ደቡብ ኦሞ ውስጥ በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል ግችት ተቀስቅሶ የነዋሪዎችና የፖሊሶች ህይወት ጠፋ፤ ግጭቱና ውጥረቱ ሊቆም አልቻለም።

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን አመር ወረዳ- ላላ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ አርብቶ አደሮችና- በፖሊስ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ነፍስ መጥፋቱን ነገረ ኢትዮጰያ ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትናንት ጥር 7/2007 ዓ.ም  <<አርብቶ አደሮች ማጎ ፓርክ ገብተው አውሬ ገድለዋል>> በማለት  ፖሊስ- አርብቶ አደሮቹ ገዳዩን አሳልፈው እንዲሰጡት በጠየቀበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው። በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ...

Read More »

አርበኞች- ግንቦት 7 ለ አንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ለ ኢትዮጰያ ህዝብ፣ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረበ።

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው  በግንቦት 7 እና በ አርበኞች ግንባር መካከል የተደረገውን ውህደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ << እኛ መዋሃድ መወሰናችንን  ስንገልጽ፤ በተናጠል ከሚደረጉት – በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣፡”የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም’ የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም ጭምር ነው።” ብሏል። <<ከትናናሽ ድርጅቶች ...

Read More »

የጥምቀት በዓል መድረሱን ተከትሎ  ውጥረት አለ፤ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከሥላሴ በዓል ላይ ተባረሩ

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥር 7/2007 ዓ.ም የዓመቱን የሥላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ መባረራቸውን ነገረ- ኢትዮጰያ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ የተጻፈበት  ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ እንዳባረራቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡  ከተባረሩት ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡትንና ...

Read More »

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 09 እና 10  ውስጥ ከሀይለስላሴ ዘመን አንስቶ በካምፕ ሲኖሩ የነበሩ  ከ500 በላይ አባት ጡረተኞችና አርበኞች  ቤታቸው  እንዲፈርስ በመደረጉከነቤተሰቦቻቸው ሜዳ ላይ መበተናቸውን ለኢሳት ገለጹ።

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልኳንዳ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  የሚገኘውንና ከጥንት ጀምሮ  የአባት ጦረኞችና የአርበኞች መኖሪያ የሆነውን የወታደር ካምፕ  ቦታው ተከልሎላቸው የሰሩት  ራሳቸው   አርበኞቹ  መሆናቸው ተመልክቷል። ፈጽሞ ባላሰቡበትና ባልተዘጋጁበት ሁኔታ መኖሪያ ካምፓቸው ያለ ምንም ተለዋጪ ማረፊያ  መሳሪያ በታጠቁ ወታደሮች እንዲፈርስ መደረጉ እንዳስደነገጣቸው የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፤ ውሳኔውን በመቃወም እስከ ፍትህ ሚኒስቴር ድረስ አቤት ቢሉም ሰሚ ማጣታቸውን ገልጸዋል። እንደ ነዋሪዎቹ  ገለጻ፦ቤታቸው ...

Read More »

ከደምሕት ጋር ግንኙነት አለህ ተብሎ  የታሰረው ወጣት ሺሻይ አዘናው ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትግራይ ሕዝብ ዲሚክራሲያዊ ድርጅት ‹‹ደሚህት››  ጋር ግንኙነት  ተብሎ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት የመቀሌ ዞን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ወጣት ሺሻይ አዛናው በትናንትናው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት። ወጣት ሲሳይ  ቀደም ሲል በተጠየቀበት የሃያ ስምንት ቀናት ቀነ-ቀጠሮ መሰረት ትናንት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት   ቢቀርብም፣ ፖሊስ ማስረጃዬን ሰብስቤ አልጨረስኩም በማለት   እንደገና የሃያ ስምንት ቀናት ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አንድ ከፍተኛ ቧለስልጣን አባረሩ።

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፎርቹን ሳምንታዊ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ -የአእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤትን በጀነራል ዳይሬክተርነት እረየመሩ ያሉትን አቶ ብርሀኑ ያዴሎን   ካለፈው ታህሳስ 27 ቀን ጀምሮ ከስልጣን አንስተዋቸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተጻፈ ደብዳቤ  ከዚያው እለት ጀምሮ በአስቸኳይ አቶ ብርሀኑ ያዴሎ ከስልጣናቸው መነሳታቸውንና በምትካቸው በቢሮው የፓተንት ዳይሬክተር የሆኑት  አቶ ግርማ በጅጋ መተካታቸውን ይገልጻል። አቶ ብርሀኑ ያዴሎ የደኢህዴግ ...

Read More »

የኢሳት ባልደረባ የሆነው የጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ባለቤት ወይዘሮ አበባ መልሰው ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ከኢትዮጰያ ተባረረች።

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ለእህቷ ስርግ ወደ ኢትዮጰያ አቅንታ የነበረችውና ላለፉት 20 ቀናት በአዲስ አበባ የቆየችው ወይዘሮ አበባ፤ ከነ ልጆቿ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ታስራ እንድታድር ከተደረገች በሁዋላ ነው ከሀገር የተባረረችው። በእህቷ ሰርግ ላይ በርካታ ደህንነቶች ሲከታተሏት እንደነበረ የገለጸችው ወይዘሮ አበባ፤ በማግስቱ በቤተሰቦቿ ቤት ሳለች  ሁለት ደህንነቶችና አራት ፖሊሶች በመምጣት  ...

Read More »

ግብጽ በዓባይ ግድብ ላይ ተቃውሞ አሰማች።

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር -በኢትዮጰያ እየተሰራ ያለው ግድብ የሚይዘው የውሀ መጠን በግብጽ  የውሀ ድርሻ ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል  እንደሚቃወመው አስታወቀ። አህራም  ኦንላይን “ሜና”የተሰኘውን የ አገሪቱን የዜና አገልግሎት ጠቅሶ  እንደዘገበው በመስኖ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የአባይ ግድብ ቃል አቀባይ የሆኑትን ሚስተር አላን ያሲን  በአሁኑ ወቅት ኢየተሰራ ያለውና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይይዛል የተባለው ግድብ ግብጽ የውሀ ...

Read More »

አንድነት ለፍትህኗ ለዲሞክራሲ ፓርቲ- ከመድረክ ጋር በትብብር ከመ ኢአድ እና ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ደግሞ ውህደት ፈጥሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነጻነት የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተክሌ በቀለን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ታህሳስ 25 ቀን 2007 ኣመተ ምህረት ባደረገው ስብሰባ  መጪውን ምርጫና ከምርጫው ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች፤ እንዲሁም ከምርጫው በሁዋላ ፓርቲዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ትብብርና ውህደት የሚያመቻች ኮሚቴ ተቋቁሟል። በስብሰባው፣ ፓርቲዎች በትብብርና በውህደት መስራት እንዳለባቸው ስራ አስፈጻሚው መምከሩን ...

Read More »

በጣይቱ ሆቴል መቃጠል ህብረተሰቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው።

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት እሁድ ጥር 3-2007 ማለዳ ላይ ነበር በ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሰመናዊ ሆቴል የሆነው ታሪካዊው ጣይቱ ሆቴል በእሳት የወደመው። የዓይን ምስክሮች በወቅቱ እንደተናገሩት፤የእሳት አደጋ ብርጌድ መስሪያ ቤት በሆቴሉ አቅራቢያ ሆኖ ሳለ እሳቱ ከተነሳ በትንሹ ለአንድ ሰኣት ያህል አንድም የ እሳት አደጋ መኪና አለመታዬቱ፣ሰግይተውም ከመጡት ሶስት መኪኖች መካከል አንድኛው ወሃ የለኝም ብሎ እንዲሁ መቆሙ ነው ...

Read More »