በኢትዮጵያ የምግብና የጤና ክትትል የሚፈልጉ ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች ቁጥር ሁለት ሚሊዮን ደረሰ

ኢሳት (ታህሳስ 19 ፣ 2008) በኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የድርቅ አደጋ ተከትሎ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ልዩ የምግብ ድጋፍና የቅርብ ክትትልን የሚፈልጉ ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች ቁጥር ወደ ሁለት ሚሊዮን አካባቢ መድረሱን የተባበሩት መግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። እነዚህ ተረጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ ካልቀረበላቸውም የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ እንደሚሆን ድርጅቱ አሳስቧል። ልዩ የምግብ ድጋፍና የጤና ክትትልን የሚፈልጉ ህጻናትና እናቶችን ቁጥር በቅርቡ ወደአንድ ሚሊዮን አካባቢ ደርሶ ...

Read More »

ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ የግብፅን ጥቅም የሚያስጠብቅ ስምምነት ፈረመች

ኢሳት (ታህሳት 19 ፣ 2008) ላለፉት ሶስት ቀናቶች በሱዳን ካርቱም 11ኛ ዙር ድርድራቸውን በአባይ ግድብ ዙሪያ ሲያካሄዱ የሰነበቱት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና፣ ሱዳን ባለፈው አመት በመሪዎች በመርህ ደረጃ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ማክሰኞ ገለጡ። ከግድቡ ጥናት ራሱን ባገለለው የኔዘርላንዱ ኩባንያ ምትክም፣ ሌላ ድርጅትን በመምረጥ ጥናቱ በአስቸኳይ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ሺንሃኣ ዘግቧል። ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ የሶስቱ ሃገራት መሪዎች ታሪካዊ ...

Read More »

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወጣቶቸ እያደኑ ማሰራቸውን ቀጥለዋል

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ እንደገና ባገረሸበት ማግስት አመጹን ደግፈዋል በሚል በክልሎች እና በአዲስ አበባ የተለያዩ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። በአንቦና ወለጋ ዩኒቨርስቲዎች በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያው የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ ከሚታወቁት መካከል ደግሞ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ዮናታን ተስፋየ በደህንነት ሃይሎች ታፍኖ ማእከላዊ እስር ቤት ...

Read More »

ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ በኪሳራ ምክንያት ከንግድ ባንክ መዋሃዱን ሰራተኞች ተናገሩ

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባንኩ ሰራተኞች እንደገለጹት ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እንዲዋሃድ የተደረገው ከጀርባው ያለውን የዘረፋ ወንጀል ሽፋን ለመስጠት ነው።ሰራተኞቹ በዘረፋው ወንጀል የበላይ የመንግስት አካላት እንዳሉበት ይገልጻሉ። ባንኩ በ2008 ዓም 12 ሚሊዮን ብር መክሰሩን የሚገልጹት ሰራተኞች ለኪሳራው ምክንያት ናቸው ያሉዋቸውን በርካታ የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረው አቅርበዋል። ባንኩ አገልግሎትን እንዲያቀላጥፍ በሚል ቲ 24 ...

Read More »

በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ለመሬት ዝርፊያ ከፍተኛ አመራሮችን ተጠያቂ አደረጉ

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚገኙት ከፍተኛ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችና የስራ ሂደት መሪዎች ለኢሳት እንደተናገሩት ‹‹ በእኛ ዘመን መሬት በየትኛውም አቅጣጫ በሙሰኞች እጅ መውደቁ ቁጭት ፈጥሮብናል፡፡ ››ይላሉ ፡፡ ትልቁን ሚና የሚጫወቱት የስርአቱ አመራሮች ናቸው ሲሉ ይወቅሳሉ። ከአደርባይነት የተላቀቀ አመራር ማግኘት ከፍተኛ የወቅቱ ችግር መሆኑን የሚናገሩት የስራ ሃላፊዎች በተለይ መሬት በከተሞች ላይ ትልቅና ፈታኝ ...

Read More »

ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ 5ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎች እንደታሰሩ ታወቀ

ኢሳት ዜና (ታህሳስ 18 ፣ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ቀጥሎ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች የተያዙ ሰዎች ቁጥር አራት ሺ አካባቢ መድረሱን የኦሮሚያ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሰኞ አስታወቀ። ለእስር ከተዳረጉት መካከልም 500 ያህሉ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሎዎች የሚገኙ አባላት መሆናቸዉን የኦፌኮ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ በቀለ ነገአ ለሀገር ዉስጥ መገናኛ ገልጸዋል። በሳምንቱ መገባደጃ ሁለት የስራ ...

Read More »

በድርቁ ምክንያት 400ሺ ህጻናት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው፣ አንድ ሚሊዮን ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 18 ፣ 2008) በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከ 400ሺ የሚበልጡ ህጻናትን ለአሳሳቢ የጤናና የአካል ችግር አጋልጦ እንደሚገኝና ጉዳት የሚደርስባቸው ህጻናት ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ። ለተረጂዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ በመቅረብ ላይ አለመሆኑ ችግሩን እያባባሰው እንደሆነም ድርጅቱ ገልጿል። ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ወደ ግማሽ የሚጠጉት ህጻናት ...

Read More »

ሲፒጄ በጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደው ያለው የእስር ዘመቻ እንዳሳሰበዉ ገለጸ

ኢሳት ዜና (ታህሳት 18 ፣ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቀሶ የነበረዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ መቀመጫዉን በዚህ በአሜሪካ ያደረገዉ CPJ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሰኞ አስታወቀ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለእስር የተዳረገዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራው በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ተቋሙ ጥሪዉን አቅርቧል። በአንድ ሳምንት ዉስጥ ለእስር ሲዳረግ ሁለተኛ ጋዜጠኛ የሆነዉ ...

Read More »

በማስተር ፕላን ላይ የተነሳት ተቃውሞ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ማገርሸቱ ታወቀ

ኢሳት ዜና (ታህሳስ 18 ፣ 2008) ከአንድ ወር በላይ የዘለቀውና፣ ለአንድ ሳምንት ጋብ ብሎ የሰነበተው ተቃውሞ፣ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ዳግም መቀስቀሱ ተገለጸ። በመላው ኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ጋብ ያለ ቢመስልም፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ሰሜን ሸዋ በተለያዩ ከተሞች ዩንቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ታውቋል። ባለፈው ዓርብ ማለትም በወለጋ ዩንቨርስቲ፣ በሰሜን ሸዋ ወረዳዎች፣ ቱሉ ሚልኪ እንዲሁም ...

Read More »

መንግስት በሃይል ሊያዳፍነው የሞከረው ተቃውሞ እንደገና አገረሸ

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ መንግስት አጋዚ የሚባለውን ጦሩን በማሰማራት ሊጨፈልቀው ያሰበው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደገና አገርሽቶ በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ተደብድበው ታስረዋል። ተማሪዎቹ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ወደ ጫካዎችና አጎራባች ከተሞች ቢያመልጡም ወታደሮቹ እግር በእግር እየተከታተሉ በመደብደብ አስረዋቸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ወታደሮቹ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ...

Read More »