የባህር ዳር ከተማ ፖሊሶች በሙሉ ለስድስት ቀናት  አስቸኳይ ስልጠና ገብተዋል

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትራፊክና የማረሚያ ቤት ፖሊሶችን ጨምሮ የባህር ዳር ከተማ  ፖሊሶች በሙሉ ከእሁድ እለት ጀምሮ  ስልጠና  ላይ ናቸው። አባይ ማዶ በሚገኘው የምክር ቤት አዳራሽ እሁድ እለት በተጀመረውና እስከ ፊታችን አርብ በሚቆየው ስብሰባ  በጠቅላላ ፖሊሶች በመግባታቸው፤ በከተማዋ ም ሆነ በማረሚያ ቤቶች የሚታይ አንድም ፖሊስ የለም።

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ የቦርዱን ውንጀላ-መሰረተ-ቢስ  አለው።

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታህሣሥ 28/2007 ዓ.ም ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ህገ-ወጥ ተግባራት›› እየፈጸመ እንደሆነ በመግለጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ ለጻፈው ደብዳቤ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በፃፈው መልስ ምርጫ ቦርድ ያቀረባቸው ውንጀላቸው ህገ-ወጥ በመሆናቸው ቦርዱ ከውንጀላዎች  እንዲቆጠብ ጠይቋል፡ << ሰማያዊ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና ሳያገኝ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፣ ቦርዱ ያዘጋጃቸውን ስብሰባዎች ረግጦ ወጥቷል፣ ከቦርዱ እውቅና ውጭ ፓርዎቹን እያስተባበረ ነው>> በማለት ምርጫ ...

Read More »

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ሳይገኝ ቀረ።ጠቅላላ ጉባኤውን ተካፍሎ ወደ ቤቱ ሲሄድ የነበረ የፓርቲው አባል በፖሊሶች ተደበደበ።

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ  -አንድነት በአራት ቀናት ዉስጥ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሮችን በምስጢር አሰጣጥ መምረጥ እንዳለበት ሲያሳስብና ሲያስጠነቅቅ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም፤  ይህን የቦርዱን ማስጥንቀቂያ ተከትሎ  አንድነት ከትናንት አርብ  ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤና  የአመራር ምርጫ  ታዛቢ እንዲልክ በደብዳቤ የተጠየቀው ምርጫ ቦርድ፤  “አየለ የሚባል ሰው ሌላ የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል የሚል ደብዳቤ ስላሰገባ፣ በሁለት ቦታ መገኘት አንችልም” የሚል ...

Read More »

ምርጫ ቦርድና ከመኢአድና ከአንድነት ፓርቲዎች ጋር የገባው ውዝግብ  ይበልጥ እየ ተካረረ ነው።

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መኢአድ መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ሲል አንድነት ፦” ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም እያለ ነው። ባሳለፍነው ሳምንት መግቢያ የምርጫ ቦርድ  ምክትል ሰብሳቢ  <<አንድነትና-መኢአድ በውስጠ ድንባቸው መሰረት ያልፈቷቸው ችግሮች አሉ፤ችግሮቻቸውን ካልፈቱ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ>> ማለታቸው ነው  የውዝግቡ መነሻ። በወቅቱ በውስጠ-ደንቡ መሰረት ምንም ያልፈታው ችግር እንደሌለ የገለጸው አንድነት ፓርቲ፤ ምርጫ ቦርድ  በምርጫው እንዳይሳተፍ ካገደው ውሳኔው ፖለቲካዊ ...

Read More »

በመጪው  የጥምቀት በዓል ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርቶችን  መልበስ አትችሉም ተባሉ፤ 

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቲሸርቶቹ ላይ የሚያሳትሟቸውን ሀይማኖታዊ  ጥቅሶችም  በራሳቸው መምረጥ እንደማይችሉ ተነገሩ። ድርጊቱ  የግል የማመን መብታችንን የሚጋፋ ከመገሆኑም በላይ ሀይማኖታችንንም መድፈር ነው ያሉ ወጣቶች ቁጣቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ፖሊሶች ከትናት ታህሳስ 1 ቀን ጀምሮ በ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች በመንቀሳቀስ ወጣቶች  ለመጪው የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሰማያዊ-ቲሸርት መልበስ እንደማይችሉ፣ እንዲሁም በቲሸርቶቻቸው ላይ የሚያሳትሟቸውን ሀይማኖታዊ ጥቅሶች  ፓሊሶች  እስከሚነግሯቸው ...

Read More »

ታንኮችን የጫኑ  የመከላከያ ስራዊት  መኪናዎች  ወደ ጎንደር አቅጣጫ መጓጓዛቸውን  የባህር ዳር ነዋሪዎች ተናገሩ።

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስኞ  እለት ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ታንኮችን የጫኑ የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች  ባህር ዳር ከተማ መግባታቸውን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት እንዳሉት፤ ከየት አቅጣጫ እንደመጡ ያልታወቁ የጦር ተሸከርካሪዎች  ሰኞ ምሽቱን ባህርዳር ወደሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት(መኮድ) ካምፕ ገብተው ካደሩ በሁዋላ  በማግስቱ ጧት ወደ ጎንደር አቅጣጫ ተጓጉዘዋል። ተሸከርካሪዎቹ የጫኗቸው ታንኮች ላይ ከባድ መሳሪያዎች ...

Read More »

ሁለት የኢሳት ጋዜጠኞች በድንበር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለመዘገብ ወደ ኤርትራ መሄዳቸው የበርካታ ኢትዮጵያንን እያነጋገረ ነው።

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በትናንት በዘገባው እንዳስታወቀው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም  ወደ ኤርትራ ያቀኑት  በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የ ኢት ጰያ ተቃዋሚዎች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ በዓይን አይቶ ለመዘገብ፤እንዲሁም  ከተሳካላቸው በወደፊቱ የኢትዮጰያና የኤርትራ ግንኙነት ዙሪያ  የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ነው። ይህን ተከትሎ  እጅግ በርካታ ኢትዮጰያውያን ለጋዜጠኞቹ ያላቸውን አክብሮትና አድንቆት  በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። እነኚህ ...

Read More »

ኢህአዴግ – በመንግስት በጀት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመምህራንን እና ለመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው።

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገራዊው ምርጫ ጥቂት ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች ማሰተማራቸውንና ስራቸውን በማቆም ስልጠና እንዲገቡ መታዘዛቸውን ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህም መሰረት በባህር ዳር የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ከፊታችን ማክሰኞ ጀምሮ ማስተማራቸውን በማቁዋረጥ ወደ ስልጠና እንዲገቡ ታዘዋል። እንዲሁም በጋሙጎፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በማቆም ወደ ስልጠና እየገቡ ...

Read More »

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ፤ እንዲሁም በሰማያዊ ፓርቲ አባል አቃቤ ህግ ምስክር አሰማ

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መውደቁን  ቤተሰቦቹ ገለፁ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት፤ ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ከመሆኑም በላይ በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ ይወሰዳል፡፡ ቤተሰቦቹ እንዳሉት፦ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በኮማንደር ...

Read More »

በጎንደር አርማጭሆ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊበርድ አልቻለም

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ በጎንደር አርማጭሆ ውስጥ <<ሶረቃ>> የሚባለውን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማካለል በወሰዱት እርምጃ የተነሳው ግጭት እስካሁን ሊበርድ እንዳልቻለ  በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል። ወኪላችን እንዳለው ታጣቂዎቹ፤ አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት አስነስተው ቦታውን ለማካለል ያደረጉትን ጥረት የአካባቢው ህዝብ  ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስና ውጊያ ጭምር በመግጠም  ነበር ያከሸፈው።በወቅቱ የታጣቂዎቹን ...

Read More »