ኢሳት (ታህሳስ 25 ፣ 2008) ባለፈው ሐሙስና ቅዳሜ ጠዋት በዲላ ዩንቨርስቲ በእጅ በተወረወረ ቦምብ ጥቃትና በስለት ተወግተው 4 ተማሪዎች መሞታቸውን ከዲላ የአይን እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል። ከተጎጂዎቹ ውስጥ በቦምብ ጥቃት የሞቱት በተለምዶ “ሰመራ” ተብሎ በሚጠራው ካምፓስ የሚኖሩ ሁለት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሌሎች ከ10 የማያንሱ ተማሪዎች ደግሞ በቦምብ ፍንዳታውና በጩቤ ተጎድተው በዲላ ሬፈራል ሆስፒታል ህክምና እያገኙ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪውም ባለፈው ቅዳሜ ጠዋት ...
Read More »የመንግስት ወታደሮች በኦሮምያ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንደቀጠሉ ነው
ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለተከታታይ ሳምንታት በኦሮምያ የተደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቀጥሏል። የመንግስት ወታደሮች ያለርህራሄ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እየወሰዱ ነው። እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ መንገድ የተገደሉ ዜጎችን ምስል በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ማየት የተለመደ ክስተት ሆኗል። መንግስት የሚወስደው ከልክ ያለፈ እርምጃ ተቃውሞን ከመባባስ ውጭ ሊገታው አልቻለም። በምእራብ ሃረርጌ በቆቦ ከተማ፣ ...
Read More »በዲላ ዩኒቨርስቲ ግጭቱ ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል ተማሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ
ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶስት ቀናት በፊት በዲላ ዩኒቨርስቲ ምሽት ላይ በተመሳሳይ ሰአት በፈነዱ 4 ቦንቦች አንድ ተማሪ ወዲያውኑ ሲሞት፣ አንደኛው ሆስታል ከገባ በሁዋላ መሞቱ መዘገቡ ይታወሳል። ፍንዳታውን ተከትሎ 10 ተማሪዎች በጩቤ የተወጉ ሲሆን፣ አንዳንድ ተማሪዎች ለዘጋቢያችን እንደገለጹት ጉዳቱን ያደረሱት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት አለመሆናቸውን ተናግረዋል። በፍንዳታው አንድ አዳማና ሌላ ደብረብርሃን ልጅ ሲገደሉ፣ አንድ አርባ ...
Read More »ድርቁ እየተባባሰ በመጣባቸው አካባቢዎች የትምህርት ሰራው እየተጎዳ መምጣቱ ተነገረ፡፡
ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ፣ የሚያስተምሩ መምህራን በየጊዜው ስራቸውን በመልቀቃቸው የትምህርቱ ስራ አደጋ ላይ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጎንደር ከተማ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡ በዞኑ ባሉት 280 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ120 ሽህ በላይ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቆም በቋፍ ላይ መሆናቸወን የተናገሩት የዞኑ አመራሮች በተለይ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፖሊሶች ሁለት ኬንያዊያንን አግተው መውሰዳቸው ታወቀ
ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቅዳሜ እለት የኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች በኢትዮ ኬንያ ድንበር ቦሪ አቅራቢያ ተሻግረው ሁለት ኬንያዊንና ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን አግተው መውሰዳቸውን የቀጠናው ፖሊስ አስታውቋል። የመርሳቤት ግዛት የፓሊስ አዛዥ የሆኑት ሞፋት ካንጋ እንዳሉት ግለሰቦቹ ምን እንዳደረጉ ያወቅነው ነገር የለም። በእርግጥ በኦሮሞ ሕዝብና በኢትዮጵያ መንግስት መሃከል ችግር እንዳለ እናውቃለን። የታገቱትን ዜጎቻችንን እንደሚለቁና የወሰዱብንን ...
Read More »በዲላ ዩንቨርስቲ ቦምብ ፈንድቶ 2 ተማሪዎች ሲሞቱ በርካታዎች ቆሰሉ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) ሐሙስ ምሽት በዲላ ዩንቨርስቲ በደረሰ የእጅ ቦንብ ፍንዳታ ሁለት ተማሪዎች የሞቱ ሲሆን፣ በርካታ ተማሪዎችም ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ላይ እየወሰዱ ያለው የእስር ዘመቻና ግድያ ተቃውሞው በድጋሚ እንዲቀሰቀስ ማድረጉን ለመርዳት ተችሏል። ግድያ ይቁም የሚል መፈክሮችን በማሰማት ላይ የሚገኙት እነዚሁ ተማሪዎች የፅጥታ ሃይሎች ከትምህርት ...
Read More »ኢትዮጵያ ከህገወጥ ገንዘብ ተቋማት ጋር በተያያዘ በአመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣው ኢትዮጵያ ከህገ-ወጥ ንግድ ተቋማት ጋር በተያያዘ በየአመቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እያጣች እንደሆነ አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም ይፋ አደረገ። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2004-2013 26 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያጣችው ኢትዮጵያ ከዚሁ ገንዘብ መካከል 19.7 ቢሊዮን ዶላር ከህገወጥ ንግድ ጋር የተያያዘ መሆኑን ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተለጀንስ አስታውቋል። ሃገሪቷ ...
Read More »በአፋርና ሶማሌ ክልል የምግብ እጥረት አሳሳቢ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) በደቡብ የአፋር አካባቢና በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በድርቅ ምክንያት የተከሰተው የምግብ እጥረት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርብ አስታወቀ። በነዚህ አካባቢዎች የአደጋው አሳሳቢነት በደረጃ ሁለትና ሶስት ውስጥ ተመድቦ ቢቆይም፣ ይኸው አሃዝ ወደ ደረጃ አራት ከፍ ማለቱን የምግብ እጥረቱ የከፋ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። በእነዚሁ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ-አደሮች አፋጣኝ ...
Read More »የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት አባላት ማህበር አባላቱ ከህዝቡ ጎን በመሆን እንዲታገሉ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ታህሳስ ፣ 2008) የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አርበኞች ማህበር በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ድርጊት በማውገዝ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ህዝቡ እያካሄደ ካለው ትግል ጎን እንዲሰልፍ ጥሪን አቀረበ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት መብታቸውን በሚጠይቁ ሰዎች ላይ የሚወስደው የግፍ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጸው ማህበሩ፣ ህዝቡ ለሰላም ያለውን ተስፋም ጨልሞ እንደሚገኝ አስታውቋል። እያንዳንዱ የቀድሞ ሰራዊት አባላት በያለህበት ሆነህ በመደራጀትና ...
Read More »በአባይ ጉዳይ ላይ ያደረኩት ምንም ስምምነት የለም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስተባበለ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከግብፅ መንግስት ጋር የተደረሰ ምንም አይነት አዲስ ስምምነት የለም ሲል ሃሙስ አስተባበለ። የግብፅ ባለስልጣናት በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ ስምምነት መፈረሙንና የየትኛውም ሃገር በተናጥል በግዱቡ ላይ ምንም አይነት ስራ እንዳያከናውን ውሳኔ መደረጉን በመግለጽ ላይ ናቸው። ሁለት የፈረንሳይ አለም አቀፍ ተቋማት በግድቡ ላይ የሚያካሄዱት ጥናት እስኪጠናቀቅ ድረስ ግድቡን በውሃ የመሙላቱን ሂደት እንዳይካሄድ ፕሬዚደንት አልሲሲና በድርድሩ ...
Read More »