(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከ2 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ታስረው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ። አቃቢ ሕግ ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ኣንዲለቀቁ ያደረገው በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ እመሰክራለሁ በማለታቸው እንደሆነ ጉዳዩን ለሚከታተለው ችሎት ገልጿል። ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 የስኳር ፕሮጀክት ለዚሁ ተብሎ የተመደበውን በጀት ተቀናሽ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ...
Read More »ሳውዲአረቢያ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ ፈቀደች
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010)በአለም ላይ ሴቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ በሕግ ክልከላ ያደረገችው ብቸኛ ሀገር ሳውዲአረቢያ እገዳውን በማንሳት ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ ፈቀደች። የሳውዲው ንጉስ ሳልማን እገዳውን በማንሳት ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ መፍቀዳቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአድናቆት ተቀብለውታል። የሴቶችን መብት ለማክበር አዎንታዊ ርምጃ ሲሉም ገልጸውታል። ሴቶች መንጃ ፈቃድ ማውጣት እንዲችሉ የሚፈቅደው ይህ የንጉሱ ውሳኔ ከ10 ወራት በኋላ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሰኔ 24/2018 ጀምሮ ተግባራዊ ...
Read More »በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አስታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010)በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የማጣራት ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑንም ሃላፊው ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጎረቤት ሶማሌ ላንድ የሚኖሩ ከሶስት ሺ የሚበልጡ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን መንግስት በይፋ አስታውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ...
Read More »የብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) የብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በ4ኛ ቀን ውሎው በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ። የራያ ጉዳይ ተጨምሮበት ስብሰባው በጭቅጭቅና ሃይለቃል በተሞላበት ምልልስ በቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የግጨው፣የወልቃይትና የራያ ጉዳይ እያለ ሌላ አጀንዳ አያስፈልገንም ያሉት ተሳታፊዎች የብአዴንን መሪዎች በጥያቄ ወጥረው መያዛቸው ተሰምቷል። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ የሚወረወሩት ተራ የሚባሉ አይነት ስድቦች ስብሰባውን የከፋ እንዲሆን ማድረጉን ...
Read More »ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ። በህወሃት መንግስት የእጅ አዙር ትዕዛዝና ግፊት በኦህዴድ አስፈጻሚነት በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለው ማፈናቀል ሕጻናትን ጨምሮ ነፍሰጡር እናቶችና ደካማ የሆኑ አዛውንቶች ከፍተኛ ጉዳት ላይ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ወገናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቀው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈናቀሉት የሲዳማ ብሔር ተወላጆችን ቀይ መስቀል ለጊዜው እየረዳቸው ...
Read More »የደመራና የመስቀል በአል በድምቀት ተከበረ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) በኢትዮጵያና በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ምዕመናኑ የደመራን በአል በድምቀት አከበሩ። የመስቀልም በአልም በመላው ኢትዮጵያ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ውሏል። በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በከፍተኛ ድምቀት የተከበረው የደመራ በአል ከኢትዮጵያ ውጪ በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ብዙ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል። ከአሜሪካ ርዕሰ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ በተጨማሪ በሌሎች የአሜሪካ ከተሞች ሎስአንጀለስ፣ ...
Read More »የትነበርሽ ንጉሴ የስዊዲን አማራጭ የኖቤል ሽልማትን ተቀዳጀች
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) የሰብአዊ መብት ጠበቃና የሕግ ባለሙያ የትነበርሽ ንጉሴ የስዊዲን አማራጭ የኖቤል ሽልማትን ተቀዳጀች። ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ የተባለውን ሽልማት ያገኘችው የትነበርሽ ንጉሴ ከሁለት ሌሎች የአማራጭ ኖቬል አሸናፊዎች ጋር 374 ሺህ ዶላር ገንዘብ ትካፈላለች። የትነበርሽ ንጉሴ ሽልማቱን ያገኘችው ከ5 አመት የልጅነት እድሜዋ ጀምሮ ሊከላከሉት በሚችሉት በሽታ ምክንያት አይነ ስውር ብትሆንም በጥረቷ ስኬታማና ሌሎችንም የአካል ጉዳተኞች በመረዳት ላበረከተችው አስተዋጽኦ ነው። ገና ...
Read More »በሌብነት የተጠረጠሩ አራት የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤቶች ከሀገር ማምለጣቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) በሌብነት የተጠረጠሩ አራት የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤቶች ከሀገር ማምለጣቸው ታወቀ። ሆኖም በሌሉበት በአራቱም ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ መመስረቱ ታውቋል። የኮንስትራክሽን ድርጅቶቹ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሃላፊዎች ጋር በመሆን በ2 ቢሊየን 150 ሚሊየን ብር ዘረፋ ተጠያቂ መሆናቸው ተመልክቷል። በሌብነት ተጠርጥረው ሲፈለጉ ከሀገር በማምለጣቸው ፍርድ ቤት ያልቀረቡት የሳትኮን ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ተክላይ፣የገምሹ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ እንዲሁም የዲ ኤም ...
Read More »መንግስት የብርን ዋጋ በመቀነስ የገጠመውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመከላከል የመጨረሻ ጥናት ማዘጋጀቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) በኢትዮጵያ የተደቀነውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና አመታዊ የዕዳ ክፍያ በተመለከተ መንግስት የብርን ዋጋ በመቀነስ ለመሻገር የመጨረሻ ጥናት ማዘጋጀቱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በዚህ አመት መንግስት ሊከፍለው የሚገባውን ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ እዳ ለመሸፈን የኢትዮጵያ ሒልተን ሆቴልን ለመሸጥ ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል። ኢትዮ-ቴሌኮምን ለኬንያው ሳፋሪ ኮም 50 በመቶ ለመሸጥ አንዳንድ ባለስልጣናት በሚስጥር መነጋገራቸውንም የደረሰን ዜና ያስረዳል። የብር ዋጋ ቢቀንስ የወጭ ...
Read More »በብአዴን ድርጅታዊ አመራር አባላት መካከል የተከሰተው ውዝግብና አለመግባባት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/20015) በብአዴን ድርጅታዊ አመራር አባላት መካከል የተከሰተው ውዝግብና አለመግባባት ተባብሶ መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። የድርጅቱ ማእከላዊ አባላት እና የክልሉ ምክር ቤት ሳይስማሙበት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተፈራረሙት የግጨው ስምምነት ለውዝግቡ ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ተገልጿል። የሞባይል ስልክ እንዳይገባ ተደርጎ በሚስጥርና በጭቅጭቅ የተካሄደው የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት ስብሰባ የቃላት ልውውጥ ደርሶናል። የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ፕሬዝዳንቶች የተፈራርሙት የግጨው ስምምነት በተወሰኑ ሰዎች ...
Read More »