ከ4 ሺ በላይ የሶማሊ ክልል ዜጎች ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ ተሰደዱ

ከ4 ሺ በላይ የሶማሊ ክልል ዜጎች ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ ተሰደዱ (ኢሳት ሐምሌ 27/2010)የሶማሊ ክልል ተወላጆች የአብዲ አሌን አገዛዝ ለመቃወምና ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ድጋፋቸውን ለመግለጽ በድሬዳዋ የሚያካሂዱትን ስብሰባ በሃይል ለመቆጣጠር ወደ ስፍራው ያቀኑት የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት፣ በፌደራል ፖሊሶች እንዲመለሱ ከተደረጉ በሁዋላ በመንገዳቸው ላይ በአይሻ ወረዳ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ4ሺ 500 በላይ ዜጎች ወደ ጅቡቲና ወደ ሶማሊላንድ መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የጅቡቲ መንግስት ...

Read More »

በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ከመሃል አገር የሄዱ ሰራተኞች እየታሰሩ ነው ቤተሰቦቻቸው አድራሻዎቻቸውን ማወቅ አልቻንም ሲሉ ተናግረዋል።

(ኢሳት ሐምሌ 27/2010)በመቀሌ፣ ዓድዋ፣ አክሱምና አዲግራት አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሾፌሮችን፤ በተለያዩ የስራ ጉዳዮች ከመሃል አገር ለስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ካለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ “ሰላዮች ናችሁ” በሚል እያሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል። ካለምንም ጥፋታቸው ከስራ ገበታቸው፣ ከመንገድ ላይ ታፍነው የተያዙት ዜጎችን አድራሻ የት እንደታሰሩና፤ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ ባለመቻላቸው ቤተሰቦቻቸው ስጋት ላይ ወድቀዋል። ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው አድራሻቸው የጠፉ ዜጎችን ...

Read More »

በትግራይ ክልል የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ መባሉ ትከክል አይደለም ሲል ፖሊስ አስታወቀ

(ኢሳት ሐምሌ 27/2010) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የ መከላከል አባላት ዋሉ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክል አይደለም ብሎአል። በወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀረ-ሽብርና የተደራጁ ወንጀሎኞች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ እንደገለፁት፣ የሃገሪቱ ክልሎች የፖሊስ አባላትን እንደሚያሰማሩ ተናግረው፣ በትግራይ ክልልም አባላቱን በማሰማራት ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ “በማህበራዊ ሚዲያ የፖሊስ አባላቱ መቀሌ አየር ማረፊያ ላይ በክልል የፖሊስ ...

Read More »

በደሴ ከተማ አንድ ተጠርጣሪ ወጣትን ለመያዝ በተፈጠረ ግርግር የትራንስፖርት አገልግሎት ለሰዓታት ተቋረጠ

(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)ነዋሪነቱ አራዳ በመባል በሚታወቀው የደሴ ከተማ ኗሪ የሆነውን ወጣት ባዬን ለመያዝ ፖሊስ የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክር ሁኔታውን በቅጡ ባልተረዱ የአካባቢው ነዋሪዎችና በፀጥታ አስከባሪዎች መሃከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ተጠርጣሪውን ይዘው የአዲስ አበባ ታርጋ ባላት ሲቪል መኪና ሲጓዙ በነበሩት ፖሊሶች ላይ በከተማው መውጫ ኬላ አቅራቢያ ወጣቶች ግርግር በመፍጠር የተሽከርካሪዋን መስታወት በመስበር ግለሰቡን አስመልጠዋል። የፀጥታ አስከባሪዎቹ ጉዳት ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ተወላጆች ታሪካዊ ያሉትን ሁለተኛ ጉባኤያቸውን በድሬዳዋ በማካሄድ ላይ ናቸው

(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)የአብዲ ኢሌን አገዛዝ የሚቃወሙ የክልሉ ተወላጆች ሁለተኛ ስብሰባዎችን በድሬዳዋ ከተማ ላይ በማካሄድ ላይ ናቸው። የክልሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ተደርጎ የነበረው የመጀመሪያው ስብሰባ በአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተደናቀፈ ቢሆንም፣ ዛሬ የተጀመረው የድሬዳዋው ስብሰባ ግን እስካሁን በሰላም እየተካሄደ ነው። የስብሰባው አስተባባሪዎች እንደሚሉት፣ ሶስተኛውን ስብሰባ ጅግጀጋ ላይ ለማድረግ እቅድ አላቸው። አስተባባሪዎቹ ...

Read More »

የአንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

የአንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ (ኢሳት ሐምሌ 26/2010)በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ 1948 ዓ.ም የተወለደው አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ባጋጠመው የኩላሊት ህመም በተወለደ በ62 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ላለፍት 42 ዓመታት የመድረክ ንጉስ እንደነበር በሙያ ባልደረቦቹና በጥበብ አድናቂዎች የተመሰከረለት ፍቃዱ ተክለማሪያም ኦቴሎ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ቴዎድሮስ፣ ንጉሥ አርማህ፣ መቃብር ቆፋሪውና የሬሣ ...

Read More »

በዚምባቡዌ ሀራሬ በተከሰተ ግጭት ሶስት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በዚምባቡዌ ከተካሄደው ምርጫ ጋር በተያየዘ በዋና ከተማዋ ሀራሬ በተከሰተ ግጭት ሶስት ሰዎች  ተገደሉ። በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ ገዥው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አጭበርብሯል የሚሉ በርካታ ወጣቶች በጎዳናዎች ላይ ድንጋይ በመርወርወር ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በዚህ ወቅት ወታደሮች ድንጋይ ሲወረውሩ በነበሩት ተቃዋሚዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የሶስት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ ተነግሯል። ኤም ዲ ሲ የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲ ስብስብ መንግስት የወሰደውን ርምጃ ያልተመጣጠነ ...

Read More »

የፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) የአንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ስነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ። ከቀብር ስነ ስርዓቱ ቀደም ብሎ በብሔራዊ ትያትር ቤት በርካታ አድናቂዎቹና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት አስከሬኑ አሰኛኘት ተድርጎለታል። የአንጋፋው ከያኒ ፍቃዱ ተክለማሪያም የቀብር ስነ ስርዓት  አጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አድናቂቆቹ እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ከመንግስት ባለስልጣናት መካከልም የውጭ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልዩነታቸውን አስወግደው በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሱ አራት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልዩነታቸውን አስወግደው በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ሂጅራ ፋውንዴሽን፣ በድር ኢትዮጵያ፡ ሰላም ፋውንዴሽንና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊ ህብረት በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ አንድነታቸውን የሚያረጋግጡ ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል። አራቱን የኢትዮጵያ ሙስሊም ተቋማትን በመሽምገል ከስምምነት እንዲደርሱ ያደረጉት ከሀገር ቤት የመጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መሆናቸውም ታውቋል። ትላንት ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010)በወታደራዊ ልዩ ልዩ  ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ለመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ምህረት የተደረገው በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ ነው ተብሏል። በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት እንደተደረገላቸው ታውቋል። የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው የሰራዊት አባላት ተቋሙ ባዘጋጃቸው አካባቢዎች ባሉ ጽህፈት ቤቶች በአካልም ሆነ በተዘጋጀ ፎርም ...

Read More »