(Sept. 12) የአውሮጳ ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጎሜዝ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን የሞቱት በሃምሌ (July) ወር መሆኑን አጋልጠው አንባገኑ የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጥር ይዞ ጭቆናውን ለመቀጠል ሲሞክር እና ይፋዊ የስልጣን ሽግግር አለማድረጉን የአውሮፓ ፓርላማ በቸልታ መመልከቱ አግባብ አለሞሆኑን በቅርቡ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ተናገሩ። በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጨቋኝ አገዛዝ እንዲቀጥል የማድረግ ሙከራ ለማስተካከል አለመጣሩ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የጋራ የውጭና የደህንነት ስትራቴጂክ ...
Read More »የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት በመከላከያ ውስጥ ያለውን ቅሬታ እንደሚያባብስ ተጠቆመ
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ማክሰኞ ዕለት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት ከብሔራዊ ተዋጽኦ አንጻር በመከላከያ ውስጥ ያለውን የቆየ ቅሬታ ማባባሱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ትላንት ከሕመማቸው በማገገም ላይ ባሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት 34 የመከላከያ ኮሎኔሎችን ወደ ብርጋዴር ጄኔራል ያሳደገ ሲሆን ከነዚህ ሹማምንት መካከል ከግማሸ በላይ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች መሆናቸው ከብሔር ...
Read More »አቶ አባይ ወልዱ አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ሊቀመንበር ሆኑ
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ በሟቹ በአቶ መለስ ምትክ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑትንና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ ኦህዴድ በበኩሉ ከህመም ጋር በተያያዘ የመልቀቂያ ደብዳቤ ባስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ምትክ የአ/አ ከተማ ከንቲባ የሆኑትን አቶ ኩማ ደመቅሳን መምረጡን ምንጫችን ጠቁሟል፡፡ አዲሱ አመራር አቶ ኃይለማርያም ...
Read More »በሊቢያ የአሜሪካ አምባሳደር ተገደሉ።
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሊቢያ ምሥራቃዊ ግዛት በቤንጋዚ በሚገኘው የ ዩናይትድ ስቴትስ ቆንስላ ታጣቂ ሚሊሺያዎች ድንገት በከፈቱት ጥቃት በአሜሪካ የሊቢያ አምባሳደርን ጨምሮ አራት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተገደሉ። ቢቢሲ እንደዘገበው፤ታጣቂዎቹ፤አምባሳደር ክርስቶፈር ስቴቨንስ እና ሦስት ሌሎች የዩናይትድስቴትስ ባለስልጣናትን የገደሉት፤ አሜሪካ ውስጥ በተዘጋጀና የነቢዩ መሀመድን ታሪክ ያጎደፈ ነው ባሉት ፊልም ምክንያት ተተቃውሟቸውን ለመግለጽ ነው። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እስካሁን ያረጋገጠው ...
Read More »ሀገሪቱን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ይመሯታል ተባለ
ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመስከረም ወር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በሚያካሂደው ምርጫ የሚመረጠው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ድርጅቱን ለስድስት ወራት ብቻ በጋራ እንደሚመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡ አቶ ሬድዋን ዛሬ ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ ቀጣዩ ጉባዔ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ...
Read More »በኢትዮጵያ የታሰሩት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች፤እንዲሁም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ሂሩት ክፍሌ ተፈቱ
ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን ለተባሉት ሁለቱ ዊድናውያን ጋዜጠኞች ይቅርታ ማድረጓን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታወቁ። ከስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች በተጨማሪ የ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ እና በነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ የተከሰሰች ሂሩት ክፍሌ በምህረት ተፈትተዋል። አሶሲየትድ ፕሬስ ባለስልጣኑን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተፈችዎቹ ይቅርታ የጸደቀው፤ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ ነው ። ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፐርሰን ...
Read More »የአመት በዓል ገበያ ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል
ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አመት ዋዜማ አዲስ አበባ የፍርሃትና የዝምታ ድባብ ሰፍሮባታል:: የአመት በዓል ገበያም ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል:: በመርካቶና በአዲሱ ገበያ አካባቢ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተው 50 ኪሎ ማኛ ጤፍ 1200 ብር ኩንታሉ 2400 ብር ጠቆር ያለው ጤፍና ሰርገኛ እንደ ደረጃው ከ1400 ብር እስከ 1800 ብር የኤልፎራ ዶሮ ብር 100 እየተሸጠ ሲሆን የሀበሻ ዶሮ በገበያ ላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ባንኮች በጠቅላላ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ በመከሰቱ ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ እንደተሳናቸው ተዘገበ
ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር፦”የዶላር ያለህ!” በሚል ርዕስ ባጠናቀረው ዘገባ የውጪ ምንዛሬ እጥረቱ ከተከሰተ የሰነበተ ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ግን ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክቷል። ከወራት በፊት በቂ የውጭ ምንዛሪ ያለ መሆኑ ቢገለጽም፣ አሁን በተጨባጭ የሚታየው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል-ብሏል ጋዜጣው። የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የባንኮችን ደጃፍ የሚረግጡ አስመጪዎች፤ <ሌተር ኦፍ ክሬዲት> ለመክፈት እና ማስመጣት የሚገባቸውን ምርት ለማምጣት ...
Read More »አዳማ በመጠጥ ውሀ እጥረት እየተሰቃየች ነው
ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት በጣለ ከባድ ዝናም ከቆቃ ወደ ናዝሬት የተዘረጋው ቧንቧ በመወሰዱ የ አዳማ ነዋሪዎች ለ 15 ቀናት በውሀ ጥም መቃጠላቸውን ተናገሩ። በድንገት ውሀ የተቋረጠባቸው የናዝሬት ነዋሪዎች፣ ችግሩ አልፎ አልፎ እንደሚከሰተው ቀላል መስሏቸው ከዛሬ ነገ ይሠራል በማለት በትዕግስት ቢጠብቁም፣ ችግሩ ተባብሶ 15 ቀናት እንደሞላዋቸው ተናግረዋል:: የከተማው ማዘጋጃ ቤት ነዋሪዎቹ እንዳሉት፤የከተማው ማዘጋጃ ቤት የተፈጠረውን ...
Read More »በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ድረድር ተጀመረ
(Sept. 10) በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ድረድር እየተካሄደ መሆኑን፤ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጪ ግንባር የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት ገለጡ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደተናገሩት ድርድሩ በናይሮቢ በኬንያ መንግስት አደራዳሪነት ባለፈው ሀሙስና አርብ ተካሄዷል። የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚደራደረው በሶስተኛ አገሮች መሆን እንዳለበት ጠይቆ የነበረ ሲሆን፤ ያንን ቅድመሁኔታ ሳይቀበል የቆየው የኢትዮጵያ ...
Read More »