Uncategorized

ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ ድርጅቶችን መለየቱ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 17/2011)ለገቢና ለወጭ ንግድ አገልግሎት በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ወስደውና ምርቶች ወደ ውጪ ልከው ገንዘቡን ወደ ሀገርቤት ያልመለሱ 240 ድርጅቶችን ብሔራዊ ባንክ መለየቱን አስታወቀ። ባለፉት አስራ አራት ዓመታት በርካታ አስመጪዎች የተለያዩ ምርቶችን እንዲያስመጡ ከተለያዩ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶላቸው ነበር። ነገር ግን ምርቱን ሳያስመጡ እንዲሁም ምርት ልከው ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሬን ሀገር ውስጥ ሳያስገቡ በመንግስት በተደረገ ጫና ከብሄራዊ ባንክ እገዳቸው ተነስቶላቸው ተጨማሪ ...

Read More »

በኢሳና አፋር ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት 18 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) በኢሳና አፋር ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት 18 ሰዎች መገደላቸው ተገደሉ። ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱ ወገኖች ተካሄደ በተባለውና በመሳሪያ በታገዘው  ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ የገዋኔና አዋሽ አካባቢ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ የኢትዮጵያ መንግስት የአፋር ንጹሃንን ህይወት እንዲታደግ በሚል መግለጫ አውጥቷል። አርዱፍ በግጭቱ ከኢሳዎች ጀርባ የጅቡቲ መንግስት የመሳሪያ ድጋፍ ያደርጋል ሲል ከሷል። ግጭቱ ...

Read More »

በኢንዶኔዥያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 አሻቀበ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)ኢንዶኔዥያን በመታው አውሎ ንፋስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ሲያሻቅብ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1ሺህ መብለጡ ታወቀ። በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም። በእሳተጎመራና በመሬት መደርመስ ጭምር የተዘጋው አውሎ ነፋስ የሙዚቃ ኮንሰርት በማሳየት ላይ የነበሩ ሙዚቀኞችን ጭምር ከመድረክ ጠርጎ ሲሄድ ታይቷል፣ ህንጻዎችም ፈራርሰዋል። 265 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ የሚኖርባትና 17ሺህ ያህል ደሴቶች የሚገኙባት ኢንዶኔዢያ በሳምንቱ መጨረሻ በገጠማት አደጋ ዋነኛው ...

Read More »

አቶ ፍጹም አረጋ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)በአሜሪካ ዋሽንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ በቆዩት በአቶ ካሳ ተክለብርሃን ምትክ አቶ ፍጹም አረጋ መሾማቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። እንዲሁም ለ27 ዓመታት በሕዉሃት ሰዎች ብቻ በርስትነት ተይዞ በቆየው ቻይና ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋ በአምባሳደርነት መሾማቸውም ተመልክቷል። በአጠቃላይ 59 ያህል ዲፕሎማቶች በተለያዩ ሃገሮች የተመደቡ ሲሆን የእነዚህ ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል። ቀደም ሲል ከተመደቡት 59 ሰዎች ውስጥ በሰብዓዊ መብት ...

Read More »

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ርምጃ እወስዳለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)በኦሮሚያ ክልል በግድያ፣በዘረፋና በገንዘብ ስርቆት ላይ ተሰማርተው በነበሩ ሃይሎች ላይ ርምጃ ለመውሰድ የጸጥታ አካላት መሰማራታቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።           በሌላም በኩል ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ተሳታፊ የሆኑ 15 ያህል ሰዎች አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።           የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ክልል ...

Read More »

በብሪታኒያ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሞት እየጨመረ ነው ተባለ

          (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) በብሪታኒያ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሞት ባለፉት 5 አመታት እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።           ባለፈውአመት ብቻ 600 ያህል የጎዳና ተዳዳሪዎች በእንግሊዝና በዌልስ ግዛት መሞታቸውን የብሪታኒያ መንግስት መረጃዎች አመልክተዋል።           ባለፉት ሁለት አመታት የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ሞት በ24 በመቶ መጨመሩም ታውቋል።           እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 ጀምሮ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ቁጥር በ169 በመቶ መጨመሩን የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘገባውን አቅርቧል። ይፋዊ ...

Read More »

አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የተደረገላቸው አቀባበል ከጠበቁት በላይ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) በጎንደርና በዳባት የተደረገላቸው አቀባበል ከጠበቁት በላይ እንደሆነባቸው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ገለጹ። አርበኛ መሳፍንት ከኢሳትጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የህዝብ ስሜት የከፈሉት መስዋዕትነት ዋጋ እንዳለው ያሳየ ሆኗል። ከ250 ጦራቸው ጋር ከጎንደር በኋላ ወደ ባህርዳር የገቡት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ነጻነትና ፍትህ እስኪረጋገጥ በትግላቸው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ የደረሱባቸውን ጉዳዮች ወደፊት በዝርዝር እንደሚገልጹና አሁን ባለው ለውጥ ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ...

Read More »

ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት የተጠራው ድርድር ሳይጀመር መጠናቀቁ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011)ለንደን ላይ ከ27 ዓመታት በፊት በአምባሳደር ኸርማንኮኸን የተጠራው ድርድር ከሻዕቢያና ሕዉሃት መሪዎች ጋር ሳይተያዩና ሳይጀመር መጠናቀቁን የመንግስት ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ተናገሩ። ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ስለድርድሩዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል። ከአማጽያን ጋር የተደረጉት ድርድሮች ሁሉ የቀድሞው መንግስት ዋና ተደራዳሪ የነበሩት ዶክተር አሻግሬ ይግለጡ ከኤርትራ ጋር ችግሩን ለመፍታት የፌደሬሽን አማራጭ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል። በህወሃት በኩል ...

Read More »

ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሃገር እንድትሆን እንሰራለን ተብሏል

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ/2011) ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሀገር እንድትሆንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የለውጥ ሃይሉ ጠንክሮ እንደሚሰራ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለኢሳት ገለጹ። በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ ያካሄደውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት የሰሜን አሜሪካ የጉዞ ዓላማ  ክልሉን በልማት፣በኢንቨስትመንት እና ...

Read More »

የኦነግ ወታደሮች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ተሰቷቸዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደሮች ጥቃት ከተፈጸመባቸው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ሰጥተናል ሲሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ ገለጹ።           በትላንትናው ዕለት ኦዴፓ ያወጣውን መግለጫምየጦርነት አዋጅ ነው ያሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ የመንግስት ሰራዊት በዛሬው እለት ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው ሲሉምተናግረዋል።           አዲስ አበባ በሚገኘውና በቅርቡ በመንግስት በተሰጣቸው ጽሕፈት ቤት መግለጫ የሰጡት አቶ ዳውድ ኢብሳ በዛሬው ዕለት ዶክተር ገዳን ጨምሮ ...

Read More »