በአዳማ ከ25 ሺ ያላነሰ ህዝብ በቤት መፍረስ ምክንያት መንገድ ላይ መውደቁ ተገለጸ

፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :- መንግስት በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል ያላቸውን በመልካ አባገዳ አካባቢ የሚገኙ ቤቶችን ካለፈው ቅዳሜ ሌሊት ጀምሮ ህዝቡ ቤቱ ውስጥ እንዳለ ማፍረሳቸው ታውቋል።

በርካታ ቤተሰቦች መንገድ ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት የገለጹት አንድ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪ፣  የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቤቶች በፈቃዳችን እንደፈረሱ አድርገው የሚያቀርቡት ዘገባ ሀሰት ነው ብለዋል። የሁለት  ልጆች እናት የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው ” ቤታችን በላያችን ላይ ፈርሷል፣ ቤት መከራየትም አልቻልም፣ ኦሮሚያ ውስጥ ሰሚ የለም፣ ህግ የለም፣ ለመንግስት ኢትዮጵያዊ አይደለንም” ብለዋል። ሌሎች ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎችም በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን አድልዎ በዝርዝር ገልጸዋል።