ከ20 ቀናት በፊት በድንገት ከኃላፊነታቸው የተነሱት የማዕድን ሚኒስትር ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ በምክትላቸው አቶ ቶሎሳ ሻጊ ተተኩ፡፡

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርላማው በጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፊርማ የቀረበለትን ዕጩ ሚኒስትር አቶ ቶሎሳ ሻጊ ሞቲን ሹመት ተቀብሎ አጽድቆአል፡፡ አቶ ቶሎሳ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩ ሲሆን ከማዕድን ጋር ተያያዥ በሆኑ ስራዎች ከ20 ኣመታት በላይ አገልግለዋል፡፡ ከ16 ዓመታት በላይ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ ከኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትር ዴኤታ ባሉት የኃላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዩትና ...

Read More »

ከ100 ሺ በላይ የሚሆኑ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የብቃት ምዘና ፈተናውን ማለፍ ሳይችሉ ቀሩ

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-10ኛ ክፍልን እንዳጠናቀቁ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት ያልቻሉ ታዳጊ ወጣቶች  መሰረተ ልማት ባልተሟላበት ፤ የኮምፒዩተር አቅርቦት በሌለበት ፤ የተሰናዳ የትምህርት ክፍል፣ ወንበር እና የማሰተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች ሳይሟሉ እና ከተግባር መሳሪያዎች ጋር በደንብ ሳይተዋወቁ ተምረው ለምረቃ ይበቃሉ፡፡ በየአመቱ ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የሚመክኑበት ይህ የትምህርት ዘርፍ አላማው ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት ቢሆንም ውጤታማ ሊሆን ...

Read More »

መቀሌ በውሃ ጥም ውስጥ ናት

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ መቀሌ በውሃ ጥም እየተመታች መሆኑዋን ኗሪዎቿ ተናገሩ፡፡ ላለፉት አራት ወራት በሳንምንት አንድ ቀን በወረፋ የምትደረሰው ውሃ ሌሊቱን ሁሉ ስትጠበቅ ታድራለች፣ እንደነዋሪዎች አነጋገር። ከተማ አሰተዳደሩ በበኩሉ ከእርዳታ ድርጅቶች በቂ ገንዘብ በማፈላለግ  በሚቀጥለው አመት የውሃ አቅርቦቱን ለማሻሻል እንሰራለን ብሎአል፡፡ አስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸው የዕርዳታ ድርጅቶችን  ከመጠበቅ ለትሃድሶ እያለ ለግብዣ ከሚያወጣው በመቆጠብ ማሰራት እንደሚቻል ...

Read More »

አዋሳ አየር ማረፊያ ሊሰራላት ነው

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋና እንደዘገበው ከተማዋን የሚጎበኙ ቱሪስቶች መጨመራቸውን ተከትሎ በከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማሰራት እድቅ ተይዟል። የኤርፖርቶች ድርጅት የግንባታ መሬት ከአዋሳ መስተዳደር መረከቡን በመግለጽ በአንድ ሚሊዮን ብር የዲዛይን ስራው እንደሚሰራና በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጿል። አዋሳ ከአዲስ አበባ በ270 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን በአለፈው የፈረንጆች አመት ከ600 ሺ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ጎብኝተዋታል።

Read More »

አንድነት ፓርቲ ለሚዲያዎች ሃሳብን መግለጽ አሸባሪነት አይደለም አለ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን ኢቲቪ ባዘጋጀው ዶክመንተሪ ላይ “መቀመጫውን በውጭ በማድረግ የተለያዩ ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን በማሰራጨት የሚታወቀውን ኢሳት(ESAT) ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ፓርቲያችን ለአባላቱ እና ለደጋፊዎቹ መልዕክት ማስተላለፉን እንዲሁም እንደፓርቲ ለማንኛውም ሚዲያ የፓርቲያችንን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ስንጠየቅ የመመለስ መብታችንን በሚጋፋ መልኩ የፓርቲያችንን አቋም አዛብቶ ለማቅረብ ሞክሯል” ብሎአል፡፡ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ተወካዮች ብሶታቸውን ለመንግስት ባለስልጣናት ቢያቀርቡም መልስ እንዳላገኙ ተዘገበ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ ጋዜጣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የመሩትን ስብሰባ በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን፣ ከጋዜጣው ለመረዳት እንደተቻለው ሰራተኛው በሚያነሳቸው ቅሬታዎችና መንግስት በሰጣቸው መልሶች መካከል ከፍተና ክፍተት አለ። የሰራተኞቹ ተወካዮች የሰራተኛው የመደራጀት መብት እንዳልተከበረና ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደሚጣስ ገልጸዋል። የሰራተኛው የመደራጀት መብት ሲጣስም በመንግስት በኩል አርኪ ምላሽ አይሰጥም ብለዋል። ተወካዮቹ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ባለመቻላቸው መንግስት ድጎማ ...

Read More »

የመንግስት የፕሬስ ተቋማት የግል መጽሄቶችን በጽንፈኝነት ፈረጁ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በሕግ በፈረሰ ድርጅት ስም የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በጋራ አስጠንተነዋል ባሉት ጥናት መሰረት በአገር ውስጥ ከሚታሙት መጽሄቶች መካከል አዲስ ጉዳይ፣ፋክት፣ሎሚ፣ቆንጆ፣ጃና፣እንቁ እና ሊያ የተባሉ መጽሔቶች ጽንፈኛ ፖለቲካ አራማጆች መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል። አዲስዘመን ጋዜጣ በረቡዕ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዕትሙ መጽሔቶቹ በብዙ ባህርያቸው የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳናት ...

Read More »

በቦረናና በቡርጂዎች መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ የመንግስት ባለስልጣናት መንቀሳቀሳቸው ተሰማ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በማቅናት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው። ይህንንም ተከትሎ በዛሬው እለት አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካባቢያቸውን ጥለው የወጡት የቡርጂ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው ባይመለሱም ፣ እስከ ትናንት የነበረው ግጭት በዛሬው እለት መብረዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዞኑ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል ...

Read More »

ተስፋ የተጣለበት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዶ የነበረው የሰላም ድርድር ውጤት ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ፣ የመንግስት ሀይሎች ቤንቲዩ እየተባለች የምትጠራውን የነዳጅ ዘይት የሚገኝበትን ቦታ ለመቆጣጠር ጥቃት መጀመራቸው በሰላም ስምምነቱ ላይ ያለው ተስፋ እንዲጨልም አድርጎታል። የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተቀናቃኝ የሆኑት ሪክ ማቻር ደጋፊዎች ካልተፈቱ የሰላም ስምምነት ለመፈራረም እንደሚቸገሩ አማጺያኑ ቢገልጹም መንግስት ግን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የአደገኛ እጾች ተጠቃሚ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ

ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአደገኛ እጾች ተጠቃሚ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ በህጻናት እና በሴቶች ላይ የሚደረሰውም ጉዳት ጨምሯል። የተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት ሰንደቅ ጋዜጣ በስፋት ዘግቦታል። በኢትዮጵያ በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ 543 ሺ 439 ኪሎ ግራም ወይም 5 ሺ ...

Read More »