በኢትዩጵያ በከተሞች አካባቢ ያሉ የገፀ ምድር ውኃ ከፍተኛ ብክለት እንዳለባቸው ምሁራን ገለጹ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩነቨርሲቲ የሥነ ምድር ትምህርት ክፍል የከርሰ ምድር ውኃን በተለያዩ መንገዶች  ሲያጠኑ የቆዩ አንድ ምሁር ባወጡት ጽሁፍ  አብዛኛው የአዲስ አበባ ወንዞች  ለመጠጥም፣ ለእርሻም፣ ለኢንዱስትሪም መዋል የሚችል አይደለም። በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ  አዋሽ፣ ቦረከናና ሌሎች ወንዞች ከኢንዱስትሪዎችና ከከተሞች በሚወጡ ቆሻሻዎች መበከላቸው ተመልክቷል፡፡ ከሽንት ቤት ጉድጓዶች የሚወጡ ፍሳሾች፣  ከኢንዱስትሪዎች የሚወጡ ኬሚካሎችና የሳሙና እጣቢዎች ...

Read More »

የአባይ ግድብ በተያዘለት እቅድ መሰረት ያለምንም ችግር እየተከናወነ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ይህን የተናገሩት አንድ የግብጽ ጋዜጣ የአገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣን በመጥቀስ የዘገበውን ዜና ተከትሎ ነው። ጋዜጣው ፣ ኢትዮጵያ ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል በማሰብ ግድቡ 30 በመቶ እንደተጠናቀቀ እያስወራች መሆኑዋንና ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማት” መዘገቡ ይታወቃል። የአባይ ግድብ ግንባታ የገንዘብም ሆነ የቴክኒክ ችግር አላጋጠመውም ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተያዘለት የጊዜ ገደብም እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች ድርድራቸውን ጀመሩ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተቋርጦ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ዛሬ በጋዝ ላይ የምሽት ክበብ ውስት መጀመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። ቀደም ብሎ በሸራተን አዲስ የነበረው የድርድር ቦታ የተቀየረው ቦታውን አትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የጃፓኑ ጠ/ሚኒስትር ሾኒዝ አቤ በመያዛቸው ነው። ድርድሩ በምሽት ክለብ ውስጥ መሆኑ አንዳንድ ተደራዳሪዎችን አላስደሰተም። በቤቱ ውስጥ የሚሰማው ጫጫታ እንደረበሻቸው እነዚሁ ልኡካን ገልጸዋል። ድርድሩ ...

Read More »

የሰሜን ጎንደር የእስር ቤት አዛዥ ተገደሉ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢዎች ከጎንደር እንደገለጹት ኮማንደር አለባቸው የተባሉት የሰሜን ጎንደር ዞን የወይኔ ቤት አዛዥ የተገደሉት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ነው። ኮማንደሩ በጥይት መመታታቸው ቢገለጽም ዘጋቢያችን ማን እንደገደላቸው ለማወቅ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። የግለሰቡ አስከሬን ወደ ተወለዱበት በየዳ ወረዳ መላኩ ታውቋል። አወጋን እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል። ድርጅቱ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ባወጣው መረጃ ” ...

Read More »

ነጋዴዎች ቦንድ እንዲገዙ እየተገደዱ ነው

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወልድያ የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ለኢሳት እንደገለጹት  ፈቃድ ለማሳደስ በሚሄዱበት ጊዜ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ካልገዛችሁ አይታደስላችሁም ተብለዋል። የግል ክሊኒኮችን ከፍተው የሚሰሩ ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ በሚሄዱበት ጊዜ ከ2ሺ ብር ጀምሮ ቦንድ እንዲገዙ ተገደዋል። የኢህአዴግ ካድሬዎች በየቀበሌው እየዞሩ ነጋዴዎች ቦንድ እንዲገዙ ያለበለዚያ የንግድ ፈቃዳቸው እንደማይታደስላቸው እያስጠነቀቁ ነው። እድሮችና  እቁቦችም በተመሳሳይ መንገድ ቦንድ እንዲገዙ ...

Read More »

በኦሮሚያ ካሉ ከ2 መቶ በላይ የአበባ ልማት ባለሃብቶች የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማረጋገጫ የወሰዱት ከ10 አይበልጡም ተባለ፡፡

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሚያ የአካባቢ ጥበቃ የአካባቢ ተፅዕኖና ግምገማ መምሪያ ኃላፊ አቶ አሕመድ ሁሴን በኦሮሚያ ክልል አካባቢን ለመጠበቅ እየተደረጉ ስላሉ እንቅስቃሴዎችና አካባቢን በማይጠብቁት ላይ ምን ዓይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት እንዲሁም ስለተወሰዱ እርምጃዎች እንደገለጹት፣  በኦሮሚያ ክልል ከአካባቢ ተፅዕኖ ጋር የሚነሱ ችግሮች በክልሉ በሚካሄዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የተነሳ በአካባቢ ላይ ጉዳት ይደርሳሉ፡፡ ይህንን ጉዳት ለመቀነስ አንድ ፕሮጀክት ከመተግበሩ ...

Read More »

ባለፉት ሶስት ኣመታት በሠፈራ ፕሮግራም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ በአራት ክልሎች እንዲሰባሰብ መደረጉን ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003-2005 ዓ.ም መንግስት መንደር ማሰባሰብ በሚል በሚጠራው የሠፈራ ፕሮግራም በጋምቤላ በ12 ወረዳዎች 38 ሺ፣በቤንሻንጉል ጉሙዝ በ18 ወረዳዎች 77 ሺ ፣በአፋር በ8 ወረዳዎች 10ሺ፣ በሶማሌ በ21 ወረዳዎች 150 ሺ አባወራና እማወራዎች በድምሩ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሕዝብ እንዲሰፍር ተደርጓል፡፡ እስከ2007 የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ማጠናቀቂያ ድረስ 85ሺ ቤተሰብ ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ተብሎአል፡፡ በመንደሩ ያልተሰባሰቡ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን መንግስት ቤንቲዩ የምትባለዋን የነዳጅ ከተማ መቆጣጠሩን አስታወቀ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገሪቱ ጦር ሀይሎች ቃል አቀባይ እንደገለጹት አማጽያኑ የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶች የሚገኙባትን ቤንቲዩን ለቀው የወጡት እኩለ ቀን ላይ ነው። የደቡብ ሱዳን መንግስት አካባቢውን መቆጣጠሩን ቢገልጽም፣ በአማጽያኑ በኩል የተሰጠ ምንም አይነት ምላሽ የለም። መንግስት የነዳጅ ከተማዋን መቆጣጠሩ አማጽያን በመንግስት የቀረበውን ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ይገደዱ ይሆናል የሚል አስተያየቶች ቀርበዋል። በኢትዮጵያ መንግስትና በኢጋድ አባል አገራት ሲደረግ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ ሀሳቡን በኢሳት ላይ ለመግለጽ የማንንም ይሁንታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ” የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም” በሚል ርእስ ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ ” ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ ” አድርጓል። “በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ...

Read More »

ከሳውድ አረቢያ የተባረሩ ዜጎች በችግር ላይ መሆናቸው ታወቀ

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ከ150 ሺ በላይ ተመላሽ ዜጎችን ወደ ተወለዱበት ቀየ መልሶ በመላክ በአነስተኛ እና ጥቃቅን በማደራጀት የስራ እድል እንደሚፈጥር ቢያስታውቅም፣ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በሁዋላ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው ታውቋል። ሰሜን ሸዋ አካባቢ በርካታ ስደተኞች መመለሳቸውን የገለጹት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አንድ ሰው፣ ተመላሾቹ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ትደራጃላችሁ በሚል ተስፋ ቢመጡም፣ ቃል የተገባላቸው ነገር ባለመፈጸሙ ...

Read More »