የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው በደቡብ ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ገነቴ ሰላም በር በታባለ ቦታ ነው።

በአደጋው የ38 ሰዎች ሕይወት ከማለፉ በተጨማሪ 10 ሰዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ተጎጂዎቹ በአቀስታ ሕዳር 11 እና በደሴ ሪፈራል ሆስፒታሎች የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገልጸዋል።

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሱ 48 ሰዎችን አሳፍሮ ለጋምቦ ወረዳ ቀበሌ 07 ልዩ ስሙ ገነቴ ሰላምበር በተባለ ቦታ 5 ሜትር ቁልቁለት ላይ ዘሎ በመግባቱ አደጋው መድረሱ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ የአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚሞቱና ለከፋ አደጋ እንደሚዳረጉ ይነገራል።