የአቶ ሀይለማርያም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ኢህአዴግን እያወዛገበ ነው

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአራት ቀናት በፊት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ይፋ ባደረገበት ወቅት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤አቶ መለስን ተክተው በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ መወሰኑን ይፋ ቢያደርግም፤ በተለይ በህወሀት በኩል በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ተቃውሞ እስካሁን  የ አቶ ሀይለማርያም ሹመት ሊጸድቅላቸው እንዳልቻለ  የኢሳት የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል። አቶ ...

Read More »

የመለስን እረፍት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ አምናለሁ ሲሉ ክብርት አና ጎሜዝ ተናገሩ

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ፓርላማ አባልና በ1997 ዓም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡት ክብርት አና ጎሜዝ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ በማንም ሰው ሞት  መደሰት ተገቢ ባይሆንም፣ የመለስን ሞት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። መለስ ዜናዊ አምባገነን፣ የገዛ ህዝቡን ጨፍልቆ የገዛ ነው ያሉት ክብርት አና ጎሜዝ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ የመለስን ስራዎች እያየ ...

Read More »

የኩማ አስተዳደር በይፋ ድንኳን ተክሎ ለቅሶ ተቀመጠ

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኩማ አስተዳደር በተለምዶ ማዘጋጃ ቤት ተብሎ በሚጠራው ቅጥር ግቢ ውስጥ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን  ሞት አስመልክቶ ሁለት ትልልቅ ድንኩዋኖችን በግቢው ውስጥ ተክሎአል። አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግስት በተለየ የከተማዋ ነዋሪዎች ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ቦታ ያስፈልጋል በሚል ሁለት ትልልቅ ድንኩዋን ትላንት የተከለ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ሐዘናቸውን በለቅሶ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በይፋ ባይገለጽም የአቶ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዳይጎበኝ በበላይ አካል ተከልክሏል” ይላሉ የማረሚያ ቤት ምክትል ኃላፊ

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከትላንት በስተያ ዕለት በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16 ወንጀል ችሎት የዋስትና መብቱ ተገፎ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከላከል የተፈረደበት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰረበት ዞን /ቀጠና/ እና ክፍል አልታወቀም፤ ሊጎበኙት የመጡ ሰዎች ሁሉ እንዳያገኙት ተከልክለዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ መጥተው አለ የተባለበት ...

Read More »

የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ከህዝብ እይታ መጥፋት አነጋጋሪ እንደሆነ ነው

ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ባለሀብቱ ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲን በብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአት እንዲሁም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን አቀባባል ዝግጅት ላይ አልተገኙም። አንዳንድ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ባለሀብቱ በሳውዲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ይህንን መረጃ ግን ከነጻ ወገን ማረጋጋጥ አልተቻለም። የባለሀብቱ ኩባንያ የሆነው ሚድሮክ ሰራተኞች በአቶ መለስ ዜና እረፍት ሀዘናቸውን ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን ባለስልጣኖች አቶ መለስ ዜናዊን አርዓያ በማድረግ ተከትለው እንዲሄዱ ተማጸኑ

ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሀይወት ዘመናቸው አቶ መለስ የያዙት  ዓላማ የጥቂቶች ዓላማ ከሆነ ሞት ነበር ” ብለዋል ። የመንግስትና የኢህአዴግ አመራርም የህዝቡን መልዕክት ተቀብለን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ አደርገን ለመከተል ወስነናል የሚሉት አቶ በረከት፤ ሌሎች ባለስልጣኖችና የኢህአዴግ አመራር አካላት፣ ህዝቡ እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም ተማጽነዋል። ኢሳት በትንናት ዘገባው አንድ የብአዴን ...

Read More »

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ

ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የፕትርክና ታሪክ አወዛጋቢ የሆኑት ብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች ዲፐሎማቶች በተገኙበት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል። ከሃምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ 20ኛ አመት በአለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ፣ በድንገት ማረፋቸው የብዙዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው። በተለይም የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ...

Read More »

ዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ

ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዐቃቤ ህግ ፍትህ ጋዜጣ እንዲታገድ ጠይቋል ለብይን ለነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ተቀጥሯል ሃሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም፡- “ቀደም ሲል ጀምሮ በበርካታ ኢትዮጵያዊያን የነበረው የለውጥና የነፃነት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንሥትሩን ሞት ተከትሎ ተነቃቅቷል፤ ብዙው ሕዝብ ከእንግዲህ ኢህአዴግን ማየት አይፈልግም፤ ይህን የብዙሃን ሕዝብ የለውጥ መንፈስ ጠንቅቆ የሚያውቀው አሁን በግላጭ ወደ ሥልጣን እየመጣ ያለው ...

Read More »

ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን ለማሰፈታት ሸምግልና እየተካሄደ ነው

ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ የሚመራው ራሱን “የኢትዮጽያ የሸማግሌዎች ኀብረት” በሚል የሚጠራው ቡድን ትላንት ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም፣  ማምሻውን በሸራተን ሆቴል በሰጠው መግለጫ “ሰላም ወዳድ ነበሩ” ያላቸውን በአቶ መለስ ዜናዊ ፤ዜና ዕረፍት የተሰማውን ሐዘን በገለጸበት መግለጫው በመጪው መስከረም ወር በዓልን አስታኮ ለእስረኞች ምህረት ለማድረግ ጠ/ሚኒስትሩ ቃል ገብተው ነበር ሲል ተናገረ። ፕሮፌሰር ኤፍሬም አሁን ...

Read More »

የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ሌሎች ጓዶቻቸው ለህዝብ ድጋፍ ማግኛ እየዋሉት ነው ተባለ

ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ መንግስትና ነባር ታጋዮች ፣ በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማሳበሰብና የተዳከመውንና በቋፍ ላይ የሚገኘውን ፓርቲያቸውን ነፍስ ለማዘራት እየተሯሯጡ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮቻችን ገልጠዋል። የአብአዴን ኢህአዴግ የአመራር አባል የሆነው ምንጫችን እንደገለጠው፣ ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ጭንቅት ውስጥ ይገኛል። በአንድ በኩል “የታጋይ መለስ የሽኝት ኮሚቴ” የሚል ኮሚቴ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች በማቋቋም ህዝቡ ለድጋፍ ሰልፍ ...

Read More »