(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 1/2010)ጂጂጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን በማረጋጋት ላይ መሆኑ ተገለጸ። ላለፉት ሶስት ቀናት በቀውስ ውስጥ የቆየችው ጂጂጋ በአንጻራዊ ሁኔታ መረጋጋት እንደሚታይባት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ኢሳት ያነጋገራቸውና በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋ። መከላከያ ሰራዊቱ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን መጠነኛ ለውጥ እያየን ነው ብለዋል። በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች አሁንም ተደብቀው ያሉ ነዋሪዎች ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። በድሬዳዋም ዛሬ ...
Read More »ሶማሌ ክልል የልዩ ፖሊስ አመራር አባላት ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 1/2010) የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አብዲ ኢሌ ቁልፍ የልዩ ፖሊስ አመራር አባላት መታሰራቸው ተገለጸ። ከክልሉ ፕሬዝዳንትነታቸው ተነስተው በሌላ ሰው የተተኩት አብዲ ኢሌ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። በኋላ ላይ ግን አብዲ ኢሌ በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ጅጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት ወደ አዲስ አበባ እንደተወሰዱ ዘገባዎች አመልክተዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂጂጋ ...
Read More »በጅግጅጋ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን መቆጣጠሩን እንዲሁም በሶማሊ ክልል የነበረውን ሁኔታ ሳፋ አድርገን እንዘግባለን።
(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)በጅግጅጋ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ተቆጣጠረ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የአብዲ ኢሌ ልዩ ሃይል አባላት እና እርሱ ያደራጃቸው ወጣቶች በክልሉ በሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት በመፈጸም፣ የበርካታ ዜጎች ህይወት እንዲጠፋ አድርገዋል። ከ7 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። የሌሎች ብሄሮች እና አብዲ ኢሌን ይቃወማሉ የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ንብረት ተዘርፏል፤ ከፍተኛ ሃብትና ንብረትም ወድሟል። በርካታ ዜጎች ሚካኤል ቤተከርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ያለፉትን 2 ...
Read More »(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)የሶማሌ ክልል ተወካዮች የጋራ የምክክር መድረክ ላለፉት ሦስት ቀናት በድሬዳዋ ሲያካሂዱ የቆዩትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ባወጡት መግለጫ ክልሉን እየመሩ ያሉ ሰዎች ከሥልጣናቸው እንዲነሱና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። ዛሬም ሰዎች እየተገደሉ ነው።
Read More »በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ላይ በተነሳ ተቃውሞ ከፍተኛ ውድመት ደረሰ
(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)ተቃውሞው የክልሉ መንግስት ከመንገድ ስራ ጋር በተያያዘ በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ነው። ይህን ተከትሎ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል። ይህንን ተከትሎ የከተማው ህዝብ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አቃጥሏል። በዛሬው ተቃውሞ የተርጫ ከተማ ከንቲባ የአቶ አንበሰ ኡርካ ንግድቤትና መኖሪያ ቤት፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አንድነት አሸናፊ መኖሪያ ቤት፣ የገቢዎችና ማዘጋጃ ቤቶች ተቃጥለዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች የዞኑ አስተዳዳሪና የድርጅት ጽ/ቤትን ተጠያቂ ...
Read More »የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከኮለኔል መንግስቱ ጋር የተነሱትን ፎቶ አነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ጋር መገናኘታቸውና ፎቶ መነሳታቸው ከኢትዮጵያውያን አልፎ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ መሆኑ ታወቀ። ይህን ተከትሎም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኮለኔል መንግስቱ ጋር የተነሱትን ፎቶ ከማህበራዊ ገጻቸው ላይ መሰረዛቸው ተሰምቷል። ያያዙትንም ጽሁፍ አጥፍተውታል። አለም አቀፉ የመገናኛ ብዙሃን ቢቢሲ በድረገጹ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባሰራጨው ጽሁፍ አቶ ሃይለማርያም ኮለኔል መንግስቱን ያገኙት ...
Read More »አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን ቤተሰቦች ለመደገፍ የ25 ሚሊየን ብር ስጦታ ተደረገላቸው
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈውን የብአዴን አመራር አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን ቤተሰቦች ለመደገፍ ባለሃብቶች የ25 ሚሊየን ብር ስጦታ ማድረጋቸው ታወቀ። አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ በብአዴን በኩል ካሉ ግንባር ቀደሞች አንዱ መሆናቸውም ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሎስ አንጀለስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ባካሄዱት ውይይት አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን በስም ጠቅሰው አስተዋጿቸው የጎላ እንደነበር መስክረዋል። የብአዴን የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የክብር ተናጋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የክብር ተናጋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተጠየቀ። በመንግስታቱ ድርጅት የስዊዲን አምባሳደር ኦሎፍ እስኩግ በጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም መፍጠር የቻሉ መሪ በመሆናቸው በምክር ቤቱ የክብር ተናጋሪ እንዲሆን መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል። ተስፋ የቆረጥንበትን የሁለቱን ሀገራት ፍጥጫ በአጭር ጊዜ መፍትሄ የሰጡ መሪ በማለትም አምባሳደሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። በሌላ ...
Read More »የጭልጋ ወረዳ አመራሮች ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም በአማራና ቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱ 7 የጭልጋ ወረዳ አመራሮች መታሰራቸው ታወቀ። በአማራ ክልል ፖሊስ የተያዙት አመራሮች በህወሀት የሚደገፈውን የቅማንት ኮሚቴ በማገዝ በአካባቢው ግጭት እንዲፈጠር ማድረጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በግጭቱ የተነሳ በጭልጋ ወረዳ አይከል ዙሪያ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ የንግድ ተቋማት እንደተዘጉም ለማወቅ ተችሏል። ለአንድ ሳምንት ተዘግቶ የነበረው የአይከል መንገድ ትላንት መከፈቱ ታውቋል። ...
Read More »በሶማሌ ክልል ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ ተሰደዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) በሶማሌ ልዩ ሃይል የሚፈጸመውን ጥቃት በመሸሽ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ መሰደዳቸው ታወቀ። ከትላንት ጀምሮ በደወሌ፣ አይሻና ሽንሌ ዞን የተሰማራውና በአብዲ ዒሌ የሚታዘዘው ልዩ ሃይል ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ህዝቡ በመሰደድ መጀመሩ ነው የተገለጸው። በጥቃቱም የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። የፌደራል ፖሊስ ህዝቡን ከልዩ ሃይሉ ጥቃት ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በድሬዳዋ በሶማሌ ክልል የሰብዓዊ መብት ...
Read More »