ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮምሽኑ ያካሄደውና በይፋ ያልወጣው የጥናት ሰነድ እንደሚያመለክተው በኣለም ላይ ከእስያ ሀገራት ሲንጋፖር፣ሆንግ ኮንግ፣ ከአፍሪካ ቦስትዋናና ሞሪሺየስ በጸረ ሙስና ትግል በተጨባጭ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸው አመልክቶ ፣ እነዚህ ሀገራት ለውጤት የበቁት የፖለቲካ አመራሩ ለጸረ ሙስና ትግሉ ቁርጠኛ በመሆኑና ራሱንም ከሙስና በማራቁ እንዲሁም ለሙስና ምርመራ ቢሮዎች የሰጠው ድጋፍና ነጻነት ከፍተኛ በመሆኑ ...
Read More »የገናን በዓል አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሽንኩርት ዋጋ ከወትሮው በተለየ መልክ ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ፡፡
ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁሉም ዓይነት ሸቀጦች ላይ ጭማሪ መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የሽንኩርት ግን ከወትሮው የተለየ መሆኑን ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ተጠይቀውም “ከቦታው ስለማይገባ ነው” የሚል መልስ ከመስጠት ውጪ ዝርዝር ምክንያት ማቅረብ አልቻሉም፡፡ በዚሁ መሰረት የአበሻ ሽንኩርት በኪሎ ግራም ከ27 እስከ 30 ብር ፣ የፈረንጅ ከ10 እስከ 16 ብር ፣ ነጭ ሽንኩርት ከ50 ...
Read More »በኬኒያ 27 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ፍርድ ቤት ቀርበው የ9 ወራት እስራት ወይም 15 ሽህ የኬኒያ ሽልንግ መቀጮ ተፈረደባቸው
ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል ያላቸውን 27 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ወደ ደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ሰጥተን እናሻግራችኋለን ያሏቸውን ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪ ደላሎችን ፖሊስ ይዞ ኢምቡ ፍርድ ቤት አቀረበ። ከስደተኞቹ ውስጥ ሶስቱ የ13 የ14 እና 15 ዓመት ታዳጊዎች ሲሆኑ በደላሎች ዓማካኝነት ካለምንም ሕጋዊ ፈቃድ ድንበር ጥሰው በመግባታቸው ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔውም ...
Read More »በአሰላ ከተማ የግንቦት ሰባት የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት በተሳካ ሁኔታ ተበተነ
ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2008) የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀቶች በአርሲ አሰላ ከተማ በርካታ ቀበሌዎች ትናንት ማክሰኞች በተሳካ ሁኔታ ለህዝብ መድረሳቸው ተገለጸ። በአካባቢው የሚኖሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አስተባባሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በከተማው ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ከ1600 በላይ የሚሆኑ የትግል ጥሪ ወረቀቶች በከተማዋ ለሚኖረው ህዝብ እንዲደርስ ተደርጓል። ሕዝብ በሚያዘወትርባቸው በተለያዩ ግልጽ ቦታዎች የትግል የጥሪ ወረቀቶች ተለጥፈው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የተበተነውን ...
Read More »በኢትዮጵያ ለምግብ ድጋፍ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊዮን ደረሰ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) ከተያዘው ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ ለምግብ ድጋፍ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊዮን መድረሱን የብሄራዊ አደጋ መከላከያ ኮሚቴ ማክሰኞ ይፋ አደረገ። በአሁኑ ወቅት በድርቁ ምክንያት አስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ከተጋለጡት 10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተጨማሪ፣ ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በምግብ ራስ ማስቻል ፕሮግራም ድጋፍን እንደሚሹ ኮሚቴው ገልጿል። በተያዘው አመት በአገሪቱ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ባይከሰትም ወደ ስምንት ሚሊዮን ...
Read More »ሱዳን፣ ኢትዮጵያና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ስምምነት ዙሪያ በአዲስ አበባ ሊመክሩ ነው
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) ኢትዮጵያና ግብፅ ባለፈው ሳምንት በሱዳን በተፈራረሙት ስምምነት አተገባበር ዙሪያ የሚመክር ውይይት ረቡዕ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የግብፅ ባለስልጣናት ማክሰኞ አስታወቁ። ለሁለት ቀን በሚቆየው በዚሁ አስቸኳይ የውይይት መድረክ ግብፅ ያቀረበቻቸው አዳዲስ ሃሳቦች እንዴት ወደተግባር ሊለወጡ እንደሚችሉ የሚመክር መሆኑንም የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ገልጸዋል። የሃገሪቱ የመስኖ ልማት ሚኒስትር አማካሪ የሆኑት አላ ያሲን ሃገራቸው የወንዙን ፍሰት እንዳታስተጓጉል የሚያደርጉ ሃሳቦችን አቅርባ ...
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች በአማጺ ሃይሎች የተያዘውን ጁባላንድ ለመቆጣጠር ውጊያ ጀመሩ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) በሶማሊያ ታጣቂ ሃይል ቁጥጥር ስር የሚገኘው የጁባላንድ ግዛትን መልሶ ለመያዝ የኢትዮጵያ ወታደሮች ውጊያ መጀመራቸውን የሶማሊያ ባለስልጣናት ማክሰኞ ገለጡ። እሁድ ወደ ዋና ከተማዋ ኪስማዩ ከደረሱት ወታደሮች በተጨማሪም ወደ 300 የሚጠጉ ወታደሮች በግዛቲቱ ስር በምትገኘው ዋርዴር አካባቢ መድረሳቸውንም የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች መልሶ ለመያዝ ጥረት እያደረጉበት ያለው አካባቢ ባለፈው አመት በሴራሊዮን ሰላም አስከባሪ ሃይል ስር ...
Read More »ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር ወታደሮቿን አሰማራች
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) ሰሞኑን የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች የኬንያ ድንበርን በመጣስ ሁለት ኬንያውያንን ማገታቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ በድንበር አካባቢ ወታደሮች ማሰማራቷ ተገለጠ። የኢትዮጵያ ወታደሮች በሳምንት መገባደጃ በሞያሌ አካባቢ በምትገኘው የኬንያዋ ቦሪ መንግደር በወሰዱት በዚሁ እርምጃ ካገቷቸው ሁለት ሲቪሎች በተጨማሪ ጠመንጃዎችን እንዲወስዱ የማሳርቤት ግዛት ኮሚሽነት ሞፋት ካንኪ አስታውቀዋል። ጉዳዩ በሁለት ሃገራት ዲፕሎማቶች በኩል ክትትል እየተደረገበት ኣንደሚገኝ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ድርጊቱን ተከትሎ ኬንያ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ግድያው እና እስራቱ ቀጥሏል፥ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች እንዲተባበሩም ጥሪ ቀርቧል
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሊተገበር የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎችን መግደሉን፣ መደብደቡንና፣ ማዋከቡን አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። በኦሮሚያ ስላለው ስለወቅታዊ ሁኔታ አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር እንዲሰጡን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ፣ በመንግስት ሃይሎች ዜጎችን የማሰሩ ሄደት አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ተናግረዋል። ባለፈው እሁድ በሃገረማሪያም ይኖር የነበረ አንድ የኦፌኮ አመራርና ...
Read More »በኦሮምያ ዜጎች በህወሃት ንብረቶች ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ እየጣሉ ነው
ታኀሳስ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ህዘባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ሲሆን፣ ዜጎች በህወሃት ኩባንያዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ትንናት በምስራቅ ሀረርጌ ቆቦ ከተማ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ መሰላ ከተማም ተዛምቷል። የኢህአዴግ ወታደሮች በሚወስዱት ጭካኔ የተሞባለት እርምጃ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። የስርዓቱ ወታደሮች የሚወስዱት ጭካኔ የተሞላበት የሃይል እርምጃ ያሳሰባቸው የክልሉ ነዋሪዎች፣ የህወሃት ንብረት በሆነው ሰላም ...
Read More »