክልል ቢበትናቸውም፣ አረጋውያኑ ተመልሰው በምጣት በልመናው ቀጥለዋል።

አንድ ነዋሪ እንዳሉት ቀድሞ ” አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይለመንም ነበር፣ አሁን ግን ልመናው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ሆኗል፣ ህዝቡ ጸሎት ማድረስ በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ” ብለዋል፡፡ በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት መባባስ እንዲሁም አረጋውያኑን የሚንከባከብ ድርጅት መጥፋት ለአረጋውያኑ ስደት በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

በችግሩ ዙሪያ የአዲስ አበባን መስተዳድር ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።