ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመንአቶአንዳርጋቸውጽጌንማገቷሌላአደገኛናበጣምአሳሳቢክስተትነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል። ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን አንዳርጋቸውን ...
Read More »3 እስራኤላዊ ወጣቶች መገደላቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ጨምሯል።
ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸው እንደታወቀ የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው በሃማስ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቁዋን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል። የአገሪቱ መሪ ጠ/ሚ ናትኒያሁ ” ወጣቶቹ በሰው እንስሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” ተገድለዋል ያሉ ሲሆን፣ በሃማስ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። ይህን ተከትሎም ማምሻውን እስራኤል በሃማስ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከ30 ላላነሰ ...
Read More »በአዊ ዞን ነዋሪዎች በየጊዜው ቤት እንዲያፈርሱ መታዘዛቸው እንዳስመረራቸው ገለጹ`
ብአዴን ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚል በተለያዩ የአማራ ክልሎች እያካሄደ ባለው ውይይት የአዊ ዞን ነጋዴዎችና ነዋሪዎች መንግስት በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ መሰላቸታቸውንና ቤት አፍርሱ በመባላቸው ለችግር መደረጋቸውን ገልጸዋል። በውጭአገራት ለረጅም አመታት ኖራ፣ በአነገሯ ኢንቨስት እንድታደርግ ተጠይቃ ወደ አገሯ የገባች ነዋሪ ፣ ወደ አገሯ ከመግባቱዋ በፊት ሲነገራት የነበረው ማግባቢያና ወደ አገሯ ከተመለሰች በሁዋላ በአካል ያየችው ነገር እንደተለያየባት ገልጻለች። ” በአገርሽ ላይ አትሰሪም በሉኝና ...
Read More »የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች በድጋሜ ተቀጠሩ
በማህበራዊ ድረገጾች በመጻፍ የሚታወቁት የዞን ዘጠኝ አባላት እሁድ እለት ችሎት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ ግብረአበሮቻቸውም አልተያዙም በሚል ሰበብ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ15 ቀናት ጊዜ ተፈቅዶለታል። አቤል ዋበላ፣ በፈቃዱ ሃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የተባሉ ወጣት ጸሃፊዎች ለሀምሌ 7 ቀን 2006 ዓም ተቀጥረዋል። ችሎቱን ለመከታተል የሄደው ህዝብ ወደ ችሎት እንዳይገባ የተከለከለ ሲሆን ከጠበቃው ከአቶ ...
Read More »10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ተገደሉ
አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው 10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮ -ሱዳን ድንበር አካባቢ ከተገደሉ በሁዋላ በድንበር አካባቢ ውጥረት ሰፍሯል። እሁድ እለት ደግሞ ተጨማሪ 13 የሱዳን ወታደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ጥቃቱም በኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተዘግቧል። የሱዳን ኮማንዶ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሃይሉን እያሰባሰበ መሆኑን የገለጸው ዘገባው፣ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሷል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ከተሞቻቸውን ከታጣቂዎች ጥቃት ለመከላከል በሚል አንዱ ...
Read More »“እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ
መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውንለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለውተብሎበካሜራተቀርፆመነገሩየሚያሳዝንመሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል። ‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች በስም ከመጥቀስ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ” ለአንድነታችን በጽናት እንቆማለን” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት የረመዳንን ጾም ጀመሩ
ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ ውስጥ ረጅም ጊዜ በማስቆጠር ክብረወሰን የሰበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣ በረመዳን ጾም መግቢያም ” በአንድነታችን እንጸናለን” በሚል መፈክር ተካሂዷል። እንደወትሮው ሁሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው የጸሎት ስነስርአት፣ ሙስሊሙ “በአንድነታችን እንጸናለን” የሚሉ በወረቀት ላይ የተጻፉ መፈክሮችን ከፍ አድርጎ በማሳየትና እጅ ለእጅ በመያያዝ መልእከቱን አስተላልፏል። ዝግጅቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ...
Read More »በሃረር ታስረው ከሚገኙት መካከል የ3ቱ የዋስትና መብት ተከበረ
ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በሃረር ከተማ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ከታሰሩት ነጋዴዎች መካከል የዋስትና መብት ተከልክለው የነበሩት በቢንያም መንገሻ መዝገብ የተከሰሱት 3ቱ ነጋዴዎች በ20 ሺ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቷል። ነጋዴዎቹ ያወስትና መብት መከልከላችን ትክክል አይደለም በሚል ይግባኝ ብለው ነበር። በሌላ መዝገብ የተከሰሱት 21 ተከሳሾች ደግሞ ዳኛ አልተሟላም በሚል ለፊታችን ሃሙስ ሰኔ 25 ...
Read More »የደመወዝ ጭማሪው ጡረተኞችን ስለማካተቱ አለመነገሩ ጡረተኞችን አሳስቦአል
ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርም ደሳለኝ የሲቪል ሰርቪስ ቀንን በማስመልከት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ኣ.ም እንደሚደረግ ሲገልጹ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጡረተኞችን ጭማሪው ስለ መመልከቱ አለመነገሩ እንዳሳሰባቸው አንዳንድ ያነጋገርናቸው ጡረተኞች ገለጹ፡፡ በአጼው ዘመነ መንግሥት ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ጉልበታቸው ሳይደክም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ...
Read More »የቀድሞ የሶቭየት ህብረት ግዛቶች የአውሮፓ ህብረትን ሊቀላቀሉ ነው
ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጦርነት ውስጥ የምትገኘዋ ዩክሬን፣ ጆርጂያና ሞልዶቫ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ አገሮቹን በሂደት የህብረቱ ሙሉ አባል ያደርጋቸዋል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ውሳኔውን አጥብቀው ሲቃወሙት፣ ስምምነቱ አገሮቹን ከሁለት እንደሚከፍላቸው አስጠንቅቀዋል። አዲሱ የዩክሬን መሪ ስምምነቱን ታሪካዊ ሲሉ አወድሰውታል። የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት ቫን ሮምፑይ በበኩላቸው ስምምነቱ ለአውሮፓ ታላቅ ድል ነው ብለዋል።
Read More »