(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) በቅርቡ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት አቶ ታደሰ ካሳ በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው እንዲከሰሱ ከተወሰነ በኋላ ሂደቱ በእጅ አዙር እንዲቋረጥ ተደርጎ መቆየቱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። አቶ ታደሰ ካሳ ወይንም ታደሰ ጥንቅሹ በመባል የሚታወቁት የብአዴን መስራች የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም/አብቁተ/ን ሲመሩ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ለሞቱ ቤተሰቦች ካሳ ተከፍሏል በሚል ያለ ማወራረጃ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸው በኦዲት ...
Read More »ኦህዴድ ስያሜውን ቀየረ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011)ኦህዴድ ስያሜውን መቀየሩና ከ10 በላይ የሚሆኑ ነባር የፓርቲውን አባላት በክብር ማሰናበቱ ተገለጸ። በጅማ እየተካሄደ ባለው 9ኛ የድርጅቱ ጉባኤ ላይ ኦህዴድ ስያሜውን በመቀየር የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ተብሏል። ፓርቲው ከነባር የፓርቲው አባላት አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከ10 በላይ የሚሆኑ አባላቱን በክብር አሰናብቷል። ከነዚህም ውስጥ አቶ ሱለይማን ደደፎ ፣አቶ ድሪባ ኩማ ፣አቶ ጌታቸው በዳኔ፣ አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ ...
Read More »ለቡራዪ ተፈናቃዮች በ72 ሰዓት ውስጥ ከ265 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) በአርቲስት ታማኝ በየነ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በተከፈተ የጎ ፈንድ ሚ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለቡራዪ ተፈናቃዮች በ72 ሰአት ውስጥ ወደ ከ265ሺህ ዶላር የሚጠራ ገንዘብ ተሰበሰበ። አዘጋጆቹ እስከ 500ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ማቀዳቸውን በመግለጽ ኢትዮጵያውያን ለወገናቸው ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አድርገዋል። በተያያዘ ዜና ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ዜጎች አንድ ሚሊየን ብር መስጠቱ ታውቋል። ቴዲ አፍሮ ...
Read More »በቡራዩና አካባቢዋ 58 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) በቡራዩና አካባቢዋ በተከሰተው ግጭት 58 ሰዎች መገደላቸውን አምንስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ አደረገ። አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን በመጥቀስ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ከአርብ እስከ ሰኞ ባሉት ቀናት ውስጥ የ58 ሰዎች አስከሬን ታይቷል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪና ሪፖርት አጠናቃሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ከናይሮቢ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል ለፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት ኤ ኤፍ ፒ በሰጡት መግለጫ ግድያው በዱላና በድንጋይ ...
Read More »ኦህዴድ ነባር አመራሮችን አሰናበተ
ኦህዴድ ነባር አመራሮችን አሰናበተ ( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኦህዴድ መስራቾችና የህወሃት ደጋፊዎች ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጌታቸው በዳኔ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ግርማ ብሩ፣ እሸቱ ደሴ፣ ተፈሪ ጥያሩ፣ ደግፌ ቡላ፣ አበራ ሃይሉ፣ ሱሌይማን ደደፎ፣ ኢተፋ ቶላ፣ ዳኛቸው ሽፈራውና ጊፍቲ አባሲያ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል። ፓርቲው ራሱን ከኦህዴድ ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወይም ኦዴፓ ቀይሯል። በጅማ እየተካሄደ ባለው የድርጅቱ ...
Read More »ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ
ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ ( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በቡራዮ ከተማ ለደረስው አስከፊ ጭፍጨፋ ስለባ ለሆኑ ወገኖቻችን የገንዘብ ማስባስብ ዘመቻ ጀምሯል። የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የሰብ ዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ ጉዳተኞቹን ስፍራው ድረስ በመሄድ ከጎበኙ በኋላ ጎፈንድ አካውንት በመክፈት በአፋጣኝ ዜጎችን ለመታደግ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻውን አስጀምረዋል። ...
Read More »ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011)የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አመራሮች ጋር አስመራ ላይ ተወያዩ። ከኦብነግ ጋር በሚደረገው የሰላም ንግግር አካሔድ ላይ መወያየታቸውም ተመልክቷል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊና የሶማሌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/ሶሕዴፓ/ ሊቀመንበር በአቶ አሕመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት የልኡካን ቡድን፣ከአድሚራል ወይንም ጄኔራል ሞሐመድ ኦማር ከተመራው የኦነግ ልኡካን ቡድን ጋር የተወያዩት አስመራ ውስጥ መሆኑም ታውቋል። አስመራ ውስጥ ትላንት በተካሄደው ...
Read More »ኢትዮጵያና ኤርትራ የተፈራረሙት ባለ ሰባት አንቀጽ ስምምነት ይፋ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የተፈራረሙት ባለ ሰባት አንቀጽ ስምምነት ይፋ ሆነ። ባለፈው ሳምንት በሳውዳረቢያ ጅዳ ሁለቱ መሪዎች በፈረሙት ስምምነት መሰረት በጸጥታና መከላከያ እንዲሁም በንግድና በኢንቨስትመንት መስክ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። በባህልና በማህበራዊ ጉዳዮች ጭምር በትብብር ለመስራት ፊርማቸውን ያኖሩት ሁለቱ መሪዎች በጋራ ኢንቨስትመንት ለመሰማራትና የጋራ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመፍጠር መስማማታቸው ተመልክቷል። የጦርነቱ ዘመን አክትሞ የሰላም ዘመን ...
Read More »የመንጋ ፍትህና ስርአት አልበኝነት እየተስፋፋ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) የመንጋ ፍትህና ስርአት አልበኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አሳሰበ። የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በቡራዪ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ጨምሮ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ርምጃዎች አሳሳቢ መሆናቸውንም አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸው ሐገሪቱ ተጋርጦባት የነበረውን አደጋ ያስታገሰና የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ነው ሲልም ሰመጉ አስታውቋል። ነሐሴ 9/2010 በደቡብ ክልል ሰካ ዞን ብሔርን መሰረት ባደረገ ...
Read More »ኢትዮጵያን ከመገንባቱ ሂደት ማንም ሃይል ሊያስቆመን አይችልም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) ኢትዮጵያን ከመገንባቱ ሂደት ማንም ሃይል ሊያስቆመን አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። ኢትዮጵያንም አፍሪካንም እንገነባለን ያሉት ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ህልውና እንዲቀጥል ኦሮሞዎች ሃላፊነት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። በጅማ ዛሬ በተጀመረው የኦህዴድ 9ኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞን ትግል ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ካላችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም ...
Read More »