ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ያለፈቃዳቸው እንዲላኩ የተደረጉት የቀድሞው የጋምቤላ መሪ አቶ ኦኬሎ አኳይ እና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች መንግስት ያቀረበባቸውን የሽብርተኝነት ክስ በማስተባባል የመቃወሚያ መልስ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ መቃወሚያቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የክስ መቃወሚያውን ወድቅ ማድረጉን ተከትሎ የጥፋተኝነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የታዘዙት እስረኞቹ፣ አቃቢ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ አለመፈጸማቸውን እና ንጹሃን መሆናቸውን አስረድተዋል። ...
Read More »የዩኒቨርስቲተማሪዎችየሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ለኢህአዴግ ፈታኝ እንደሆኑበት ተሰብሳቢዎች ገለጹ
ነሃሴ ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርትሚኒስቴርከ360 ሺህበላይነባርናአዳዲስየዩኒቨርሲቲተማሪዎችየመንግሥትንፖሊሲናስትራቴጂን እንዲሰለጥኑአስገዳጅመመሪያማውጣቱን ተከትሎ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተሰበሰቡ ከ1500 በላይ ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያያቄዎች ለኢህአዴግ ካድሬዎች ፈታኝ እንደሆኑባቸው ውይይቱን የሚከታተሉት ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በከፍተኛ መሰላቸትና ጫጫታ የሚካሄደው ስብሰባ ዋና አላማ ተማሪውን ስለመጪው ምርጫ ማዘጋጀትና አዳዲስ አባላትን መመልመል ነው። ባለፈው አርብ በተደረገው የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ ተማሪዎች ከመብት ፣ ከዲሞክራሲና ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተዋል። እውን በአገራችን የብሄር ...
Read More »የአዲስ አበባ ህዝብ የአቶ መለስን ሙት አመት እንዲዘክር ተጠየቀ
ነሃሴ ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባከተማአስተዳደርየቀድሞጠ/ሚኒስትርአቶመለስዜናዊየሞቱበትን 2ኛሙትዓመትበማስመልከት ረቡዕነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ምምሽትበመስቀልአደባባይ ባዘጋጀው የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ላይ ሕዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ቤት ለቤት ቅስቀሳና ምዝገባ ማድረግጀምሯል፡፡ የአስተዳደሩወረዳዎችሠራተኞችናካድሬዎችቤትለቤትበመዞር «ታላቅየሻማማብራት» በሚልርዕስ 2ኛዓመት ዝክረመለስየመታሰቢያሥነሥርዓትበመስቀልአደባባይ መዘጋጀቱንየሚገልጸውንየጥሪወረቀትበማደልላይሲሆኑ በሥነሥርዓቱላይከእያንዳንዱቤትማንእንደሚገኝ፣የሚገኘውሰውየሞባይልስልክቁጥርበመመዝገብላይ ናቸው፡፡ በጥሪ ወረቀቱ ላይ ከቀኑ 7 እስከ 7፡30 በየወረዳው በተዘጋጁ ተሽከርካሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እንደሚኬድ ያሳስባል፡፡ምዝገባውበሰውላይየስነልቦናተጽዕኖ በማድረግብዙሰውፈርቶምቢሆንእንዲወጣታስቦ የተደረገመሆኑንለጉዳዩቅርበትላቸውወገኖችጠቁመዋል፡፡ ለዚህዝግጅትአስተዳደሩከፍተኛገንዘብመመደቡምታውቋል፡፡
Read More »ጃፓናውያን የመንግስት አማካሪዎች የኢኮኖሚ እድገቱን አጣጣሉት
ነሃሴ ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊን በኢኮኖሚ ዙሪያ ሲያማክሩ የነበሩትና የአሁኑ ጠ/ሚ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም በማማከር ላይ የሚገኙት ጃፓናውያን ኢኮኖሚስቶች የኢህአዴግን የእድገት ቁጥር በማጣጣል፣ የትራንስፎርሜሽን እቅዱም አለመሳካቱንም ገልጸዋል። ሪፖርተር እንደዘገበው ኢኮኖሚስቶቹባልናሚስት ፕሮፌሰርኪኒቺኦህኖናፕሮፌሰርኢዙሚኦህኖየአምስትዓመቱየኢኮኖሚዕቅድይፋከመዘጋጀቱበፊትከቀድሞውጠቅላይሚኒስትርመለስዜናዊጋርተነጋግረው ነበር፡፡እቅዱ ሲዘጋጅኢትዮጵያልታልፍባቸውናልታካትታቸውይገባልያሏቸውንሐሳቦችለአቶመለስቢያካፍሉዋቸውምዕቅዱይፋከተደረገበኋላ አቶ መለስ ሳያካትቷቸው መቅረታቸውን ለማወቅ እንደቻሉ ተናግረዋል። “የታቀዱትየተለጠጡየወጪንግድግቦችያልተሳኩትምመጀመሪያውኑብቁየሆኑኢንዱስትሪዎችባለመኖራቸውመሆኑን” የተናገሩት ፕሮፌሰሮቹ፣ የኢትዮጵያባለሥልጣናትፈጣንዕድገትለማምጣትችኩልመሆናቸውንናትዕግሥትእንደሌላቸውተናግረዋል። መንግሥትከአሥራአምስትዓመታትበፊትግብርናመርየኢንዱስትሪፖሊሲመነሻ አድርጎ የአምስትዓመትየኢኮኖሚዕቅዶችሲተገብርቢቆይምይህነውየሚባልውጤትሊያመጣ አለመቻሉም ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። ለዚህም መንስኤውአገሪቱያለባት ፖለቲካዊናመዋቅራዊችግሮች ናቸው ብለዋል፡፡መንግስትየኢኮኖሚዕቅዶቹንመተግበርየጀመረውዘግይቶ መሆኑን ...
Read More »ፍርድ ቤቱ በፋክት መጽሄት ክስ ዙሪያ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ
ነሃሴ ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመጣል ህዝቡን ያነሳሳሉ በማለት ክስ ከተመሰረተባቸው መጽሄቶች መካከል አንዱ የሆነውን የፋክት መጽሄትን ጉዳይ ለማየት የተሰየመው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ፣ ስራ አስኪያጇ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ሌላ ቀጠሮ ለመስጠት ተገዷል። ስራ አሰኪያጇ ወይዘሮ ፋጡማ ኑርየ ለምን ሳይቀርቡ እንደቀሩ የታወቀ ነገር የለም። ፖሊስ ተከሳሷ እንዲቀርቡ በስልክ መልእክት ማስተላለፉን ለፍርድ ቤት ...
Read More »በመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያልሰለጠኑ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መግባት ሊከለከሉ ነው
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስቴር ከ360 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂን እንዲሰለጥኑ አስገዳጅ መመሪያ ያወጣ ሲሆን በሥልጠናው ላይ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ያልያዘ ተማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹ ትምህርቱን መቀጠል እንደማይችል በግልጽ አስጠንቅቋል፡፡ የትምህርትሚኒስትሩአቶሺፈራውሽጉጤሰሞኑንለጋዜጠኞችእንደገለጹትበመንግሥትፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችላይ ከ250ሺህበላይነባርየዩኒቨርሲቲተማሪዎችእናከ116 ሺህበላይአዳዲስተማሪዎችለተከታታይ 15 ቀናት አበልበመክፈልባሉበት አካባቢበፕላዝማሥልጠናእንደሚሰጥአስታውቀዋል፡፡ የሥልጠናውየመጀመሪያዙርከሳምንት በኃላእንደሚጀምርያስታወቁትሚኒስትሩሁለተኛው ዙር በመስከረምወር 2007 ዓ.ምተሰጥቶለማጠናቀቅመታሰቡን ተናግረዋል፡፡ ሥልጠናውንየሚሰጡትከፍተኛየመንግሥትባለስልጣናትመሆናቸውን የሥልጠናውዝርዝርእናየሚፈጀውወጪምንያህል እንደሆነተጠይቀውከመናገርተቆጥበዋል፡፡ሆኖምሌሎችምንጮችበሥልጠናውከተካተቱት ርዕሰ ጉዳዮችመካከል ስለሃይማኖትአክራሪነት፣ስለሽብርተኝነት፣ስለልማታዊመንግሥትጉዳዮችእንደሚገኙበትጠቅሰዋል፡፡ ይህሥልጠና ኢህአዴግ በመንግሥት ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች እየታሰሩ ነው
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም 4 የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች መታሰራቸውን ተከትሎ እስረኞችያሉበትንሁኔታናየዞኑንአደረጃጀትለመጎብኘትከአዲስአበባየተላኩትየድርጅትጉዳይኃላፊውአቶብርሃኑተክለያሬድናየድርጅት ጉዳይቋሚኮሚቴአባልየሆነው ዮናስ ከድር ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አቶ ከሳሁን አየለ እና አቶ ሻምበልካሳ የተባሉት አስተባበሪዎች ታስረዋል። ሉሉመሰለ፣በፈቃዱ አበበ፣ ካሳሁን አየለ፣ሻምበል ካሳናኢ/ርጌታሁን የተባሉት የፓርቲው አስተባባሪዎችና አባላት በእስር ላይ ይገኛሉ።
Read More »በሎሚ መጽሄት ስራ አስኪያጅ ላይ የተከፈተውን ክስ ለማየት ቀጠሮ ተሰጠ
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከከሰሳቸው አምስት የግል ሚዲያ ተቋማት መካከል የሎሚ መጽሄትን ክስ የተመለከተ ሲሆን፣ ስራ አስኪያጁ አቶ ግዛው ታየ ከጠበቃቸው ጋር ተማክረው መልስ እስከሚሰጡ ድረስ ሌላ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የምክር ጊዜውን የፈቀደ ሲሆን፣ ተከሳሹ የ50 ሺ ብር ዋስ አስይዘው ለነሃሴ 14 እንዲቀርቡ ...
Read More »የኢትዮ-ሱዳን ድንበር በአንድ እዝ በሚመራ ወታደራዊ ሃይል ሊጠበቅ ነው
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን በኩል አቋርጠው የሚገቡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስጋት ፈጥረውብኛል በሚል የሱዳን መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን የድንበር ጥበቃ እንዲያድርግ ሲወተውት የቆየው የኢህአዴግ መንግስት፣ በቅርቡ በሁለቱ ድንበሮች አካባቢ የጋራ ጦር ለማሰማራት የደሰበትን ስምምነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማድርግ ሰሞኑን አዲስ የጸጥታ ስምምነት ተፈራርሟል። በዚሁ የጸጥታ ስምምነት መሰረት ሁለቱን ድንበሮች የሚጠብቅ ጥምር ጦር በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ይሆናል። ወታደራዊው እዙን ...
Read More »ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጦርነት መነሳቱ ተሰማ
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዴ ጠበቅ ሌላ ጊዜ ላላ ሲል የቆየው የደቡብ ሱዳን ግጭት መልሶ ማገርሸቱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ዩኒቲ ስቴት በሚባለው ግዛት የተጀመረው ጦርነት በቅርብ ጊዜ ከተደረጉት ሁሉ የከፋ ነው ተብሎአል። የኢጋድ አገሮች በአዲስ አበባ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በማይቀበሉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ በሚዝቱበት ሰአት ግጭት መቀስቀሱ፣ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች በኢጋድ ሽምግልና ላይ አለመተማመናቸውን እንደሚያሳይ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። ...
Read More »