የአፍሪካ ህብረት የሱዳንን ምርጫ እንደማይታዘብ አስታወቀ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህብረቱ በሱዳን ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅደመ ምርጫ ዝግጅቶች በቂ አይደሉም ብሎአል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሲቪክ ማህበረሰብአባላትና ሚዲያው በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን

የገለጸው ህብረቱ፣ “በዚህም የተነሳ አሁን ባለው ሁኔታ በሱዳን ነጻ ምርጫ ለማድረግ ሁኔታዎች ምቹ ባለመሆናቸው ለመታዘብ አንችልም” ብሎአል።

አፍሪካ ህብረት ራሱን ከምርጫ ታዛቢነት ያገለለበት ሁኔታ ብዙዎችን አስገርሟል። በኢትዮጵያ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ሁኔታዎች ምቹ አይደሉም በሚል የአውሮፓ ህብረት ራሱን ከምርጫ ታዛቢነት ሲያገል ፣ የአፍሪካ ህብረት በብቸኝነት ይታዘባል። በሱዳን ያለው ሁኔታ ከኢትዮጵያ የተሻለ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያን ምርጫ ሲታዘብ የሱዳንን አልታዘብም ማለቱ፡ህብረቱ በምእራብ አገሮች ፍላጎት ብቻ የሚንቀሳቀስ ነው በሚል እያስተቸው ነው።

የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ የሚካሄዱ ኢ ፍትሃዊ ምርጫዎችን ሳይቀር በማጽደቅ ይታወቃል።