ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ጽህፈት ቤት ፖሊስ አዛዥ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ በምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት እንዳልደረሰቻው ገልጸዋል። አዛዡ እንዳሉት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሽብረተኞችን በተመለከተ ከፌደራል መንገስቱ የጸረ ሽብር ግብረሀይል ጋር በጋራ የሚሰሩ በመሆኑ፣ በዚሁ ወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ካሉ በጋራ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል ሲሉ አክለዋል በጅጅጋ የተከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ...
Read More »ገዢው ፓርቲ የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ወደ ቤተሰብ አወረደ
ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ በትምህርት ቤቶች ፣ በአርሶ አደሩና በከተማው ነዋሪዎች ላይ ሲዘረጋ የቆየውን የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በቤተሰብ ደረጃ ለማዋቀር የተለያዩ ደብደባዎችን እየበተነ ነው። የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለወረዳ 02 የቤተሰብ አባላት ባዘጋጀው የቤተሰብ ማቋቋሚያ ቅጽ ላይ የቤተሰብ ፖሊስ መመስረት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ” በቤተሰብዎ መካከል ለሚፈጠሩ የጸጥታ ...
Read More »በአዳማ ከ25 ሺ ያላነሰ ህዝብ በቤት መፍረስ ምክንያት መንገድ ላይ መውደቁ ተገለጸ
ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል ያላቸውን በመልካ አባገዳ አካባቢ የሚገኙ ቤቶችን ካለፈው ቅዳሜ ሌሊት ጀምሮ ህዝቡ ቤቱ ውስጥ እንዳለ ማፍረሳቸው ታውቋል። በርካታ ቤተሰቦች መንገድ ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት የገለጹት አንድ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪ፣ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቤቶች በፈቃዳችን እንደፈረሱ አድርገው የሚያቀርቡት ዘገባ ሀሰት ነው ብለዋል። የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም ተባለ
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም መንግስት እስካሁን እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ ታወቀ። የኢሳት የጁባ ወኪል እንደገለጹት አብዛኛው አገሮች ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው ። ኬንያና ኡጋንዳ አውቶቡሶችን በመላክ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን በመላክ ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ጁባ ...
Read More »ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከፍትህ አካላት ትብብር አጣሁ አለ
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ስራዎች የሚገልጽ ” የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከትናንት እስከ ዛሬ ” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አዘጋጅቶ አውጥቷል። ዘጋቢያችን እንደገለጸው በተሻሻለው የፀረ-ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 29 መሰረት በሙስና ወንጀል ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በሙስና ወንጀል የተገኘ ተመጣጣኝ ንብረት እንዲወረስ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይሰጣል ቢልም ፍርድ በቶች ...
Read More »ከሚኒስትርነት ወርደው በአምባሳደርነት መሾማቸውን አያውቁም ነበር ተባለ
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማዕድን ሚኒስትር በመሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉትት ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከ16 ዓመታት በላይ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ ከኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትር ዴኤታ ባሉት የሀላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዩትና እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር 2010 የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያየ አደረጃጀት ይዞ ለሁለት ሲከፈል ...
Read More »የደቡብ አፍሪካ ታላቁ የሰራተኛ ማህበር ለገዢው ፓርቲ ድጋፍ እንደማያደርግ አስታወቀ
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ300 ሺ በላይ አባላት ያሉት የደቡብ አፍሪካ የሜታል ሰራተኞች ማህበር ደቡብ አፍሪካ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ በስልጣን ላይ ያለውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሲደግፍ ቆይቷል። ማህበሩ ለማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ድጋፉን እንደማይሰጥም አስታውቋል። የፕሬዚዳንት ዙማ መንግስት ሙስናንና ድህነትን በመዋጋት በኩል በቂ ስራ አልሰራም በሚል እየተተቸ ነው። የሰራተኛው ማህበር ከታዋቂው ነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ...
Read More »በጅጅጋ ከተማ ታቆሽሻላችሁ ተብለው ከታሰሩት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-9ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ከተማ ያቆሽሻሉ ተብለው ተይዘው ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ ከምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በመሞታቸው በታሰሩበት አካባቢ እንዲቀበሩ ተደርጓል። ሟቾቹ በደንብ ባለመቀበራቸውና የአንዳንዶችን አስከሬን ጅብ አውጥቶ ስለበላው፣ ሌሎቹ ከእስር ቤቱ ራቅ ብለው በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ኢሳት ከክልሉ ...
Read More »የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ከስልጣን ተነሱ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልልን ላለፉት ስምንት ዓመታት ተኩል በፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አያሌው ጎበዜ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ በምትካቸው ምክትል ፕሬዚደንቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተሹመዋል፡፡ አቶ አያሌው ከኃላፊነታቸው የተነሱት እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዙር ፤ አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቶ አያሌው መውረድና በአቶ አንዳርጋቸው መተካት ...
Read More »በጉንዶ መስቀል በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩ ባለስልጣናት ምርመራ ተካሄደባቸው
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በጉንዶመስቀል ከተማ በመስተዳድሩ ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩት መካከል ከ108 በላይ ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች የተለያዩ የሃለፊነት ቦታዎችን ወስደዋል በሚል የአካባቢው ፖሊስ ምርመራ በማድረግ ላይ ነው። ፖሊስ እስካሁን ባደረገው ምርመራ 13 ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥረው ለአመታት ደሞዝ ሲቀበሉ መቆየታቸውን በማረጋገጥ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መርቶታል። በቀሪዎቹ ...
Read More »