Uncategorized

በሱዳን የገዢው ፖርቲ ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011)ሱዳን ውስጥ ለተቃውሞ አደባባይየወጡ ወጣቶች የገዢውን ፖርቲ ጽሕፈት ቤት አቃጠሉ። የተቃውሞው መነሻ በነዳጅ እና በዳቦ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ተቃውሞው የተነሳውና የተቀጣጠለው ከርዕሰ መዲናዋ ካርቱም 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አትባራ በተባለው ከተማ ሲሆን በተቃውሞው የሱዳኑ ገዢ ፓርቲ ናሽናል ኮንግረስ ጽሕፈት ቤት ከመቃጠሉ ባሻገር በጎዳናዎችም ላይ እሳት እያነደደ መገኘቱን አልጀዚራ ዘግቧል። አንድ የሱዳን ፓውንድ ...

Read More »

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ።           የደርግንመንግስት በመቃወም ስርአቱን ከከዱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመጀምሪያው የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ1981 በኮለኔል መንግስቱሃይለማርያም ላይ የተካሄደው የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ላይ ከውጭ ሆነው ተሳታፊ እንደነበሩም መረዳት ተችሏል።           ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ትላንት ከናሚቢያ ዊንዲሆክ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንደተቀበሏቸው ...

Read More »

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ጸደቀ

(ኢሳትዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በኢትዮጵያ ከወሰንና ከማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚል የተዘጋጀው ረቂቃአዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ።           በ33 ተቃውሞ የጸደቀው ይህ አዋጅ እንዳይጸድቅ 10 የሕወሃት የፓርላማ አባላት በፊርማ አስቀድመው ጥያቄ አቅርበዋል።           ጥያቄያቸውም አዋጁ ሕገ መንግስቱን ይጻረራል የሚል ሲሆን የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ኮሚሽኑ የማማከር እንጂ የመወሰን ስልጣን ስለሌለው ሕገ መንግስት አይጻረርም በማለት ሞግተዋል።           “የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ለማቋቋም ...

Read More »

በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች ከ750 በላይ የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። የራያ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ለኢሳትእንደገለጸው ተቃውሞ ከተነሳበት ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ በተወሰደ የጅምላ እስር 761 የራያ ተወላጆች ታስረውበአራት የትግራይ እስር ቤቶች ውስጥ ታጉረዋል። ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ የሚገልጸው ኮሚቴው አንድ ሰው በድብደባ ምክንያት ህይወቱ ማለፉን አስታውቋል። ከታሰሩት በተጨማሪ በርካታ የራያ ተወላጆች ...

Read More »

በአማሮ ኬሌ በተከሰተ ግጭት በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ11/2011) ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦነግ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎችና በአማሮ ኬሌ ነዋሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት በሰውናንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስር በሚገኘውየአማሮ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ለሁለት ዓመት የዘለቀው ግጭት ሰሞኑን እንደ አዲስ ማገርሸቱን የአካባቢውነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የአንድ አርሶ አደር ህይወት የጠፋበት ግጭት ከትላንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ጃሎ የተሰኘ ቀበሌ በእሳት መውደሙንም ...

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ብር ጭኖ በሚጓዙ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች  ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመውጥቃት አንደኛው ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ተሽከርካሪዎቹ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ይዘው ሻኪሶ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለማድረስ እያመሩ እንደነበረ ታውቋል። ሻኪሶ ከተማ ለመድረስ 20 ኪሎሜትር ሲቀራቸው ጥቃቱ ...

Read More »

ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ ህግ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ የሚከለክል መመሪያ የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አወጣ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከመጋቢት23/2018 ጀምሮ መሳሪያዎቹን መጠቀም የተከለከለ በመሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ አምራቾች እንዲያወድሙ አሊያም ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡትላንት መመሪያ ወጥቷል። ከአውቶማቲክ መሳሪያዎች ውጭ ከፊል አውቶማቲክና አውቶማቲክ ያልሆኑ መሳሪያዎችን ገዝቶ መታጠቅ በማይፈቀድባት አሜሪካ የአሰቃቂ ግድያዎች እየጨመሩ መምጣት ብርቱ ተቃውሞን ሲያስከትል ቆይቷል። በተለይም ከአንድ ...

Read More »

የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ10/2011) የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ።           ለ12 አመታት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፈው ቅዳሜ በ94 አመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።           ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል።

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ብድር ከ550 ቢሊዮን ብር በለጠ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስትና ለግል ኩባንያዎች ያበደረው ብድር ከ550 ቢሊዮን ብር መብለጡ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮችለኢሳት እንደገለጹት ትልቁን ብድር የወሰደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ሲሆን የስኳር ኮርፖሬሽንና የባቡር ኮርፖሬሽንበተከታይነት ከፍተኛ ብድር መውሰዳቸው ተመልክቷል። ከ550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 74 በመቶውን 6 የመንግስት ድርጅቶች የወሰዱ ሲሆን የዚህም ጠቅላላ ድምር 413 ቢሊዮን ብር ያህል እንደሆነም ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። የብድሩ ...

Read More »

በአማራ ክልል ሶስት ቀበሌዎች በቁጥጥሩ ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) ከቅማንት የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው የቆዩ ሶስት ቀበሌዎችን በቁጥጥሩ ስር ማዋሉንየአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ላለፉት ሶስት ዓመታት ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆነው በቆዩት ጉባይ ጀጀቢት፣ሌንጫና መቃ በተሰኙ ቀበሌዎች የቅማንትን ጥያቄ በጉልበት ለመፍታት በሚፈልግ ሃይል አማካኘነት የተደራጀ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው መቆየቱን የኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ...

Read More »