የአመት በዓል ገበያ ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አመት ዋዜማ አዲስ አበባ የፍርሃትና  የዝምታ ድባብ ሰፍሮባታል:: የአመት በዓል ገበያም ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል::

በመርካቶና  በአዲሱ ገበያ አካባቢ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ  እንደተመለከተው 50 ኪሎ ማኛ ጤፍ 1200 ብር ኩንታሉ 2400 ብር ጠቆር ያለው ጤፍና ሰርገኛ እንደ ደረጃው ከ1400 ብር እስከ  1800 ብር የኤልፎራ ዶሮ ብር 100 እየተሸጠ ሲሆን የሀበሻ  ዶሮ  በገበያ ላይ እንደ ኪሎው  ከመቶ ሀምሳ  እስከ  210 እየተሸጠ ነው::

አንድ  እንቁላል 2 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን በግ ከ1300 እስከ  3500 ብር ነገር ግን በመርካቶ አካባቢ ግን ከዚህ ወደድ እንደሚል ዘጋቢያችን ገልፆልናል::  ቅቤ ከብር 150 እስከ 160 ሲሸጥ የሸኖ ለጋ ቅቤ ግን እስከ 200 ብር በመሸጥ ላይ ነው:: በሬ ከ15000 እስከ 20000 እየተሸጥ ነው::

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide