አንድ እንግሊዛዊ ባህር ዳር ውስጥ ተገደለ

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የኢሳት የክልሉ ወኪላችን እንደገለጸችው ማንነቱ በውል ያልታወቀው እንግሊዛዊ ጧት ላይ ባዶ እጁን ወደ ጊዮርጊስ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በአንድ የሚሊሺያ አባል ተገድሏል። ገዳዩ መሳሪያ በመያዝ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ ሟቹን ሲጠባበቀው እንደነበር ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው ሰዎች ገልጸዋል። በሆቴሉ አካባቢ ጫማ በመጥረግ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች  ገዳዩ መሳሪያውን ይዞ ከእነሱ ጋር ሲቀመጥና ሲንቀሳቀስ እንደነበር ገልጸው፣ በሰውየው ሁኔታ ግራ በመጋባት ከአካባቢው እንዲርቅ እንዳደረጉትና ራቅ ብሎ ሲጠባባቅ እንደነበር ተናግረዋል። ድርጊቱ ሲፈጸም ፖሊሶች በአካባቢው የነበሩ ሲሆን፣ ገዳይ ፈረንጁን ከገደለው በሁዋላ የላምንም ማንገራገር እጁን ለፖሊሶች ሰጥቷል። በጉዳዩ ዙሪያ የእንግሊዝ ኢምባሲንና የክልሉን ፖሊስ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።