ከ4 ሺ በላይ የሶማሊ ክልል ዜጎች ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ ተሰደዱ

ከ4 ሺ በላይ የሶማሊ ክልል ዜጎች ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ ተሰደዱ
(ኢሳት ሐምሌ 27/2010)የሶማሊ ክልል ተወላጆች የአብዲ አሌን አገዛዝ ለመቃወምና ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ድጋፋቸውን ለመግለጽ በድሬዳዋ የሚያካሂዱትን ስብሰባ በሃይል ለመቆጣጠር ወደ ስፍራው ያቀኑት የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት፣ በፌደራል ፖሊሶች እንዲመለሱ ከተደረጉ በሁዋላ በመንገዳቸው ላይ በአይሻ ወረዳ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ4ሺ 500 በላይ ዜጎች ወደ ጅቡቲና ወደ ሶማሊላንድ መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የጅቡቲ መንግስት ስደተኞችን መቀበሉን ምንጮች ነዋሪዎች ገልጸዋል። ወታደሮቹ በፈጸሙት ጥቃት ከ6 ያላነሱ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ከ80 በላይ ሰዎች ተደብድበው መታሰራቸውን ከእነሱም መካከል 20 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ጦሩን ሻለቃ አሊና ሻለቃ ዘከርያ የተባሉ የልዩ ሃይል አባላት ጥቃቱን ማስተባባራቸው፣ አይሻ ወረዳ ላይ ለሚሰራው የንፋስ ሐይል ማመንጫ ስራን የሚጠብቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢው ሄደው ጥቃት ሲፈጸም ማየታቸውን እና በሰላም እንዲያመልጡ መርዳታቸውን ተናግረዋል።