ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) የአክሰስ ሪል ስቴት እንዲሁም የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ መታሰራቸውን ከአዲስ አበባ የደረስን ዜና አመለከተ። በመንግስት ዋስትና ወደሃገር ቤት ከተመለሱ ወራት ብቻ ያስቆጠሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ተመልሰው የታሰሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይገለጽም፣ ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር የተያያዘ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሃይላንድ ውሃን በማምረት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በመግባት በንግዱ አለም ታዋቂ የሆኑት አቶ ...
Read More »የግቡፁ ፕሬዚዳንት ከመከላከያና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ መከሩ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) የግቡፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሃገራቸው የመከላከያና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ መምከራቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ። ሰኞ በተካሄደው በዚሁ ዝግ ውይይት ፕሬዚደንቱ በቅርቡ ተደርሰዋል በተባሉ ስምምነቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው መምከራቸውን አል-አህራም የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። ፕሬዚደንቱ ከከፍተኛ የመከላከያና የደህንነት ሃላፊዎች ጋር ምክክርን አካሄደዋል ቢባልም ውይይቱ በዚህ ደራጃ ለምን እንደተካሄደና በምን አበይት ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትን እንዲመሩ ተመረጡ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) ማክሰኞ በይፋ የተቋቋመንውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትን እንዲመሩ አንድ የመንግስት ባለስልጣን በዋና ፀሃፊነት ተመረጡ። በሃገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና አሳታሚ ድርጅቶችን ያስተዳድራል የተባለውን ይህንን ምክር ቤት በሃላፊነት ለመምራት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ገብረመድህን ለምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተመርጠዋል። ለጋዜጠኞች መብት መከበርና ለሙያው ድጋፍን ያደርጋል ለተባለው ለዚህ ምክር ቤት የረፖርተር ...
Read More »በሃረማያ ዩንቨርስቲ ዳግም የተቀሰቀሰውን አመጽ ተከትሎ ተማሪዎችና አርሶ-አደሮች ክፉኛ ተደበደቡ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) ሰኞ ሃረማያ ዩንቨርስቲ ዳግም የተቀሰቀሰውን የተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ ዩንቨርስቲው ትምህርት ማቋረጡን እማኞች ገለጡ። የጸጥታ ሃይሎች በተማሪዎች ላይ እየወሰዱ ባለው የሃይል እርምጃ በርካታ ተማሪዎች መደብደባቸውንና ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ተማሪዎች ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል። ከዚህ በፊት ለእስር የተዳረጉ ተማሪዎች እንዲፈቱ ጥያቄን ማቅረብ የጀመሩ በርካታ ተማሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚወስዱትን የሃይል እርምጃ እንዲቆም ጥያቄ ማቅረባቸው ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ ...
Read More »የኖርዌይ ኤምባሲ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በማገርሸቱ ዜጎች የጥንቃቄ እርምጃን እንዲወስዱ አሳሰበ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገ የኖርዌይ ኤምባሲ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዳግም በማገርሸቱ ምክንያት ዜጎች በክልሉ በሚያድርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃን እንዲወስዱ አሳስቧል። የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በቅርበት የምትከታተለው ኖርዌይ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ የጸጥታ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት በቅርቡ ለኤምባሲ ተወካዮች በሰጡት ማብራሪያ ተቃውሞው በቁጥጥር ስር ዉሏል ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። ይሁንና ...
Read More »በጅማ ዩኒቨርስቲ ቦንብ ሲፈነዳ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ተማሪዎች ተደብደቡ
ጥር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ተማሪዎች እንደገለጹት ፣ ትናንት ምሽት ላይ መብራት ከጠፋ በሁዋላ የእጅ ቦንብ የተወረወረ ሲሆን፣ ፍንዳታውን ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ተማሪዎች ማደሪያ ክፍል እየገቡ ደብድበዋቸዋል። በፍንዳታው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ተማሪዎቹ ፍንዳታውን ያደረሱት ወታደሮች ናቸው ይላሉ። ፍንዳታው ተቃውሞ ሊያሰሙ ይችላሉ በሚሉዋቸው ተማሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሆን ብሎ የተቀናበረ ...
Read More »በምስራቅ ሀረርጌ የተከሰተው ረሃብ የህልውና ስጋት መደቀኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል
ጥር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ረሃብ ገብቷል የሚሉት ነዋሪዎች፣ አስቸኳይ እርዳታ በፍጥነት ካልደረሰላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ሊያልቅ ይችላል። በገጠር አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ወደ ከተሞች መሰደድ ጀምሯል። ምንጮችና ወንዞች በመድረቃቸው ውሃ ለማግኘት አልተቻለም ሲሉ የውሃ እጥረት ለመሰደዳቸው ዋና ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። አንዳንድ አርሶአደሮች ከብቶቻቸውን እየሸጡ ችግሩን ለማሳለፍ እየሞከሩ ቢሆኑም፣ የከብቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ...
Read More »ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሁሉም ዜጋ በኅብረት እንዲቆም አገራዊ ጥሪ አቀረበ
ጥር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን ለመቀየር እያንዳንዱ ዜጋ ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለመጣል በአንድነት በፅናት መታገል እንደሚገባው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአቋም መግለጫውን ጠቅሷል። “መብታቸው ለተረገጠ፤ ለተገፉ፤ አድሎ ለተፈጸመባቸው፤ ስብዓዊ መብታቸው ለተገፈፉ ዜጎች መቆም ያለብን ወቅት ላይ ነን። መደራጀትና የትኩረት አቅጣጫችንን የጋራ በሆኑ እሴቶችና ግቦች ላይ ማተኮር ያለብን ጊዜ ቢኖር ዛሬ ነው። እያንዳንዳችን ...
Read More »ህወሃት/ኢህአዴግ የዘር-ፍጅት በመቀስቀስ ላይ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገለጹ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሁለት ወራት ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የዘር ፍጅት በመቀስቀስ የተቃውሞውን አቅጣጫ ለመቀየር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ታማኝ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የዘር ፍጅት እቅዱ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች በተለይም በአማሮች ላይ የተነጣጠረና የተቀነባበረ ጥቃት በመሰንዘር፣ የሌላ አካባቢ ተወላጆች በስጋት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ በማድረግ ሁኔታውን ወደ እርስ-በእርስ ግጭት ...
Read More »ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር ተጨማሪ ወታደሮችን አሰማራች
ኢሳት (ጥር 2 ፣ 2008) በኢትዮጵያና የኬንያ ድንበር አካባቢ በሳምንቱ መገባደጃ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ኬንያ ተጨማሪ ወታደሮችን በድንብር ዙሪያ አሰማራች። ከኢትዮጵያ የዘዘቁ ታጣቂዎች ቅዳሜ አንድ የኬንያ ተጠባባቂ ባልደርባን የገደሉ ሲሆን፣ በድርጊቱም በርካታ የቤት እንስሳትቶችም እንደተወሰዱ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው ገብተዋል የተባሉ ታጣቂዎች በአንድ ተሽከርካሪ ላይ የተኩስ እርምጃ በመክፈት አብዲ ኤደን የተባለ የሃገሪቱ ተጠባባቂ ሃይል ባልደርባ መገደሉን የማርሳቤት ...
Read More »