የስዊዲን መንግስት የኢትዮጵያን አምባሳደር ጠርቶ አነጋገረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) የስዊዲን መንግስት የኢትዮጵያን አምባሳደር ጠርቶ ማነጋገሩ ተገለጸ። የስዊዲን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አምባሳደሩን የጠራው በቂሊንጦ እስር ቤት በሚገኙት በዶክተር ፍቅሩ ማሩ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር መሆኑን የስዊዲን ጋዜጦች ዘግበዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ስለተጓተተው የዶክተር ፍቅሩ ማሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ ቀርበው እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። ስዊዲን በዶክተሩ የፍርድ ቤት መራዘም ምክንያት በግልጽ ቅሬታ እንዳደረባት ለአምባሳደሩ ማሳወቋን ጋዜጦቹ ጠቅሰዋል። ...

Read More »

ለዋልድቦ መነኮሳት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድቦ መነኮሳት የክህነት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን ተከትሎ አቤት በማለታቸው ለውሳኔ ዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢደረግም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን አላየነውም በሚል ለመጋቢት 10 /2010 ተለዋጭ ቀጥሮ መስጠቱ ታወቀ። አባ ገብረኢየሱስ ያሉበት ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። በመነኮሳቱ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያኒቱም ሆነች ምእመናኑ ዝም ማለታቸው አነጋጋሪ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል። ሁለት ግዜ በምህረት ይለቀቃሉ ተብሎ ነገር ግን የፍርድ ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) በመላ ኢትዮጵያ የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። ዛሬም ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችና ሊጭኑ በጉዞ ላይ የነበሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች በየመንገድ ዳሩ ቆመው እንደሚታዩም ተገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል የሚገባው የነዳጅ ስርጭትም ከፍተኛ መስተጓጎል እንደተፈጠረበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የተጠራውን ዘመቻ በመጣስ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተሽከርካሪ በጎጃም አማኑዔል በተባለ አካባቢ ከጫነው ነዳጅ ጋር መቃጠሉ ታውቋል። አገዛዙ ግን ምንም ...

Read More »

በአዲስ አበባ አሽከርከሪዎች የነዳጅ ማደያዎችን አጨናንቀው ዋሉ

በአዲስ አበባ አሽከርከሪዎች የነዳጅ ማደያዎችን አጨናንቀው ዋሉ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) ቄሮ ለአንድ ሳምንት የጠራውን ነዳጅ አቅርቦት እቀባ ተከትሎ በአዲስ አበባ ነዳጅ ለመቅዳት የፈለጉ አሽከርከሪዎች ማደያዎችን አጨናንቀው ታይተዋል። ቄሮ ነዳጅ በሚያመላልሱ ቦቴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ካስጠነቀቀ በሁዋላ፣ በአገሪቱ የነዳጅ እጥረት ሊፈጠር ይችላል ብለው የሰጉ አሽከርካሪዎች፣ ነዳጅ ማደያዎችን አጨናንቀው ታይተዋል። ምንም እንኳ እስካሁኑ ሰአት ድረስ በነዳጅ ማመላለሻ መኪኖች ...

Read More »

የሶማሊው ክልል መሪ አቶ አብዲ ሙሃመድ ከቀብሪበያህ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራ ቤተሰብ አባላትን አሰረ።

የሶማሊው ክልል መሪ አቶ አብዲ ሙሃመድ ከቀብሪበያህ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራ ቤተሰብ አባላትን አሰረ። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) እርምጃው የተወሰደው በውጭ ያሉ የዲያስፖራ አባላት በቅርቡ በሚካሄደው የሶህዴፓ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ለማስገደድና ለፕሬዚዳንቱ ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ለማስገደድ ነው። ከታሰሩት መካከል የ90 ዓመት አዛውንት ሳይቀር ይገኙበታል። በርካታ ወላጆች መታሰራቸውን ተከትሎ፣ ህጻናት ቀንና ሌሊት በጸሃይና በብርድ እንዲቀጡ እየተደረገ ነው። ምንጮች እንደገለጹት ...

Read More »

የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ተመልክቶ የቀረበው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው

የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ተመልክቶ የቀረበው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ፣ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አማኑኤል አብርሃም ፣ አቶ አጽብሐ አረጋዊ ፣ የሰብአዊ መብት ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር በተገኙበት የወቅቱን የሀገሪቱን ሁኔታ ተመልክቶ በአገዛዙ የቀረበው ስምንት ነጥቦችን የያዘው የእቅድ ዝርዝር ተቃውሞ አጋጥሞታል። በስብሰባው ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

በእስር ላይ የሚገኙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መስፋፋትና የመሬት ቅርምት በመቃወማቸው ብቻ ከሚማሩበት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከታሰሩ ተማሪዎች ውስጥ የተወሰኑት ቢፈቱም ቀሪዎቹ አስታዋሽ አጥተው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ፋኩልቲ ተማሪ የሆኑት ወየቻ ታምሩ፣ ወሰኑ ገረመው፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ፣ ገዳ ገመቹ፣ ኢዮብ ሙሊሳ እና ...

Read More »

ሬክስ ቴለርሰን ከስልጣን ተሰናበቱ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ  ሚኒስትራቸውን  ሬክስ ቴለርሰንን ከስልጣን አሰናበቱ ፡፡ በምትካቸውም የሲ አ ይ ኤ ዳይሪክተር ማይክል ፖምፒኦን  መተካታቸውን አስታውቀዋል። ሬክስ ቴለርሰን ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሃገራትን ጎብኝተው በተመለሱ ማግስት ነበር የስንብታቸው ዜና የተሰማው። የዩኤስ አሜርካው ሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  የአሜሪካው የሰለላ ድርጀት ዳይሬክተር  የሆኑትን የ54 ዓመቱን ማይክል ፖምፒኦን  የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን ያስታወቁት ...

Read More »

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ። አደጋው የደረሰው በደቡብ ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ገነቴ ሰላም በር በታባለ ቦታ ነው። በአደጋው የ38 ሰዎች ሕይወት ከማለፉ በተጨማሪ 10 ሰዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ተጎጂዎቹ በአቀስታ ሕዳር 11 እና ...

Read More »

የምርት ገበያ የግብይት መጠኑ በ40 ሺ ቶን ቀነሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) የምርት ገበያ በሁለት ወር ውስጥ ብቻ የግብይት መጠኑ በ40 ሺ ቶን ቀነሰ። በሃገሪቱ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ለግብይቱ መቀነስ ዋነኛ ምክንያት ተደርጓል። የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት የየካቲት የግብይት አፈጻጸም የሚያሳየው ሪፖርት እንዳመለከተው የግብይት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ  መሄዱን የምርት ገበያ መረጃዎች አመልክተዋል። በየካቲት ወር የነበረው ግብይት ካለፈው ጥር ጋር ሲነጻጸር 28 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። የየካቲት ወር ግብይት በታህሳስ ...

Read More »