ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። >> ነው ሲል ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ ገለጸ።

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑና አቶ አንዳርጋቸው ...

Read More »

በምርጫ ቦርድ እና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረው  ውጥረት እየተካረረ ነው። የአንድነት አመራሮች ለአባሎቻቸው ጥሪ እያቀረቡ ነው።

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጥረቱ  መካረር ምክንያት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር  ከቦርዱ ውሳኔ ቀድመው ወደ ድርጅት ሚዲያ በመሄድ ” አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ” የሚል መግለጫ መስጠታቸው ነው። ዶክተር አዲሱ፤ ሁለቱ ፓርቲዎች  በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ  በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን አለመፍታታቸውን በመጥቀስ፤  አሁን ባሉበት ሁኔታ በምርጫ ሊሳተፉ እንደማይችሉ ...

Read More »

ከትናን በስቲያ ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር የሚገኙ የውስጥ መንገዶች  በግድግዳ ላይ ጽሁፎችና መፈክር በተጻፈባቸው ወረቀቶች አሸብርቀው ማደራቸውን ፍትህ ራዲዮ ዘገበ።

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮው  ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የውሎ ሰፈር የውስጥ መንገዶች ግድግዳ ላይ የተጻፉት መፈክሮች-ህዝበ-ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ያቄዎች የሚያሰተጋቡና  መብታቸውን በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም  መሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ናቸው። ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል፦”አዐባሪዎች አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ!ኮሚቴው ይፈታ!የሂጃብ ገፈፋው ይቁም! ትግሉ ይቀጥላል! እና ፍትህ ናፈቀን!”የሚሉት ይገኙበታል። በግድግዳ ላይ ከተጻፉትና ከተለጠፉት ባሻገር ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር ያነሷቸውን ጥያቄዎች የሚያስተጋቡ ...

Read More »

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ካርዲናል ሆኑ

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የካርዲናልነት ማዕረግ አገኙ፡፡ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስን ጨምሮ ለ15 ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግና ለአምስት ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት ደግሞ ድምፅ አልባ  የካርዲናልነት ሹመት ባለፈው እሑድ ረፋድ ላይ በቫቲካን በመስጠት ይፋ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናቸው፡፡ ቫቲካን ሬዲዮ ታኅሣሥ 26 ...

Read More »

ምርጫ ቦርድ ፤አንድነትና መኢአድ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ አለ።

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት፤ ከምርጫው ከታገድኩ  ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው የሚሆነው አለ። አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)  የውስጥ ችግሮቻቸውን ካለፈቱ የምርጫውን ሂደት ላይሳተፉ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ  ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር ፦ሁለቱ ፓርቲዎች በውስጥ  ህገ ደንባቸው ሊሄዱ እንዳልቻሉ በመጥቀስ፤ ይህንንም አስመልክቶ ቦርዱ  ሊያወያያቸው ቢሞክርም ሊግባቡ ...

Read More »

ወሎ ውስጥ በኦሮሞዎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው ተባለ

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ፤ ከአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ  ታስረው ከስምንት ወራት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ታሳሪዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ። ሊጉ  የ 26  እስረኞችን ስም ዝርዝር በማያያዝ ባወጣው መግለጫ፤ ከወራት በፊት የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን በመቃወም ተነስቶ ከነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ  የወሎ ኦሮሞዎችን ጨምሮ ...

Read More »

አቶ መለስን የሸለመው”ያራ” ኩባንያ” ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተበት

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ 97 ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የሸለመው “ያራ” የተሰኘ የኖርዌይ ድርጅት  በሙስና ተከሰሰ ፤ ኢትዮጰያውያንም ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1997 ዓመተ ምህረት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ 200 000 ዶላር የሸለመውና- ሽልማቱን ተከትሎ  በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኢትዮጵያ ብቸኛ የማዳበሪያ አቅራቢ የሆነው የ”ያራ ኩባንያ”ዳይሬክተር ቶርሊፍ ኢንገር፤ በኖርዌይ ታሪክ ትልቅ በተባለው የሙስና ...

Read More »

የህወሀት መስራችና የቀድሞ ሊቀ-መንበር  የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ፤ ጎተራን  ለአምሰት አመት ኮንትራት በ600 ሺህ ብር እንደወሰደው ፎርቹን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገበ።

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ጋዜጣው ዘገባ የአክሊል ክሬቲቭ ኤጄንሲ ባለቤት የሆነው ተከስተ ስብሀት  ነጋ፤ በአካባቢው ያለን 4000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሬትን ለተለያዩ መዝናኛዎች፣እንዲሁም  43 ትልልቅ ጎተራዎችን ለማስታወቂያ ስራ  ነው በ600 ሺህ ብር ለአምስት ዓመት ኮንትራት የወሰደው። ለጥቂት ቀናት የሚለጠፍ አንድ ማስታወቂያ ብቻ ብዙ ሺህ ብር  በሚያስከፍልበት በአሁኑ ወቅት፤ ትልቅ አደባባይ የሆነውን የጎተራን አካባቢና ትላልቆቹን  43 ...

Read More »

የጣና ሐይቅና ብዝሀ- ህይወቱ ላይ እስካሁን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘርፈ ብዙ አደጋ አንዣቦበታል ተባለ፡፡

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጣና ሐይቅና በዙሪባ በሚገኙ የእርሻ መሬቶች ላይ የተከሰተውን አደገኛ አረም ለማየት የተንቀሳቀሰው ቡድን ሃምሳ ሽህ ሄክታር የሚሸፍን የጣና ሐይቅ እና ዙሪያው በእምቦጭ አረም መወረሩን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጿል ፡፡ ይህም ለሐይቁ ህልውና አስጊ መሆኑን፤ የተለያዩ ከፍተኛ የገዢው መንግስት አካላትና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮች በበኩላቸው፦” የምናርሰው መሬት ሙሉ በሙሉ በአረሙ በመወረሩ ...

Read More »

አንድ የአየር ሃይል አብራሪ ተቃዋሚዎችን  መቀላቀሉ ተሰማ

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡዕ ታህሳስ 15፣ 2007 ዓም ኢሳት 4 የአየር ሃይል አብራሪዎች ወደ ኬንያ ማምራታቸውን በሰበር ዜና ካቀረበ በሁዋላ፣ አንድ ተጨማሪ የአየር ሃይል ባልደረባ ጠፍቶ ተቃዋሚዎችን መቀላለቀሉ ተሰምቷል። ባለፈው ሮብ የጠፉት የሚግ 23 አብራሪ ሻምበል ገዛሃኝ ደረሰ፣ የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ ሻምበል ዳንኤል ግርማ፣  የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ መቶ ...

Read More »