ዮዌሪ ሙሴቬኒ ዶናልድ ትራምፕን አደነቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) አሜሪካ በታሪኳ ካገኘቻቸው ምርጥ ፕሬዝዳንቶች አንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ሲሉ የዩጋንዳው መሪ ዮዌሪ ሙሴቬኒ ገለጹ። ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካን በተመለከተ በግልጽ በመናገራቸው ወድጄያቸዋለሁ በማለት ከቅሬታና ተቃውሞ ይልቅ አድናቆት ቸረዋቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ በኢሚግሬሽን ጉዳይ ላይ በዚህ ወር መጀመሪያ በኋይት ሃውስ በተደረገ ስብሰባ የአፍሪካ ሀገራትን ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው ይታወሳል። አፍሪካን በተመለከተ ዶናልድ ትራምፕ በግልጽ በመናገራቸው ወድጄያቸዋለሁ በማለት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አስተያየታቸውን ...

Read More »

ለትግራይ ተወላጆች የተዘጋጀው ፌስቲቫል ተሰረዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በውጭ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በከፍተኛ ወጪ ያዘጋጀው ፌስቲቫል ተሰረዘ። በመጪው ሃምሌ በመቀሌ ሊካሄድ የነበረው ፌስቲቫል የተሰረዘው በሕወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ክፍፍል ጋር በተያያዘ እንደሆነ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል። ሆኖም ለትግራይ ተወላጆች የተላለፈው መልዕክት ፌስቲቫሉ የተሰረዘው በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ነው የሚል ነው። በአቶ አባይ ወልዱ የሕወሃት ሊቀመንበርነትና በርሳቸው ቡድን የበላይነት ወቅት የተደረገው ይህ ጥሪ በአይነቱ ልዩና ...

Read More »

ህዝብን በመጨፍጨፍ ትግሉን ለመቀልበስ አይቻልም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) ህዝብን በመጨፍጨፍ ትግሉን ለመቀልበስ አይቻልም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ በወልዲያ በህወህት ታጣቂዎች የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ ። ትግሉን ከአሁኑ በተሻለ ህዝቡና ታጋይ ሃይሎች አዲስ መርሀግብር በመንድፈ በጋራ መታገል ይኖርብናል በማለት ጥሪውን አቅርቧል። በተመሳሳይ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ በወልዲያ የተፈጸመውን ጥቃት ትውልድ ላይ የተቃጣ ብሔራዊነትን አደጋ ላይ የጣለ ሲል መግለጫ አውጥቷል። የ2010 የጥምቀት በዓል በአብዛኛው የሀገሪቱ ...

Read More »

አራት ተከሳሾች ተፈረደባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) መንግስት ክሳቸውን ሰርዞ እፈታቸዋለሁ ካላቸው 115 እስረኞች መካከል 4ቱ ችሎት ቀረበው እንደተፈረደባቸው ታወቀ። ይፈታሉ ተብሎ ስማቸው ከተጠራውና ለስልጠና ወደ ቃልቲ ተውሰደ ከነበሩት 115 እስረኞች መካከል እንደነበሩም ታውቋል። ነገ ግን ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነዚሁ ክሳቸው ተነስቶላቸዋል የተባሉት 4 ተከሳሾች ቀርበው የተላለፈባቸውን ፍርድ እንዲሰሙ መደረጉ ታውቋል። የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው እንዲህ አይነቱ አካሄድ ...

Read More »

በመተማ ከተማ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) በሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ከተማ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ። ትላንት ምሽት በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት የህወሃት አባል በሆነ ግለሰብ ሆቴል ላይም ጉዳት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል። በሆቴሉ የህወሃት አገዛዝ የቀጠናው የደህንነት ሃላፊዎች ስብሰባ ያደርጉ ነበር ተብሏል። በተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የከተማዋ ሁለት ባለስልጣናት ወደ ጎንደር ሆስፒታል መወሰዳቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባልታወቁ ሃይሎች የተፈጸመውን ይህን ጥቃት በተመለከተ በመንግስት በኩል የተባለ ...

Read More »

በወልቂጤ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ዛሬ የተካሄደው ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ ቢጀመርም ልዩ ሃይል ሰዎችን ማሰሩን ተከትሎ ወደ ግጭት መቀየሩን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወልቂጤ ከተማ ሊገነባ የመሰረት ድንጋይ የተጣለለት ሆስፒታል ፕሮጀክት ወደ ትግራይ ተወስዷል የሚል መረጃ ህዝቡ ዘንድ መድረሱ ለተቃውሞው መቀስቀስ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር ትርቃለች። ወደ ...

Read More »

የሃይማኖት አባቶች አወገዙ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) በወልዲያ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሃይማኖት አባቶች አወገዙት። በውጭ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገር ቤት የሚገኘው ቤተክህነት በጉዳዩ ላይ ዝምታን መመረጡ እጅግ እንዳሳዘናት በመግለጽ መግለጫ አውጥታለች። የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ኢማም ሼህ ካሊድ ኡመር የከፋ እልቂት ከመከሰቱ በፊት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሰከን እንዲል ጥሪ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ መስራች ወንጌላዊ ዳንዔል ጣሰው ግድያውን የፈጸሙ ለፍርድ እንዲቀርቡ ...

Read More »

ኬንያ ወደ ጠፈር ሳተላይት ልታመጥቅ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) ኬንያ ወደ ጠፈር ሳተላይት ለማምጠቅ ዝግጅት መጀመሯ ታወቀ። የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ኬንያ በመጪው መጋቢት ወር የምታመጥቀው ይህ ሳተላይት የባህር ዳርቻዎቿን ለማሰስና የግብርና ስራዎቿን ለማገዝ እንደሚጠቅማትም ይፋ ሆኗል። ከአፍሪካ ሃገራት 8ኛ በመሆን ሳተላይት የምታመጥቀው ኬንያ የጃፓን የህዋ ምርምር ማዕከል የሙያ ምክር እንዲሁም በጃፓን መንግስት የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደርጎለታል። ነገር ግን ይሄ ድጋፍ ቢደረግለትም ሳተላይቱን ሙሉ በሙሉ ሰርተው ...

Read More »

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 3 እጩዎች ለትምህርት ሚኒስቴር አስተላለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመራር ቦርድ የሕወሃቱን እጩ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ካህሳይን ጨምሮ 3 እጩዎችን ለትምህርት ሚኒስቴር አስተላለፈ። ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት በኦሕዴድ ከታጩት ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ በተጨማሪ ዶክተር ጄይሉ ኡመር ሁሴንም በእጩዎች ውስጥ ተካተዋል። ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትነት ሕወሃትና ኦህዴድ መፋጠጣቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትን ለመምረጥ ብቃትን መሰረት ባደረገ መልኩ ውድድር እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣንን የሚመሩት የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አባላት ናቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የሚባለውንና ለመገናኛ ብዙሃን ፈቃድ የሚሰጠውን ተቋም ሙሉ በሙሉ የሚመሩት የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አባላት መሆናቸው ተጋለጠ። የሕወሃትን ቀውስ ተከትሎ እየተበተነ ያለው መረጃ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚሰሩ እንዲሁም በግል መገናኛ ብዙሃን የሚሳተፉ የሕወሃት አባላት ዝርዝርም ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ በግል እንዲሁም በማህበረሰብ ለሚሰሩ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንዲሁም የሕትመት ሚዲያዎች ፈቃድ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የተባለውን ተቋም የሚመሩት ...

Read More »