ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ...
Read More »የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በውጭ ስርአቱ ጥሩ ነው ይበሉ እንጅ በግል ሳናግራቸው ለውጥ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል ሲሉ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ተናገሩ
ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያን የ1997 ምርጫ የታዘቡት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት አዲስ ስታንዳርድ ለተባለ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ነው። በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮፓ፣ አፍሪካና ካረቢያን አገሮች የፓርላማ ጉባኤ ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና የአምባገነን ምንጭ የሆነው መለስ ዜናዊ ቢሞትም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ተለውጣለች በማለት በአደባባይ የሚናገሩት ባለስልጣናት በግል ...
Read More »በሳውድ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት ስትርሀ እየተባሉ በሚጠሩ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ። በውሀ እና በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እርጉዝ ሴቶች፣ ህጻናትና እናቶች አሁንም የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊን ምግብ እና ውሀ ለመግዛት ወጣ ሲሉ እንደሚገደሉ ጓደኞቻቸው የተገደሉባቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል የኢሳት የአዲስ አበባው ዘጋቢ ...
Read More »በጅማ ዞን አንድ ቻይናዊ ተገደለ
ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግለሰቡ የተገደለው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ገዳዮችም ከመንግስት ጋር ባላቸው ቅራኔ የተነሳ ጫካ የገቡ ሰዎች ናቸው ተብሎአል። ከአካባቢው ነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት በጅማ ዞን ኪሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በለጣ ጫካ ውስጥ በመደበቅ አልፎ አልፎ ጥቃት የሚሰነዝሩ የአኮረፉ ነዋሪዎች ቻይናዊውን የገደሉት ፎቶ ግራፍ ለማንሳት በሚሞክረበት ወቅት ነው። ቻይናዊው የመንገድ ሰራተኛ ግለሰቦችን በጫካ ውስጥ ...
Read More »ውድ ተመልካቾች ዜና እርማት አለን
ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ጅጅጋን በማስመልከት በተላለፉ ዜናዎች ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች እንድናደርግ የከተማዋ ነዋሪዎች ጠይቀውናል። ኢሳት በብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ እንደተዘጋ አድርጎ ያስተላለፈው ዜና ስህተት ያለበት ሲሆን የተዘጉት የጅጅጋ ነርሲንግ ማሰልጠኛኮሌጅ እና የጅጅጋ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም እንጅ ዩኒቨርስቲው አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። የአቶ መለስ ዜናዊ ሀውልት እንደፈረሰ ተደርጎ በቀረበው ዜናም ላይ ስህተት ያለ ሲሆን፣ ...
Read More »ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ
ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን መዲናህ ከተባለው መጠለያቸው ግንብ እየዘለሉ ወደ ታይባን ዩኒቨርስቲ ካምፓስ እንደገቡ የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ብርጋዴር ፋህድ ቢን አሚር አል ጋናም እንደገለጹት 15 ኢትዮጵያውያን ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ የገቡ ሲሆን የጸጥታ ሀይሎች ኢትዮጵያውያኑን በመያዝ ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ልከዋቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በሰዎች፣ በመኪኖች ወይም ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሱ የሳውዲ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡ ...
Read More »በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ
ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው። ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል። ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም በመገንባት ላይ የተጠመደው ክልሉ ፤ ...
Read More »የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በታችኛው ኦሞ የተፈጠረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚመረምር አስታወቀ
ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ አካል ነው የተባለው ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት በሚል በታችኛው ኦሞ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን በማፈናቀል እየፈጸመችው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጥነት እንድታቆም ጠይቆ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግም ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚኖሩ ብሄረሰቦች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና እስራት መፍጠሩን የመለከተው ኮሚሽኑ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ...
Read More »‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡
ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ ...
Read More »በሳውድ አረቢያ ምድር የእናቶችና የህጻናት ለቅሶ ቀጥሎአል።
ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ከሪያድ ወደ አዲስ አበባ ትሄዳላችሁ ተብለው በመኪኖች የተሳፈሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችና ህጻናት በድንገት ጉዞዓቸው መሰረዙን ተከትሎ፣ በርካታ እናቶችና ህጻናት ለከፍተኛ የውሀ ጥም በመዳረጋቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው። እናቶች እና ህጻናት ተስፋ በቆረጠ ስሜት ያለቅሳሉ፤ ማለቃችን ነው ድረሱልን ሲሉ ይማጸናሉ። ህጻናቱና እናቶች አስፋልት ላይ ተበትነው በውሀ ጥም ማለቃቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ኢሳት በቀጥታ ከስደተኞች ...
Read More »