ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከቀናት በፊት በባህርዳር የተካሄደውንና ምእመናን የተገደሉበትን የተቃውሞ ሰልፍ – የሚቃወም ሌላ የግዳጅ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ። እንደ ምንጮች ገለጻ በግዳጁ ሰልፍ የማይገኝ የባህርዳር ነዋሪ ቅጣት ይጣልበታል ተብሏል። ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ለተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ጦር አዛዥ የነበሩት ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ከደቡብ ሱዳን መንግስት በቀረበባቸው ክስ ከሃላፊነት መነሳታቸው ታወቀ
ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዳር 11 ቀን 2007 ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በአቤይ ግዛት ተሰማርቶ የነበረው የሰላም አስካባሪ ቡድን አዛዥ ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በእኤአ ጁን 19፣ 2014 ተልእኮዋቸውን ጨርሰው በሜ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገላልቻ መተካታቸውን ቢገልጽም፣ ኢሳት በዜና እወጃው አዛዡ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ መሰናበታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለጹት ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረገው የደቡብ ...
Read More »ምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ሊያካሂድ ላቀደው ብሔራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ በዛሬው ዕለት ጀመረ፡፡
ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤቶች ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ የሚታወቅ ቢሆንም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ከገቡት አሰጥ አገባ ጋር ተያዞ በምርጫው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ታውቆአል፡፡ አንድነት እና መኢአድ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ወስነው የምርጫ ምልክት ለቦርዱ ካስገቡት ፓርቲዎች መካከል ሲሆኑ ...
Read More »የአማራ ክልል ባለስልጣናት የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ በባህርዳሩ ግዮን ሆቴል ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት እስካሁን ማስከበር አልቻሉም፡፡
ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተረክቦ ቦታውን ለልማት ለማዋል ዝግጅት የጀመረው የክልሉ የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ሆቴሉን ነጻ ለማድረግ ከህዳር 15 ቀን ጀምሮ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ እና በውስጡ ያሉትን የግለሰብ ንብረቶች ለማስወጣት ያደረገው እንቅስቃሴ ለአንድ ወር ያህል አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ኤጀንሲው በቁጥር ኮቤልኤ-ዋሥ/32/1108 በቀን 16/ 03/07ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በግቢው ውስጥ የሚገኙትን የግለሰብ ...
Read More »ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት አብራሪዎች ቤታቸው ተፈተሸ
ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል። ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ አብራሪዎች በዋናው አብራሪ ተገደው መጥፋታቸውን ...
Read More »አንድ እንግሊዛዊ ባህር ዳር ውስጥ ተገደለ
ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የክልሉ ወኪላችን እንደገለጸችው ማንነቱ በውል ያልታወቀው እንግሊዛዊ ጧት ላይ ባዶ እጁን ወደ ጊዮርጊስ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በአንድ የሚሊሺያ አባል ተገድሏል። ገዳዩ መሳሪያ በመያዝ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ ሟቹን ሲጠባበቀው እንደነበር ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው ሰዎች ገልጸዋል። በሆቴሉ አካባቢ ጫማ በመጥረግ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ገዳዩ መሳሪያውን ይዞ ከእነሱ ጋር ሲቀመጥና ሲንቀሳቀስ እንደነበር ገልጸው፣ በሰውየው ...
Read More »በሽብርተኝነት መዝገብ የተከሰሱት ፍርድ ቤት ቀረቡ
ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት የሰማያዊ፣ የአንድነትና አረና አመራሮች ከሌሎች 6 ተከሳሽ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ልደታ በሚገኘው 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው በእስር ቤት ውስጥ ስለሚደርስባቸው እንግልትና የደህንነት ስጋት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አሰምተዋል። የተከሳሾች ቤተሰቦች እስረኞችን ለመጠየቅ በሚሄዱበት ጊዜ በተለየ መዝገብ መመዝገባቸውን በመቃወም ለፍርድ ቤት ባሰሙት አቤቱታ መሰረት ፣ ማረሚያ ቤቱ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ችግራቸውን በቶሎ እንዲፈቱ ተጠየቁ
ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ አፍሪካው መሪ ጃኮብ ዙማ ደቡብ ሱዳናዊያን ለ2 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በድርድር እንዲፈቱ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሰላም ድርድር ውጤት ለማምጣት በተሳነው በዚህ ወቅት፣ ደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ግፊት እያደረገች ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን የማይፈቱ ከሆነ ማእቀብ ይጣልባቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
Read More »አየር ሃይል እየታመሰ መሆኑን ምንጮች ገለጹ
ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ የአየር ሃይል አዛዦች አስቸኳይ ግምገማ ከተጠሩ በሁዋላ እርስ በርስ እየተገማገሙና ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያስቡትን የአየር ሃይል አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በተለይም የትግራይ ...
Read More »መድረክ ከምርጫው በፊት ሜዳው እንዲስተካከል ድርድር መካሄድ አለበት አለ
ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መድረክ ባወጣው መግለጫ በሀገራችን የምርጫ ሂደት የነበሩ ጉድለቶችንና በተለይም በ2002 የሀገራችን የምርጫ ሂደት የወረደበትን አዘቅት በሚገባ በጥልቀት ገምግሞ እነዚህን ቀደም ባሉት ምርጫዎች የነበሩ ጉድለቶችን ማረምና ማሰተካከል ለ2007 ምርጫ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ መሆን የምኖረውን ወሳኝ ሚና በግልጽ ቢያስቀምጥም፣ ይህንን እውነታ በአግባቡ መገንዘብ ያልቻሉና ከ1997 እና ከ2002 ምርጫዎች ደካማ ጎኖች ተገቢውን ትምህርት ለመቅሰም ያልቻሉ ...
Read More »