ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው። ኢሳት የሚኒስትሩን ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል። በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ...
Read More »በጅጅጋ ለብሄረሰቦች በአል ሲባል ትምህርት ቤቶችና መስሪያ ቤቶች ተዘጉ
ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ/ም ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ጋር በተያያዘ የመንግስት ሥራ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ በከተማዋ በየእለቱ ቤት ለቤትና በጎዳና ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተከናወነ ነው። በጅጅጋ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ከ3ሺ500 በላይ እንግዶችን ታስተናግዳለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እንግዶቹ ከሚያርፉባቸው ቦታዎች አንዱ የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ለአንድ ወር ትምህርት እንደማይኖር በመግለጽ ተማሪዎቹን ማሰናበቱ ታውቋል፡፡ ...
Read More »በሳውድ አረቢያ ምድር በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እና አስገድዶ መድፈር እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን። እሁድ 2 ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው እንደምትገኝ እኝሁ የአይን ምስክር ይገልጻሉ ከዚህ ...
Read More »በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በተቃውሞው ላይ የተገኘችው የኢሳት የደቡብ አፍሪካ ተባባሪ ዘጋቢ ዝናሽ ሀብታሙ እንደገለጸችው በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ታሰትፈዋል። ተቃውሞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ንብረት ጌታሁንም ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ተገኝቶ ስሜቱን በከፍተኛ ሁኔታ ገልጿል ብለዋል በተመሳሳይ ዜናም የአፋር ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የመንግስት 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል ብሎአል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ ...
Read More »የአፍሪካ የካረቢያንና የፓስፊክ አገራት ፓርላማ ጉባዔ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ኅብረት በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ የያዘውን አቋም እንዲደግፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቂያቸውን ለመቀበል አውንታዊ ምላሽ እንደገኙ በመግለጽ አፈጉባኤው ለጋዜጠኞች ቢናገሩም ጉዳዩ ተቀባነት ያገኘው ለውይይት እንጅ ለማጽደቅ አይደለም ተብሎአል። የአፍሪካ የካረቢያንና የፓስፊክ አገራት ፓርላማ 34ኛ መደበኛ ጉባዔ ትላንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በተካሄደበት ወቅት አፈ ጉባዔ አባዱላ ...
Read More »በጎንደር ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪ አንተነህ አስፋው የተገደለው በዩኒቨርስቲው የጸጥታ ሀይሎች መሆኑ ታውቋል። ይህን ለመቃወም የወጡ በሺ በሚቆጠሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ120 በላይ ተማሪዎች እንደታሰሩ ታውቋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ከፉኛ በመደብደባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፣ የአንድ ተማሪ ህይወትም በአሳሳቢ ሁኔታ ላኢ እንደሚገኝ ታውቋል።
Read More »የታላቁ ሩጫ ውድድር በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃና አጀብ ተካሄደ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታላቁ ሩጫ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ሥር ሆኖ እሁድ ህዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ መነሻውን ጃንሜዳ በማድረግ ፥ በ6 ኪሎ አደባባይ ፣ በምኒሊክ ሆስፒታል፣ በቀበና ፣በ አቧሬ ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ ፣ በመገናኛ አደባባይ በማደረግ ተመልሶ ጃንሜዳ የተጠናቀቀው ይህ ለ 13ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር ከወትሮው በተለየ ጥበቃና የፖሊስ ተደጋጋሚ ፍተሻ በመታጀብ ነበር፡፡ ቅዳሜ ...
Read More »መንግስት ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያንን ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው።
ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያዊያን በአስከፊ ሁኔታ እንዲባረሩ ከተደረገ በኃላ መንግስት በሳዑዲ ስፖንሰርነት ያጓጓዛቸውን ከ10ሺ በላይ ተመላሾች በካድሬዎች ማሰልጠኛ በሆነው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በማሳረፍ ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለተመላሾቹ ማቋቋሚያ መንግስት 50 ሚሊየን ብር መመደቡን፣ ገንዘቡ ሊያድግ እንደሚችልና በማቋቋም ረገድ ችግር እንደሌለ ከገለጹ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ...
Read More »በቡራዩ ቤቶችን ማፍረስ ቀጥሎአል
ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር ትናንትና ዛሬ በቡራዩ አካባቢ ከ1 ሺ ያላነሱ ቤቶችን ማፍረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች እንደሚናገሩት መስተዳድሩ ምንም አይነት መጠለያ ሳያዘጋጅ እና ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እስከ ሙሉ የቤት እቃዎቻቸው ቤቶቻቸውን በድንገት በማፍረሱ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል። አለማየሁ የተባለ አንድ ወጣት የወላጆቹ ቤት ሲፈርስ በማየቱ ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት፣ በህይወቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲሞክር ...
Read More »