አቡነ መቃርዮስ ታጋዮችን ለማበረታታ ኤርትራ ገቡ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ አቡነ መቃርዮስ ኤርትራ ገቡ።
ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ፤ አስመራ የገቡት በኢትዮጲያ ስርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጲያ የፖለቲካ ሃይሎችን ለማበረታታት ነው ተብሏል።
ስልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጲያ መንግስት በሃይል ለመጣል መሳሪያ ያነሱ የኢትዮጲያ የተቋውሞ ሃይላት በዋናነት የሚነሱትና ድጋፍ የሚደረግላቸው በኤርትራ መንግስት መሆኑ ይታወቃል።
በኢትዮጲያ ውስጥ በሰላማዊ  መንገድ እኩልነት ነፃነትና መብትን ለማረጋገጥ ያለው እድል መዘጋቱን የሚገልፁት ወገኖች ለሐገሪቱ ችግር መፍቻቸው የሃይል መንገድ እንደሆነ በማመልከት ላይ ናቸው።
የጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትና በስርዓቱ ውስጥ ያለው መናጋት ለተቃውሞ ሃይላት እንቅስቃሴ ጥሩ አጋጣሚ ተደርጎ እየተወሰደ ሲገኝ፤ የብፁዕ አቡነ መቃርዮስ አስመራ መግባት ለተቃውሞ ሃይላቱ ታላቅ ማበረታቻ እንደሚሆንም ከወደዚያው የመጣው አስተያየት ያስረዳል።