የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ችግራቸውን በቶሎ እንዲፈቱ ተጠየቁ

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የደቡብ አፍሪካው መሪ ጃኮብ ዙማ ደቡብ ሱዳናዊያን ለ2 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በድርድር እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሰላም ድርድር ውጤት ለማምጣት በተሳነው  በዚህ ወቅት፣ ደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ግፊት እያደረገች ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን የማይፈቱ ከሆነ ማእቀብ ይጣልባቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።