(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010) የትግራይ ተወላጆች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን ባቋቋሙት ዳሎል ባንክ ውስጥ ባለድርሻ ተደርገው ስማቸው የተጠቀሰው የአማራው ባለሃብት አቶ በላይነህ ክንዴ በባንኩ ውስጥ ምንም ድርሻ እንደሌላቸው ገለጹ። ይህም የትግራይ ተወላጆች በባንኩ ወስጥ ያላቸውን የ 63 በመቶ ድርሻ ይበልጥ ከፍ የሚያደርገው ሆኖ ተገኝቷል፥ባንኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃብት ለመንቀሳቀስ በመወሰን መቁቋሙንም ኢሳት ምንጮችን በመጥቀስ ባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ ...
Read More »አቶ እውነቱ ብላታ ከሃላፊነታቸው ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010) በብራስልስ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በቅርቡ ተሹመው የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ ከሃላፊነታቸው ተነሱ። የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ምክንያቶች የአምባሳደሮች ጥሪና ሽግሽግ ማካሄዱን አስታወቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎም በሪያድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተነስተው በሌላ እንዲተኩ መደረጉ ተሰምቷል። ወይዘሮ አስቴር ማሞና አቶ እውነቱ ብላታ ከእነ ባለቤቶቻቸው በአንድ ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት ከእስር ይፈታሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010)የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ዶክተር አብይ አሕመድ ትላንት በብሔራዊ ቤተመንግስት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ባካሄዱት ውይይት እንዳሉት ኢትዮጵያ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰሯ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አጥታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተበላሸውን ኢሕአዴግ የማስተካከል ርምጃ እየወሰድኩ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው ስነስርአት ላይ እንደተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ኢሕአዴግ ማሰሩ ...
Read More »በቴፒ በሚካሄደው ተቃውሞ በርካታ ንብረት ወደመ
በቴፒ በሚካሄደው ተቃውሞ በርካታ ንብረት ወደመ (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በሾንጋ ግቢ ውስጥ ከሴት ተማሪዎች መደፈር ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ተቃውሞ ወደ ሚዛን አማን ከተማ ተዛምቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ንብረት መዘረፉንና መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የግቢው ውሃ በሚጠፋበት ጊዜ ሴት ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ሲወርዱ በአካባቢው ጎረምሶች በተደጋጋሚ እንደሚደፈሩ፣ ትናንት ደግሞ ሁለት ወንዶች ...
Read More »ህወሃት ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሳዕረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው
ህወሃት ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሳዕረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሰዓረ መኮንን ለማስተካት ህወሃት ግፊት እያደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በትግራይ ብሄርተኝነት ጽንፍ አቋም አላቸው የሚባሉት ጄ/ል ሰዓረ ኢታማዦር ሹም ሆነው የሚሾሙ ከሆነ፣ በኦህዴድና ...
Read More »በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡
በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ክፍል ተብሎ በአዲስ መልክ በተዘጋጃው የሂሳብ መማሪያ መጽሃፍ ላይ ሆን ተብሎ የትግርኛ ማብራሪያ መለጠፉ በክልሉ መምህራንና ተማሪዎች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መሆኑን ምሁራን ተናገሩ፡፡ ከአሁን በፊት በብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ተከስቶ የነበረው ስህተት፣የክልሉ መስህብ ቦታ ስለሆነው የራስ ዳሸን ተራራ መገኛ ...
Read More »በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነብሮ ገዳዮችና አስገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቁ።
በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነብሮ ገዳዮችና አስገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቁ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪቃ ለተቸገሩ ወገኖቹ ቀድሞ በመድረስ የሚታወቀው ገዛኸኝ ገብረመሰቀል ወይም ነብሮ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ እንደ አለኝታና መከታ የሚታይ ተወዳጅ ሰው ነው።ሜይል ኤንድ ዘጋርዲያን-ህልፈቱን ተከትሎ ባጠናቀረው ሰፊ ሀተታ እንዳስነበበው። ይህ ሀገር ወዳድ የቁርጥ ቀን ልጅ የዛሬ ወር አካባቢ ነበር በቅጥረኞች የመገደሉ ዜና የተሰማው። ...
Read More »የተለያዩ ሀገራት 200 አትሌቶች ጥገኝነት ጠየቁ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) ለስፖርታዊ ውድድር አውስትራሊያ የገቡ 200 የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ጥገኝነት ጠየቁ ። ለኮመን ዌልዝ ውድድር ባለፈው ሚያዚያ አውስትራሊያ የገቡት ከ200 የሚበልጡት አትሌቶች ጥገኝነት የጠየቁት ወደ ሃገራቸው ቢመለሱ ስቃይ እንደሚደርስባቸው በማመናቸው ነው። ብሪታኒያ እና በብሪታንያ ቅኝ የተገዙ ሃገራት በሚያደርጉት ውድድር ላይ ለመሳተፍ አውስትራሊያ ጎልድ ኮስት ከተማ ከገቡት 8 ሺህ ያህል አትሌቶች 205 ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ሌሎች 50 የሚሆኑት ደግሞ ...
Read More »የሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) የሕወሃት ጄኔራሎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ የገቡትን የሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ መሆኑ ታወቀ። የሃገር ሽማግሌዎቹ ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ጫና እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። የአብዲ ኢሌ አስተዳደር ለሕወሃት ጄኔራሎችና ለደህንነቶች ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ሽማግሌዎቹ ወደ ሶማሌ ክልል እንዲመለሱ ግፊት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። ከአብዲ ኢሌ በድብቅ ገንዘብ ከተከፈላቸው ጄኔራሎቹ መካከልም ገብሬ ዲላና ማአሾ እንደሚገኙበትም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። ለአቤቱታ ወደ አዲስ ...
Read More »የሜድሮክና ኢዛና የወርቅ አውጪ ኩባንያዎች ከመመሪያ ወጭ ወርቅ ሲሸጡ ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14 /2010 ) የሼህ መሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሜድሮክ ጎልድ እንዲሁም የሕወሓት ንብረት የሆነው ኢዛና ጎልድ ከቤሄራዊ ባንክ መመሪያ ወጭ በልዩ ድጋፍ ወርቅ ሲሸጡ መቆየታቸው ተገለጸ። በሌላም በኩል የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከብር ምንዛሪ ለውጥ ጋር በተያያዘ መገምገማቸው ታወቀ ።ቤተሰቦቻቸውንም ወደ አሜሪካ አሽሽተዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜድሮክ ጎልድ ባለፉት 20 ዓመታት ከሻኪሶ የሚያወጣውን ወርቅ ...
Read More »