ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በቤልጂየም እና በሆላንድ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በአገር ውስጥ ለሚካሄደው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ድጋፋቸውን ገለጡ:: ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ይህን የገለጡት ባለፈው ቅዳሜ በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰልስ ፣ የኢድ አል ፈጥርን በአል ምክንያት በማድረግ ባዘጋጁት ዝግጅት ላይ ነው። የኢትዮጵያውያን ቤልጂየማውያን ሙስሊሞች መሀበር ሉቅማን መሪ የሆኑት አቶ አብየ ያሲን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለላፉት 9 ወራት ...
Read More »ESAT Ethiopian News August 28, 2012
ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በበርካታ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) የአብዴፓ ፕሬዚዳንት ተደብድበዋል፤የአንድነት ፓርቲ አባላትም እየታሰሩ ነው። በቂሊንጦ እስር ቤት፡የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር፦“መለስ መሞታቸው በቴሌቪዥን በተነገረበት ጊዜ ሌሎቹ ሲያለቅሱ፤ አንተ ስቀሀል” ተብለው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። አቶ ዘሪሁን ከደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ብዛት ፊታቸው አባብጦና መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሲያነክሱ መታየታቸውን ነው ፍኖተ-ነፃነት ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ የዘገበው። ለምን ይህ ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ሲጠይቁ፦ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጓደኞቹ የመጎብኘት እድል አገኘ::
ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) ኢሳት የማረሚያ ቤቱን ምክትል አዛዥ በመጥቀስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደማይጎበኝ በዘገበ በሁለተኛው ቀን የመጎብኘት እድል ማግኘቱን ለማወቅ ተችሎአል። ከሃሙሱ የችሎት ውሎ በኋላ ወደ ቃሊቲ የተላከው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዞን አራት ተብሎ በሚጠራውየእሥረኞች ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ተመስገን ከጓደኞቹ ጋር ለ 10 ደቂቃዎች እንዲያወራ ቢፈቀድለትም፣ ሰለምታዎችን ከመለዋጥ በስተቀር ስለ እስሩ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልቻለም። አለማቀፍ ድርጅቶች ...
Read More »አቡነ መቃርዮስ ታጋዮችን ለማበረታታ ኤርትራ ገቡ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ አቡነ መቃርዮስ ኤርትራ ገቡ። ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ፤ አስመራ የገቡት በኢትዮጲያ ስርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጲያ የፖለቲካ ሃይሎችን ለማበረታታት ነው ተብሏል። ስልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጲያ መንግስት በሃይል ለመጣል መሳሪያ ያነሱ የኢትዮጲያ የተቋውሞ ሃይላት በዋናነት የሚነሱትና ድጋፍ የሚደረግላቸው በኤርትራ መንግስት መሆኑ ይታወቃል። በኢትዮጲያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እኩልነት ነፃነትና መብትን ለማረጋገጥ ያለው እድል መዘጋቱን የሚገልፁት ወገኖች ለሐገሪቱ ችግር ...
Read More »የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት አቶ መለስ ከፋፍይ አንባገነን ነበሩ አሉ
(Aug. 27) ጄኖሳይድ ወች በመባል የሚታወቀው ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን፤ አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ አደገኛ የሆነ የዘር መከፋፈልና፤ ጥቂት የአንድ ብሄረሰብ የበላይነትን አውርሰው ያለፉ አምባገነን መሪ ነበሩ ሲሉ ተናገሩ። በአለማችን ላይ የዘር ፍጅትን ለመከላከል የሚሰራው የዚሁ ድርጅት ፕሬዚዳንትና በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ የግጭትና የዘር ፍጅት ጥናት የምርምር ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ስታንተን አቶ መለስ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍና በደል ከመፈጸም አልፈው፤ ...
Read More »መኢአድ ሁሉን አቀፍ ጉባኤ እንዲጠራ ጠየቀ
(Aug. 27) የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫዎችን እያወጡ ሲሆን፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ባወጣው መግለጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ሁሉን አቀፍ ጉባኤ እንዲጠራ ጠይቋል። የሕወሀት/ኢህአዴግ አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ አደረሳቸው ያላቸውን በደሎች የዘረዘረው መግለጫ፤ “የኢትዮጵያ ህዝብ ከአጼ ሀይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ የሚያነሳው የነጻነት ጥያቄ እንዳልተመለሰ ጠቅሶ፤ የህዝብ ብሶት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ብዙ ደም ስለፈሰሰና የአገር ኢኮኖሚ ...
Read More »ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የመገናኛ ብዙሃንን የለቅሶ ሽፋን ተቹ
(Aug. 27) የመንገስት መገናኛ ብዙሀን ስለ አቶ መለስ ጀግንነትና እንከን የለሽነት የሚያቀርቡት የግለሰብን ተክለ-ሰውነት ወይንም ፕረሰናሊቲ ከልት የመገንባት፤ እንዲሁም፤ በአቶ መለስና በፓርቲያቸው የተሰሩ ስህተቶችንና ደካማ ጎኖችን እንድንረሳ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ጽሁፍ አቶ መለስ ሰው እንደመሆናቸው፤ ድክመቶችና ስህተቶችም እያሉባቸው፤ እንደእንከን የለሽ ሰው የማቅረቡ ሂደት መጪው ትውልድ ከአቶ መለስ ህስተት ...
Read More »ህዝቡ ለአቶ መለስ ሀዘኑን እንዲገልጽ ጫናዎች እየተደረጉበት ነው
(Aug. 27) የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ሀዘኑን እንዲገልጽ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት እንደሆነ ከኢትዮጵያ የሚመጡት መረጃዎች አስረዱ። ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያሳየው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ሀዘኑን እንዲገልጽ ታዞ እንደነበር ታውቋል። በዚህም መሰረት፤ ባለፈው አርብ በጎንደር መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የሀዘን መድረክ ላይ፤ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ከስራ መግቢያ ሰዓት ቀደም ብለው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ40 ...
Read More »የተመስገ ደሳለኝን እስራት አምነስቲ አወገዘ
(Aug. 27) የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እስራት፤ መንግስት የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች የጥቃት ኢላማ ማድረጉን እንደሚቀጥልበት ጠቋሚ ነው፤ ሲል አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስጋቱን ገለጠ። አቶ ተመስገን ደሳለኝ ባለፈው ሀሙስ መታሰሩ የሚያሳየው ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላም ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች እንዳልተቀየሩ ነው ሲሉ ክሌር ቤስተን የአምነስቲ አለማቀፍ የኢትዮጵያ ተመራማሪ ተናግረዋል። ተመስገን የታሰረው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ሲጠቀምና ...
Read More »