አዳማ በመጠጥ ውሀ እጥረት እየተሰቃየች ነው

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት በጣለ ከባድ ዝናም ከቆቃ ወደ ናዝሬት  የተዘረጋው ቧንቧ በመወሰዱ የ አዳማ ነዋሪዎች ለ 15 ቀናት በውሀ ጥም መቃጠላቸውን ተናገሩ።

በድንገት ውሀ የተቋረጠባቸው የናዝሬት ነዋሪዎች፣ ችግሩ አልፎ አልፎ እንደሚከሰተው ቀላል  መስሏቸው ከዛሬ ነገ ይሠራል በማለት በትዕግስት ቢጠብቁም፣ ችግሩ ተባብሶ 15 ቀናት እንደሞላዋቸው ተናግረዋል::  የከተማው ማዘጋጃ ቤት

ነዋሪዎቹ እንዳሉት፤የከተማው ማዘጋጃ ቤት የተፈጠረውን ችግር ወዲያውኑ ለነዋሪው ሕዝብ ማሳወቅ ቢገባውም  ያን ባለማድረጉ ያለምንም መረጃ ሲሰቃዩ ከርመዋል።

በመጨረሻም ነዋሪዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት ፦“ምን ተፈጠረ?” በማለት ለማነጋጋር ወደ አዳማ ውኃና ፍሳሽ መሥሪያ ቤት

ሲሄዱ፣ ወደ ከተማ የሚገባው መስመር አደጋ  እንደደረሰበት መስማታቸው ገልጸዋል::

በአሁኑ ጊዜ ከአዲስ አበባና ከቅርብ ከተሞች በጄሪካን ውኃ እየገዙ የራሳቸውንና የልጆቻቸውን ጤንነት  ለመታደግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ  መፍትሔ ካልተገኘ በንፅህና ጉድለት በከተማው  ውስጥ ተላላፊ በሽታ ይከሰታል የሚል ሥጋት እንደገባቸውም ነዋሪዎቹ  ተናግረዋል::

ኢህአዴግ በቨርጂኒያ የራዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ሊያቋቁም ነው

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በውጪ አገር የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተዘገበ።

ኢህአዴግ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ኢሳት) ስርጭት ፤በአገር ቤት ውስጥ እንዳይተላለፍ ቢታገድም በውጪው ዓለም በሚገኘው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ተቀባይነት ማግኘቱ ስላሣሰበው እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመሆኑም መሰረቱን ቨርጂኒያ ላይ ያደረገና ከአሜሪካ- ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሌላው ዓለም ሚተላለፍ የራዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭት ለመክፈት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከወራት በሁዋላ ይከፈታል የተባለውን ይህን አዲስ ጣቢያ ገለልተኛ ለማስመሰል የሥርዓቱ አገልጋዮች በሆኑ ግለሰቦች ስም ለመክፈት የወሰነ ሲሆን፤ ለዚህ የታጩትም ሰዎች የሚያቋቁመት ጣቢያ ሚዛናዊ መረጃ የሚያቀርብ ገለልተኛ ሚዲያ እንደሆነ፤የገቢ ምንጫቸውም ከስፖንሰሮች እና ከማስታወቂያ የሚገኝ እንደሚሆን ከወዲሁ ማስወራት ጀምረዋል።

ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፍ ከታገደ በርካታ ወራት ቢቆጠሩም፤ ተጨባጭና ወቅታዊ መረጃዎችን በብቃት በማቅረብ ተዓማኒነቱንና የህዝብ አገልጋይነቱን በማስመስከሩ፤የተጋረጡበትን ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖ  በአሸናፊነት እየተወጣ መምጣቱ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide