ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከክልሉ ውሃ ልማት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የሃረር ከተማን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በሚል በተለያዩ ወቅቶች ከ747 ሚሊዮን 175 ሺ ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አብዛኛው ፕሮጀክቶች በመክሰማቸው የከተማው ህዝብ ለአሳሳቢ የውሃ ችግር ተዳርጓል። የከተማውን የውሃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተጣለበት የሃሰሊሶ መስመር መጠናቀቁን ተከትሎ ለምረቃ የተዘጋጀው መጽሄት ” ውሃ በፈረቃ ድሮ ቀረ!” በሚል ...
Read More »የደሞዝ ጭማሪ እንደሚኖር መነገሩን ተከትሎ የእቃዎች ዋጋ ወደ ላይ እየወጣ ነው
ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሃምሌ ወር መጨረሻ የደሞዝ ጭማሪ ይኖራል በማለት ከተናገሩ በሁዋላ ደሞዙ ሳይለቀቅ፣ የቤት ኪራይ እንዲሁም የምግብ እና የአላቂ እቃዎች ዋጋ ጭማሬ እያሳየ ነው። ጭማሪው በመላ አገሪቱ የሚታይ ሲሆን በአንዳንድ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ እየታየ ነው። መንግስት ስለጭማሪው ተጨማሪ ማብራሪያ ባይሰጥም፣ ነጋዴውና ቤት አከራዮች ጭማሪ በማድረጋቸው የደሞዙን ጭማሪ ለማየት በሚጓጓው ...
Read More »የኦሮምያ ክልል ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች አባረረ
ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ 17 ጋዜጠኞች ከስራ መባረራቸው ተገልጾላቸዋል። ጋዜጠኞች የተባረሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይታወቅም፣ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ተቃውሞ እንዲሁም ባህርዳር ላይ ተደርጎ ከነበረው የስፖርት ዝግጅት የቀጥታ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ቀድም ብሎ ውስጣዊ ግምገማዎች ሲካሄዱ እንደነበር የኢሳት የመረጃ ምንጮች ጠቁመው፣ 6 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ቀደም ብለው እንዲታገዱ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበርኞች ግንባር ሰራዊት በወልቃይት ድል መቀዳጀቱን ገለጸ
ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 16፣ 2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ በስርዓቱ የሚሊሻ ታጣቂ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ 18 ገድሎ ቻለው ሲሳይ እና ተጫነንጉሱ የተባሉ 2 ወታደሮችን መማረኩን አስታውቋል። ሰራዊቱ ለሁለቱም ምርኮኞች ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለድርጅቱ አላማና ግብ በማስተማር እንደለቀቃቸውም ድርጅቱ ገልጿል። ሰኔ 18-2006 ዓ/ም ደግሞ የኢሕአግሰራዊት ከመንግስት የልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በወልቃይት አወርቂ በተባለ ቦታ ከጠዋቱ ...
Read More »የእህል ንግድ ድርጅት ከ6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለገባያ ሊያቀርብ ነው
ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋገት በማሰብ ስንዴ የማከፋፈሉ እንቅስቃሴ እንደሚቀጥል ድርጅቱ አስታውቋል። ከሚከፋፈለው 6 ሚሊዮን 500 ሺ ኩንታል ውስጥ 6 ሚሊዮን ኩንታል ከውጭ አገራት ከ700 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ወጪ ወጥቶበት የተገዛ ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በግንቦት20 በአል ላይ ኢትዮጵያ በምግብ ምርት ራሱዋን ችላለች ብለው መናገራቸው ይታወቃል።
Read More »አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል። የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣ እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ...
Read More »ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ...
Read More »በአዋሳ የታሰሩ የአንድነት አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህገወጥ ቅስቀሳ አድርጋችሁዋላ በሚል የታሰሩት የአንድነት አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ5 ሺ ብር ዋስትና እንዲያስይዙ እና እንዲፈቱ ተጠይቀዋል። የቀጠሮ ጊዜያቸው የፊታችን አርብ ቢሆንም፣ እስረኞቹ ያለቀጠሮ እንዲቀርቡ ተደርጎ ያዋስትና መብት ተፈቅዶላቸዋል። ባለፈው ሰኞ ችሎቱ የእስረኞችን የዋስትና መብት ከልክሎ ነበር። የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ባለፈው እሁድ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ...
Read More »የደገሃቡር የጸጥታ አዛዥ ተገደሉ
ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ቀናት በፊት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ታጣቂዎች በደጋሃቡር ላይ ድንገት በፈጸሙት ጥቃት ከሞቱት 7 የመንግስት ታጣቂዎች በተጨማሪ የደጋሃቡር የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሻር ፣ በታጣቂዎች ጥይት ቆስለው ወደ ደጋሃቡር ሆስፒታል ከተወሰዱ በሁዋላ ዛሬ ጠዋት ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓም ማረፋቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። የአካባቢው የልዩ ሚሊሺያ አዛዥ የሆኑት ሙሃመድ ዳይክ ክፉኛ ...
Read More »ለጋሽ አገራት በኢትዮጵያ ስላለው የህዝብ መፈናቀል ምርመራ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ
ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት በጋራ እንዳስታወቁት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የህዝብ መፈናቀል ለማጣራት አንድ መርማሪ ቡድን ወደ አካባቢው ይልካሉ። ለስኳር ልማት በሚል ምክንያት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ የቦዲና ክዌጎ ጎሳ አባላትን ማፈናቀሉን ዜናውን ይፋ ያደረገው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል አስታውቋል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እንዲሁም የአለም ባንክን ያካተተው የለጋሾች ቡድን፣ የሚፈናቀሉና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ...
Read More »