ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በአዮዲን የበለጸገ ጨው የሚጠቀመው ህዝብ 23 በመቶ ያህል መሆኑን ከኢትዮጵያ የምግብ መድሀኒትና ፋርማሱዪቲካል ልማት ኢንስቲትዪት የተገኘ ጥናት አመልክቷል። አብዛኛው ህዝብ በአዮዲን የበለፀገ ጨው ማግኘት ባለመቻሉ የእንቅርት በሽታን ጨምሮ የህጻናት አእምሮና እድገት ዝግመትን፣ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ ውርጃንና የመሳሰሉ ችግሮችን በማስከተል ላይ ይገኛል። መንግስት ቁጥሩን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው ብሎአል። በአሁኑ ...
Read More »ኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ሊያነሳ እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ከጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኦህዴድ በመላው የኦሮሚያ አካባቢ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ አመራር እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚው ግምገማውን ...
Read More »በኢትዮጵያ እየደረሰ ባለው የትራፊክ አደጋ በእሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈ ነው ተባለ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ባለፉት ሶስት ወራቶች ብቻ በደረሱ የትራፊው አደጋዎች ከ1ሺ 100 በላይ ሰዎች በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች መሞታቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለጠ። ይኸው ቁጥር በአመቱ መጨረሻ 4ሺ 600 ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅና፣ በሃገሪቱ እየደረሰ ያለው የትራፊክ ጉዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሚኒስትሩ ማስታወቁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ በሃገሪቱ በአመት 2ሺ 500 ሰዎች ...
Read More »የግብፁ ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ሊመክሩ አርብ አዲስ አበባ ኣንደሚገቡ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2018) የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ሃገራቸው በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ይረዳት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በአዲስ አበባ እንደሚመክሩ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። በቅርቡ በካርቱም ስምምነት የተደረገባቸው አዳዲስ የመግባቢያ ሃሳቦችም በዚሁ ውይይት ላይ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። አርብ እረፋድ ላይ አዲስ አበባ ይገነባሉ ተብለው የሚጠበቁት የግብፁ ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ...
Read More »በኦሮሚያ በማስተር ፕላን አማካኝነት የተነሳው ተቃውሞ በድጋሚ ማገርሸቱ ታወቀ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ከማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ከሳምንት በፊት በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ የተቀሰቀሰው ዳግም ተቃውሞ መቀጠሉ ተገልጿል። በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በማውገዝ ሃሙስ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ተመሳሳይ ተቃውሞዎችም በሰሜን ሸዋ አካባቢ በሚገኙ ከተሞች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል። ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ፓርላማ በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግድያና ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ልዩ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተከትሎ ከፍተኛ የጸጥታ ሃይል ተሰማራ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ልዩ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተከትሎ በመዲናው በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱን ነዋሪዎች ገለጡ። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው የጸጥታ ቁጥጥር በተጨማሪ በሰበታ፣ ጫንጮና አካባቢዋ ባሉ የገጠር መንደሮች የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸው ታውቋል። በእነዚህ አካባቢዎች ባለፈው ወር ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድባቸው የነበረ ...
Read More »ኢትዮጵያ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈጸምባቸው አገራት አንዷ መሆኗ ይፋ ሆነ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ኢትዮፕያ በአለማችን ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው ከተጠኑ 168 ሃገራት መካከል 103ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያካሄደው ትራስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሃሙስ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ። ሃገሪቱም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ይፈጸምባቸዋል ተብለው በቀይ ቀለም ከተቀመጡት ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗንም ሪፖርቱ አመልክቷል። አውሮፓዊቷ ዴንማርክ በአለማችን ሙስና በጣም አነስተኛ ሁኔታ የሚፈፀምባት ሃገር ተብላ በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን ሶማሊያና ሰሜን ...
Read More »የምግብ አቅርቦት እጥረት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች አሳሳቢ የሆነ የምግብ አቅርቦት እጥረት አጋጥሟቸው እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃሙስ አስታወቀ። በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ውስጥም ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ የእርዳታ አቅርቦት የማይገኝ ከሆነ በርካታ ተረጂዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ድርጅቱ መግለጹን ዴይሊ ሜይል ጋዜጣ ዘግቧል። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ወቅታዊ ምላሽ ባለማድረጉ የተረጂዎች የእለት ከእለት ...
Read More »ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝና በፖለቲካ ነጻነት ነጻ ካልሆኑ አገራት ተርታ ተመደበች
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች በመገደብ ነጻ ካልሆኑ አገራት መመደቧን ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም ዛሬ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ገለጸ። ፖለቲካዊ መብቶችን እና የሲቪል ነጻነትን አስመልክቶ የተሰራው ይኸው የዘንድሮው 2016 የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ የዜጎችን ፖለቲካዊ መብቶችን በመጨፍለቅ ቀዳሚ አገር እንደሆነች በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል። በተመሳሳይ መልኩም የዜጎችን ነጻነት ካለፈ አመት በባሰ መልኩ እጅግ እንደተሸረሸረ ...
Read More »የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኦሮምያን ሙሉ በሙሉ አረጋግተናል ባለ ማግስት ተቃውሞ ተነሳ
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ፣ በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በመገናኛ ብዙሃን ባስታወቀ ማግስት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። የተቃውሞዎች ዋነኛ አጀንዳ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስረዛ ወደ ሌሎች የመብት ጥያቄዎች ተሸጋግሯል። በጉጂ ፣ ሰሜን ሸዋና ምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች፣ ነዋሪዎች የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ለወራት በዘለቀው ተቃውሞ ግድያ፣ ...
Read More »