በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡
(ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ክፍል ተብሎ በአዲስ መልክ በተዘጋጃው የሂሳብ መማሪያ መጽሃፍ ላይ ሆን ተብሎ የትግርኛ ማብራሪያ መለጠፉ በክልሉ መምህራንና ተማሪዎች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መሆኑን ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከአሁን በፊት በብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ተከስቶ የነበረው ስህተት፣የክልሉ መስህብ ቦታ ስለሆነው የራስ ዳሸን ተራራ መገኛ በተለያዩ ጊዜያት በመማሪያ መጽሐፍትና የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች የሚተላለፈው መልዕክት አግባብ እንዳልሆነ መምህራኑ ይናገራሉ፡፡
እንደዚህ ያለው ተደጋጋሚ ጥፋት ሆን ተብሎ የሚሰራ በክልሉ መምህራንና ተማሪዎች ላይ አልፎም በአመራሩ አካባቢ የህውሃትን የበላይነት ለመፍጠር እንደሚደረግ ሴራ አድርገው እንደሚለከቱት መምህራን ይናገራሉ።
በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ክፍል የተማሪዎች መማሪያ በሚል የተላከው መጽሐፍ ላይ ድጋሚ ስህተት መፈጠሩ ሆን ተብሎ እንጅ በስህተት ነው ለማለት እንደማያስደፍር መምህራን ተናግረዋል፡፡
ከአሁን በፊት የተሰሩ ስህተቶች ላይ የክልሉ መንግስት ተቃውሞ አለማሰማቱ ስህተቶች እንዲደጋገሙ እንዳደረጋቸው ምሁራኑ ገልጸዋል፡፡