በሞያሌ በተነሳው ተቃውሞ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሆቴሎች ከፍተኛ ውድመት ደረሰባቸው

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በከተማዋ ከሚታወቁት  ሆቴሎች መካከል  ፈቃዱ ሆቴል ፣ ኢትዮ ኬኒያ ሆቴል ፣ ሃጎስ ሆቴልና ማሕሌት ሆቴል ጉዳት ድርሶባቸዋል። የሆቴሉ ባለቤቶች የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ናቸው በሚል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ ኢህአዴግን በመደገፍ እና ቅስቀሳ በማድረግ የሚታወቁት የማህሌት ሆቴል ባለቤት ንብረት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።  የአካባቢው ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች የተጎዱ ...

Read More »

በአፋር ክልል በፕሬዚዳንቱና በጸጥታ ሹሙ መካከል አለመግባባቱ ተባብሷል

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ ፕሬዚዳንት እስማዔል አሊ ሴሮ እና በጸጥታ ዘርፍና በፍትህ ቢሮ ሃላፊው መካከል የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ ተባብሶ በወረዳ ያሉ አመራሮችን ሳይቀር መከፋፋሉንየኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አሊ ሴሮ ከ24 አመት በላይ የያዙትን የፕሬዚዳንትነት ቦታ በሚቀጥለው አመት እንደሚለቁ ፍንጮች መታየታቸው አሁን ለታየው የስልጣን ሽኩቻ መንስኤ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አሊ ሴሮ ለእርሳቸው ቀረቤታ ያላቸው ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድንገት ለማረፍ ተገደደ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቻይና ጉዋንዙ ግዛት የተነሳው የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 607 አውሮፕላን በህንድ የሙምባይ ግዛት በድንገት አርፎ ነዳጅ መቅዳቱ ተዘግቧል። ይሁን እንጅ ከ3 ሰአታት ቆይታ በሁዋላ እንደገና በረራውን የጀመረው አውሮፕላን ከአንድ ሰአት ተኩል በረራ በሁዋላ ዳግምበሙምባይ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። በውስጡ 283 መንገደኞችን፣ 14 የበረራ አስተናጋጆችንና ሰራተኞችን የያዘው አውሮፕላን ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር በውል ተለይቶ ...

Read More »

የአፍሪካ ህብረት የሱዳንን ምርጫ እንደማይታዘብ አስታወቀ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህብረቱ በሱዳን ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅደመ ምርጫ ዝግጅቶች በቂ አይደሉም ብሎአል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሲቪክ ማህበረሰብአባላትና ሚዲያው በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን የገለጸው ህብረቱ፣ “በዚህም የተነሳ አሁን ባለው ሁኔታ በሱዳን ነጻ ምርጫ ለማድረግ ሁኔታዎች ምቹ ባለመሆናቸው ለመታዘብ አንችልም” ብሎአል። አፍሪካ ህብረት ራሱን ከምርጫ ታዛቢነት ያገለለበት ሁኔታ ብዙዎችን አስገርሟል። በኢትዮጵያ ነጻ ...

Read More »

ሞያሌ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ እኩለቀን ድረስ በተኩስ ተናጠች

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ከትናንት ሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ እኩለቀን ድረስ ከተማዋ በተኩስ ስትናወጥ ውላለች። አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት የተኩሱ ልውውጡ የተካሄደው በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያዎች መካከል ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንድ የክልል 5 ጠባቂ መግደላቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ልዩ  ሃይል ሚሊሺያዎች በየሰዎች ቤት እየገቡ እቃዎችን ከመሰባበርና ...

Read More »

በኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ እየጨመረ ነው

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ባደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት  ምርቶችን ውደ ውጭ በመላክ    በያመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በአምስቱ አመታት ውስጥ ያሳካው ሩቡን ያክል መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። መንግስት በያመቱ ከኤክስፖርት ከ2 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን እስከ 3 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቢቆይም፣ በአምስት አምት ...

Read More »

የወላይታ ዞን የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በወላይታ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ያቀረቡ 8 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዞኑ እየደረሰባቸው የሚገኘው አፈና እና በደል መፍትሄ ካልተሰጠው ራሳቸውን  ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ሊያገሉ እንደሚችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ፣ ለምርጫ ቦርድና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ ገልጻዋል። ማስጠንቀቂያውን የጻፉት ድርጅቶች ሰማያዊ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕና ...

Read More »

በአማራ ክልል የሚገኙ የቆዳና ሌጦ ነጋዴዎች ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ፡፡

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደር ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ የቆዳና ሌጦ ነጋዴዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች እንደተናገሩት፤ ባለድርሻ አካላት ስራቸውን በአግባቡ ባለመስራታቸው ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በቆዳ ፋብሪካ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቂት ባለሃብቶችን ለመደገፍ በሚል ሰበብ  የጥሬ ቆዳና ሌጦ ዋጋን በዝቅተኛ ዋጋ እንዲቀርብ መመሪያ በማውጣታቸው በላተኛ ህብረተሰቡና አቅራቢ ነጋዴዎች መጠቀም ...

Read More »

በመከላከያ ስም የተያዙ የንግድ ድርጅቶች የግል ነጋዴዎችን ከጨዋታ ውጭ እያደረጉ ነው

ሚያዝያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ስም የተያዙ የንግድ ድርጅቶች በግሉ ዘርፍ መከናወን ያለባቸውን ስራዎች ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ መሻማታቸው፣ በግሉ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ መምጣታቸውን  ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የመከላከያን መስረተ ልማቶች ለማሟላት በሚል በልማት ድርጅትነት ራሱን ችሎ የተቋቋመው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በመውጣት ልማትን ለማገዝ በሚል ሽፋን ከግሉ ዘርፍ ጋር እየተወዳደረ በንግድ ስራ ላይ መሰማራቱ ተገቢ ...

Read More »

የመንግስት ቤቶችን ለመንግስት ባለስልጣናት ብቻ የሚያደርግ መመሪያ ስራ ላይ ዋለ

ሚያዝያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት በመባል ይጠራ የነበረውና በአሁኑ ወቅት የመንግስት ቤቶች አጀንሲ የሚባለው በምዝገባ ለዜጎች መኖሪያ ቤቶች በኪራይ የሚሰጥበትን የቆየ አሰራር በመተው ለባለስልጣናት ብቻ ለመስጠት የሚያስችል አዲስ መመሪያ አውጥቶ በሥራ ላይ አውሎአል። አጀንሲው ከዚህ ቀደም ለበርካታ ዓመታት ወረፋ በመጠበቅ ከዛሬ ነገ የኪራይ ቤት እናገኛለን ብለው ተስፋ ያደረጉ በሺ የሚገመቱ ደንበኞቹን ተስፋ ...

Read More »